
ርዕስ፦ | የስጋት ግምገማ መሣሪያ |
ኮድ፦ | A-11-SRCL-B-CH |
እትም፦ | 1.4 |
የሚመለከተው፦ | የእርሻ እና የአቅርቦት ሰንሰለት ሰርቲፊኬት ባለቤቶችን |
አፈጻጸም፦ | አስገዳጅ ይዘት |
ተፈጻሚነት የሚጀምርበት ቀን፦ | ጥር 5፣ 2018 ዓ.ም |
የሚያበቃበት ጊዜ፦ | እስከሚቀጥለው ማሳሰቢያ ድረስ |
የታተመበት ቀን፦ | ጥቅምት 3፣ 2018 ዓ.ም. |
ከሚከተለው ጋር ይገናኛል፦ | A-1-S-B-FA-V1.4 የሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው ግብርና ስታንዳርድ - የእርሻ መስፈርቶች |
የሚከተለውን ይተካል፦ |
ይህ ሰነድ ስለ ምንድን ነው?
የስጋት ግምገማ መሣሪያው የሚከተሉትን ያካተተ ነው፦
1. የስጋት ግምገማ በዝግጅት ምዕራፍ የሚከናወን እና ቢያንስ በየሦስት ዓመቱ መደገም ያለበት)።
በስጋት ግምገማው ውስጥ የሚካተቱት ርዕሰ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፦
አመራር እና ትረሰብሊቲ፦ የእርሻ ቦታ፣ ምርታማነት እና ትረሰብሊቲ።
የእርሻ ልምዶች፦ የአግሮኬሚካሎች አያያዝ፣ የአፈር ለምነት እና ጥበቃ።
የሥራ ሁኔታዎች፦ የቅሬታ አፈታት ሥርዓት፣ መገምገም እና መፍትሄ መስጠት (የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ የግዳጅ ሥራ፣ አድልዎ፣ በሥራ ቦታ የሚፈጸም ጥቃት እና ትንኮሳ)፣ የሥርዓተ ጾታ እኩልነት እንዲሁም የመኖሪያ እና የኑሮ ሁኔታዎች።
አካባቢ፦ ከፍተኛ የጥበቃ እሴት ያላቸው አካባቢዎች፣ የተፈጥሮ ሥነ-ምህዳሮች እና ዕፅዋት ጥበቃ እና ማሻሻያ።
2. መገምገም እና መፍትሄ መስጠት የስጋት ግምገማ (በ1ኛው ዓመት የሚከናወን እና ቢያንስ በየሦስት ዓመቱ መደገም ያለበት)።
በሬንፎረስት አሊያንስ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ እና የግዳጅ ሥራ የስጋት ካርታዎች መሠረት፣ መገምገም እና መፍትሄ መስጠት የስጋት ግምገማው ተፈጻሚ የሚሆነው ለሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ እና/ወይም ለግዳጅ ሥራ መካከለኛ/ከፍተኛ ስጋት በሚኖርበት ጊዜ ነው። ትልልቅ እና በተናጠል ሰርቲፋይድ የሆኑ እርሻዎች ስለ አድልዎ እንዲሁም ስለ የሥራ ቦታ ጥቃት እና ትንኮሳ የተዘጋጁ የማሻሻያ እርምጃዎችን ሁልጊዜ ይተገብራሉ።
የመገምገም እና መፍትሄ መስጠት የስጋት ግምገማ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ስጋቶችን ለመለየት እና እነዚያን ስጋቶች ለመቀነስ የሚያስችሉ እርምጃዎችን ለመጠቆም ጥቅም ላይ ይውላል።
ይህንን ሰነድ መቼ እና እንዴት መጠቀም ይቻላል?
የሰርቲፊኬት ባለቤቱ የስጋት ግምገማ መሣሪያውን እንደ መጠይቅ ይሞላል።
ለእያንዳንዱ ርዕሰ ጉዳይ አዎ ወይም አይ ተብለው የሚመለሱ የጥያቄዎች ስብስብ ይኖራል።
እንደ መልሱ ሁኔታ፣ የሚመከሩ የስጋት ቅነሳ እርምጃዎች በረድፉ ላይ ባለው ቀጣይ ሴል ውስጥ ይታያሉ።
አንድ ጥያቄ የማይመለከተው ከሆነ (ለምሳሌ በእርሻው ውስጥ ረግረግ ቦታ ከሌለ) N/A" (የለም) መመረጥ አለበት፤ በዚህ ጊዜ ምንም ዓይነት የቅነሳ እርምጃዎች አይታዩም።
የሰርቲፊኬት ባለቤቱ ለማያውቃቸው ወይም እርግጠኛ ላልሆነባቸው ጥያቄዎች፣ ተዛማጅ የቅነሳ እርምጃዎችን ለመከተል "አይደለም" የሚለው መመረጥ አለበት።
"የዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ከፍተኛ ስጋት" የቅነሳ እርምጃዎች ዝርዝር፣ ለእያንዳንዱ አገር እና ምርት ተፈጻሚ የሚሆኑትን የሬንፎረስት አሊያንስ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ እና የግዳጅ ሥራ ስጋት ካርታዎችን ያመለክታል። እስካሁን በስጋት ካርታዎቹ ውስጥ ላልተካተቱ አገሮች ወይም ሰብሎች፣ በተለዩት ስጋቶች ላይ የተመሠረቱ ተገቢ የቅነሳ እርምጃዎች መመረጥ አለባቸው። የሰርቲፊኬት ባለቤቱ በማንኛውም ጊዜ የሥራ ሂደቱን ማስቀመጥ እና መጠይቁን ለማጠናቀቅ ተመልሶ መምጣት ይችላል።
የእርሻ ስጋት ግምገማ መሣሪያውን ሲያጠናቅቁ፣ የሰርቲፊኬት ባለቤቱ ለእያንዳንዱ ለተለየ ስጋት የሬንፎረስት አሊያንስ የሚመክራቸውን የቅነሳ እርምጃዎች አጠቃላይ መግለጫ ያገኛል። የሰርቲፊኬት ባለቤቶች ለራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ ይበልጥ ተስማሚ የሆኑ አማራጭ የቅነሳ እርምጃዎችን መጠቆም ይችላሉ። ይህ "የሰርቲፊኬት ባለቤቱ የራሱ የቅነሳ እርምጃዎች" ተብሎ በተሰየመው አምድ ውስጥ ሊገባ ይችላል።
እነዚህ የቅነሳ እርምጃዎች በአመራር ዕቅዱ ውስጥ መካተት እና አፈጻጸማቸውም ክትትል ሊደረግበት ይገባል። ለእያንዳንዱ ለተለየ ስጋት የቅነሳ እርምጃዎችን መተግበር ግዴታ ነው።
አነስተኛ እና ትልልቅ እርሻዎችን በሚያካትቱ ቡድኖች ውስጥ፣ ወይም በትልልቅ እርሻዎች ብቻ በተዋቀሩ ቡድኖች ውስጥ፣ እያንዳንዱ ትልቅ እርሻ መላውን ቡድን ከሚያጠቃልለው የቡድን አመራር ግምገማ በተጨማሪ የራሱን የስጋት ግምገማ ማከናወን አለበት።
ኦዲተሮች የስጋት ግምገማ መከናወኑን፣ የቅነሳ እርምጃዎች በአመራር ዕቅዱ ውስጥ መካተታቸውን እና እየተተገበሩ መሆኑን ያረጋግጣሉ። እንዲሁም፣ የሰርቲፊኬት ባለቤቱ የተለዩ የቅነሳ እርምጃዎችን ለመውሰድ ከወሰነ፣ ይህ በማስረጃ መደገፍ አለበት።