አመላካች አባሪ v1.1

Prev Next

ርዕስ፦

አመላካች አባሪ

ኮድ፦

A—SRCL-B-CH

እትም፦

1.1

የሚመለከተው፦

የእርሻ ሰርቲፊኬት ባለቤቶች

አፈጻጸም፦

አስገዳጅ ይዘት

ተፈጻሚነት የሚጀምርበት ቀን፦

የካቲት 22፣ 2018 ዓ.ም

የሚያበቃበት ጊዜ፦

እስከሚቀጥለው ማሳሰቢያ ድረስ

የታተመበት ቀን፦

ጳጉሜ 12፣ 2017 ዓ.ም.

ከሚከተለው ጋር ይገናኛል

A-1-S-B-F-V1.4 የሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው ግብርና ስታንዳርድ።

A-33-R-B-FA-V1.0 የሬንፎረስት አሊያንስ ተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ።

የሚከተለውን ይተካል፦

A—SRCL-B-CH-V1.0-አመላካች አባሪ

ይህ ሰነድ ስለ ምንድን ነው?

ይህ አባሪ የሬንፎረስት አሊያንስ የሰርቲፊኬሽን ስታንዳርድ መስፈርት 1.7.1 አተገባበርን በተመለከተ ተጨማሪ አስገዳጅ መረጃን ይሰጣል። የእርሻ የሰርቲፊኬት ባለቤት በየዓመቱ ሰብስበው ማቅረብ ያለባቸውን አመላካቾች ይዘረዝራል። በሌላ መንገድ ካልተጠቀሰ በስተቀር፣ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች ካለፈው ዓመት ጋር ተመሳሳይ የሆነ ውሂብን በየዓመቱ መሰብሰብ አለባቸው። ይህም ማለት፣ ውሂቡ ባለፈው ኦዲት እና አሁን ባለው ኦዲት መካከል ያለውን ጊዜ መሸፈን አለበት ማለት ነው። ለምሳሌ፣ አንድ ኦዲት በጥቅምት 2019 ዓ.ም. ከተካሄደ፣ አግባብነት ያለው የውሂብ መሰብሰቢያ ጊዜ ከጥቅምት 2018 ዓ.ም. እስከ መስከረም 2019 ዓ.ም. ድረስ ይሆናል። ይህ ውሂብ በጥቅምት 2019 ዓ.ም. ኦዲት ወቅት የሚገመገም ይሆናል።

በዓመቱ ውስጥ በተለያዩ ጊዜያት የውስጥ ኢንስፔክሽን በሚካሄድባቸው በቡድን ውስጥ ላሉ እርሻዎች፣ የተሰበሰበው የእርሻ ደረጃ ውሂብ የውስጥ ኢንስፔክሽኑ ከተካሄደበት ወር በፊት ያለውን 12 ወራት የሚያሳይ መሆን አለበት። ለምሳሌ፣ በጥቅምት 2019 ዓ.ም. ለሚካሄድ ኦዲት፣ የቡድን ደረጃ መረጃ ከቀደመው ኦዲት (ጥቅምት 2018 ዓ.ም.) ጀምሮ እስከ ጥቅምት 2019 ዓ.ም. እስከሚቻል ድረስ ያለውን ጊዜ ይሸፍናል። የቡድን አባላት በመጋቢት 2018 ዓ.ም. የውስጥ ኢንስፔክሽን ከተደረገላቸው፣ የሚመለከተው የእርሻ ደረጃ ውሂብ ከሚያዝያ 2017 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 2018 ዓ.ም. መሆን አለበት።

በተጨማሪም፣ አንድ የሰርቲፊኬት ባለቤት ከአንድ በላይ የሆኑ ሰርቲፋይድ ሰብሎች ካሉት፣ ውሂቡ ትኩረት የሚያደርገው ከፍተኛ መጠኖች ባሉት የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ሰብል ላይ ነው።

ይህንን ሰነድ መቼ እና እንዴት መጠቀም ይቻላል?

ይህ ሰነድ ለሰርቲፊኬት ባለቤቶች ከመስፈርት 1.7.1 ጋር በተያያዙ እና በሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርድስ የሚፈለጉ አመልካቾች ላይ መረጃ የሚሰጥ ሲሆን፣ ውሂብን እንዴት በበቂ ሁኔታ እና በትክክለኛ መንገድ መሰብሰብ እንደሚቻልም ያብራራል። የሰርቲፊኬሽን አካል መስፈርቱን ተግባራዊ ለማድረግ ለበለጠ ዝርዝር መረጃ ይህንን ሰነድ ማጣቀስ አለባቸው።

ይዘቱ በቀላሉ ተደራሽ መሆኑን ለማረጋገጥ በአጠቃላይ መልክ የቀረበ ነው። ለበለጠ ዝርዝር መረጃ፣ እባክዎ የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ፦ የውሂብ ነጥቦች እና ሌሎች የተጠቀሱ የመመሪያ ሰነዶች ማጣቀሻዎችን ይመልከቱ። ለቃላት ፍቺ የሬንፎረስት አሊያንስ የቃላት ዝርዝር ፍቺ አባሪ ይመልከቱ።

አመላካች አባሪ 3 ዋና ዋና ክፍሎች አሉት፦  

  • መነሻ አመላካቾች

  • ዘላቂነት ያለው ግብርና አመላካቾች

  • የተሃድሶ ግብርና አመላካቾች

መነሻ አመላካቾች ለሁሉም ስታንዳርዶች ተፈጻሚ ይሆናሉ። ሆኖም ግን፣ ሌሎች የአመላካች ስብስቦች በእያንዳንዱ ስታንዳርድ ስም በተሰየሙት ክፍሎች ስር የሚገኙ ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ ተፈጻሚ ይሆናሉ።

ከእትም 1.0 ወደ እትም 1.2 በተደረገው ማሻሻያ ላይ የተደረጉ ለውጦች

ክፍል

የተደረገው ለውጥ

ይህ ሰነድ ስለ ምንድን ነው

የተስተካከለ፦ የተሻሻለ ጽሑፍ፤ በሰርቲፊኬት ባለቤት የሚሰበሰበው ውሂብ ሊያንጸባርቅ በሚገባው የጊዜ ሰሌዳ ላይ ለውጦች እና ማብራሪያዎች ተደርገዋል።

ይህንን ሰነድ መቼ እና እንዴት መጠቀም ይቻላል

የተስተካከለ፦ ስለ አዲሱ አቀማመጥ የሚያብራራ የተሻሻለ ጽሑፍ ተጨምሯል።

የአመላካች ውሂብ ነጥቦች ተፈጻሚነት

የተስተካከለ፦ በጽሑፉ ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

የጊዜ ሰሌዳ ተፈጻሚነት መግለጫ

የተስተካከለ፦ የአመላካች አሰባሰብ የጊዜ ገደብ ላይ ማብራሪያ ተደርጓል።

መነሻ አመላካቾች

አዲስ፦ ሬንፎረስት አሊያንስ የተለያዩ የአመላካች ዓይነቶችን በመመደብ፣ መነሻ አመላካቾች በሁሉም ስታንዳርዶች ላይ ተፈጻሚ እንዲሆኑ አድርጓል። ልብ ይበሉ፣ መነሻ አመላካቾች አዲስ አይደሉም፤ አሁን የተለየ ምደባ ተሰጥቷቸዋል።

ዘላቂነት ያለው ግብርና ስታንዳርድ

የተስተካከለ፦ በተወሰኑ ስታንዳርዶች ስር ያሉ የአመላካቾች አቀማመጥ ተስተካክሏል።

የተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ አመላካቾች

አዲስ፦ የተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ አመላካቾች ተጨምረዋል።  

የተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ አመላካቾች

ሁለቱንም የዘላቂነት ያለው ግብርና እና የተሃድሶ ግብርና ስታንዳርዶችን፣ ለሚከተሉ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች፣ በተሃድሶ ግብርና አመላካቾች ስር ማስታወሻ ተጨምሯል። ይህ ማስታወሻ እያንዳንዱ የተወሰነ አመላካች ለሁለቱም ስታንዳርዶች አንድ ጊዜ ሪፖርት መደረግ እንዳለበት እንጂ ለየብቻ መቅረብ እንደሌለበት ያብራራል።

የአመላካች ውሂብ ነጥቦች ተፈጻሚነት

የአንድ የውሂብ ነጥብ ተፈጻሚነት በምልክት ማድረጊያ ይገለጻል። ምልክት ማድረጊያው በአጠቃላይ ውሂቡ ከየትኛው ተዋናይ ወይም ደረጃ እንደሚሰበሰብ ያሳያል።

ለቡድኖች፣ ምልክት ማድረጊያው ይኑርም አይኑር፣ በሬንፎረስት አሊያንስ (RA) ፕላትፎርም ላይ ውሂብን የመሰብሰብ እና ሪፖርት የማድረግ የመጨረሻው ኃላፊነት ሁልጊዜም የቡድን አመራር መሆኑን ልብ ይበሉ። ለቡድኖች፣ አመላካቾቹ በየዓመቱ በውስጥ ኢንስፔክሽኖች/በራስ-ግምገማ ወቅት ሪፖርት ይደረጋሉ። በተጨማሪም ለቡድኖች፣ የቡድን አመራር ከውስጥ ኢንስፔክሽን ናሙና ጋር የሚጣጣም የውሂብ አሰባሰብ ናሙና ላላቸው እርሻዎች ውሂብ ሪፖርት ማድረግ ይኖርበታል።

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በግል ሰርቲፊኬሽን ውስጥ ለሚገኙ ትናንሽ እና ትልልቅ እርሻዎች የሚሆን ምልክት ማድረጊያ

በግል ሰርቲፋይድ የሆኑ ትናንሽ ወይም ትልልቅ እርሻዎች እነዚህን የውሂብ ነጥቦች መሰብሰብ አለባቸው።

የቡድን ሥራ አመራር ምልክት ማድረጊያ

የውሂብ ነጥቡ ለመላው ቡድኑ ተፈጻሚ የሚሆን ሲሆን፤ የቡድን አመራር ሠራተኞች ለሁሉም የቡድኑ አባላት (አነስተኛም ሆኑ ትላልቅ) እና ለራሳቸው የሥራ ክንውን የውሂብ ነጥቦችን የመሰብሰብ ኃላፊነት አለባቸው።

የቡድኑ አካል ለሆኑ ትላልቅ እርሻዎች ምልክት ማድረጊያ

የትልቁ እርሻ አመራር ለእርሻቸው የሚሆኑ የውሂብ ነጥቦችን የመሰብሰብ ኃላፊነት አለባቸው። የቡድን አመራር ይህንን ለማድረግ እርሻውን መደገፍ ያለባቸው ሲሆን ውሂቡን የማቅረብ የመጨረሻው ኃላፊነትም የእነሱ ነው።

የቡድኑ አካል ለሆኑ አነስተኛ እርሻዎች ምልክት ማድረጊያ

የውሂብ ነጥቡ ለአነስተኛ እርሻዎች ተፈጻሚ የሚሆን ቢሆንም በቡድን አመራር መሰብሰብ አለበት።

የቡድኑ አካል ለሆኑ ትላልቅ እርሻዎች እና ለቡድን አመራር ምልክት ማድረጊያ

የትላልቅ እርሻ አመራሮች ለእርሻዎቻቸው የውሂብ ነጥቦችን መሰብሰብ ያለባቸው ሲሆን፣ የቡድን አመራር ደግሞ በቡድኑ ውስጥ ላሉ አነስተኛ እርሻዎች (አግባብነት ካለው) የውሂብ ነጥቦችን ያስተዳድራል እንዲሁም በቡድኑ ውስጥ ያሉ ትላልቅ እርሻዎችን ይደግፋል።

የቡድኑ አካል ለሆኑ አነስተኛ እና ትላልቅ እርሻዎች ምልክት ማድረጊያ

የውሂብ ነጥቡ በቡድን ውስጥ ላሉ አነስተኛ እና ትላልቅ እርሻዎች ተፈጻሚ ይሆናል፤ ነገር ግን ለአነስተኛ እርሻዎች በቡድን አመራር መሰብሰብ ይኖርበታል።

የአነስተኛ፣ የትላልቅ እርሻዎች እና የቡድን አመራር ምልክት ማድረጊያ

የውሂብ ነጥቦቹ በቡድን ውስጥ ላሉ አነስተኛ እርሻዎች፣ ትላልቅ እርሻዎች እና ለቡድን አመራር ተፈጻሚ ይሆናሉ።

አመላካቾች

መነሻ አመላካቾች

ያለፈው ዓመት የተገመተ የሰርቲፋይድ ምርት መጠን በኪሎግራም

መግለጫ፦

የሰርቲፋይድ ሰብል አጠቃላይ የተገመተ መጠን። ይህ ካለፈው ዓመት የተወሰደ ግምት ነው።  

ያለፉትን የተገመቱ የሰርቲፋይድ ምርት መጠኖችን መከታተል አምራቾች እና የቡድን አመራር እርሻዎቻቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲያስተዳድሩ ይረዳል፣ ትክክለኛ የግብርና አሰራሮች እንዲተገበሩ ያበረታታል፣ እንዲሁም ለአቅርቦት ሰንሰለቱ ግልጽነትን ያመጣል። ለወቅታዊው ዓመት የምርት ግምቶች አዝማሚያዎችን ለመረዳት ጠቃሚ ነው። ግምቶቹ ከእውነተኛው የምርት ስብሰባ ወቅት ምርት ጋር ይነጻጸራሉ። ይህም የሬንፎረስት አሊያንስ የሰርቲፊኬሽን ፕሮግራም እና የትረሰብሊቲ ሥርዓትን ተዓማኒነት ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ ያደርጋል።  

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል

  • አጠቃላይ የተገመተ የሰርቲፋይድ ምርት መጠን በኪሎግራም።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

እባክዎን ልዩ ልዩ ሰብሎችን እና የምርት ሁኔታዎችን የሚሸፍነውን የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ G፦ የምርት ግምትን ይመልከቱ። ይበልጥ ትክክለኛ የሆኑ የምርት ግምቶችን ለማግኘት የሚያስችሉ መሰረታዊ መርሆች ተብራርተዋል።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ያለፈው ዓመት የተገመተ የሰርቲፋይድ ምርት መጠን በግንድ፦ ለአበቦች ብቻ ተፈጻሚ የሚሆን

መግለጫ፦

የሰርቲፋይድ ሰብል አጠቃላይ የተገመተ መጠን። ይህ ካለፈው ዓመት የተወሰደ ግምት ነው።

ያለፉትን የተገመቱ የሰርቲፋይድ ምርት መጠኖችን መከታተል አምራቾች እና የቡድን አመራር እርሻዎቻቸውን በተሻለ ሁኔታ እንዲያስተዳድሩ ይረዳል፣ ትክክለኛ የግብርና አሰራሮች እንዲተገበሩ ያበረታታል፣ እንዲሁም ለአቅርቦት ሰንሰለቱ ግልጽነትን ያመጣል። ለወቅታዊው ዓመት የምርት ግምቶች አዝማሚያዎችን ለመረዳት ጠቃሚ ነው። ግምቶቹ ከእውነተኛው የምርት ስብሰባ ወቅት ምርት ጋር ይነጻጸራሉ። ይህም የሬንፎረስት አሊያንስ የሰርቲፊኬሽን ፕሮግራም እና የትረሰብሊቲ ሥርዓትን ተዓማኒነት ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • አጠቃላይ የተገመተ የሰርቲፋይድ ምርት መጠን በግንድ።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

እባክዎን ልዩ ልዩ ሰብሎችን እና የምርት ሁኔታዎችን የሚሸፍነውን የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ G፦ የምርት ግምትን ይመልከቱ። ይበልጥ ትክክለኛ የሆኑ የምርት ግምቶችን ለማግኘት የሚያስችሉ መሰረታዊ መርሆች ተብራርተዋል።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

የእርሻ መጠን በሄክታር (ha)

መግለጫ፦

የሰርቲፋይድ እርሻዎች አጠቃላይ ስፋት። ዓላማው ለሰርቲፊኬት ባለቤት (CH)/ለእያንዳንዱ የቡድን አባል የሰርቲፊኬሽን ወሰንን ለማረጋገጥ ከሚያስፈልገው መረጃ እንደ አንዱ አካል አድርጎ የሰርቲፋይድ አጠቃላይ ስፋትን ወቅታዊ መዝገብ መያዝ ነው። ለቡድኖች፣ ይህንን መረጃ ለመሰብሰብ በሬንፎረስት አሊያንስ የቀረበውን የቡድን አባላት መዝገብ (GMR) ቅጽ መጠቀም ይችላሉ።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • ባለቤትነትን/የመሬት ይዞታን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ለምሳሌ የባለቤትነት ማረጋገጫ (deeds)፣ የኪራይ ውል ስምምነቶች፣ እና የይዞታ ማረጋገጫ ሰርቲፊኬቶችን ከንብረቱ ካርታዎች ጋር አብሮ በመጠቀም፣ አምራቹ በሰርቲፊኬሽን ወሰን ውስጥ የሚካተተውን አጠቃላይ ስፋት በሬንፎረስት አሊያንስ በተዘጋጁት ቅጾች (ለምሳሌ በቡድን አባላት መዝገብ (GMR)፣ በሬንፎረስት አሊያንስ ፕላትፎርም) ላይ መመዝገብ አለበት።  

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

የምርት ቦታ ስፋት በሄክታር (ha)

መግለጫ፦

የሰርቲፋይድ ሰብሎች የምርት ቦታ ስፋት። ለሰርቲፊኬት ባለቤት/ለእያንዳንዱ የቡድን አባል የሰርቲፊኬሽን ወሰንን ለማረጋገጥ ከሚያስፈልገው መረጃ እንደ አንዱ አካል አድርጎ የሰርቲፋይድ ሰብል ስፋትን ወቅታዊ መዝገብ ይያዙ

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • በዓመቱ መጀመሪያ ላይ፣ ዓመታዊውን የአመራር ዕቅድ በሚታደስበት ወቅት።

  • ከውስጥ ኢንስፔክሽን በፊት ማናቸውንም ለውጦች ያረጋግጡ እና ያዘምኑ።

  • የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነዶች፣ የኪራይ ውል ስምምነቶች፣ እና የይዞታ ማረጋገጫ ሰርቲፊኬቶችን ከመሬቱ ካርታዎች ጋር በማጣመር የባለቤትነትን ወይም የመሬት ይዞታን የሚያረጋግጡ ሰነዶችን ይጠቀሙ። አምራቹ በሰርቲፊኬሽን ወሰን ውስጥ የሚካተተውን አጠቃላይ ስፋት በሬንፎረስት አሊያንስ በተዘጋጁት ቅጾች (የቡድን አባላት መዝገብ (GMR)፣ ፕላትፎርም) ላይ መመዝገብ አለበት።  

  • በሰነዶች መካከል የሚታዩ ማናቸውም አለመጣጣሞች ተለይተው መመዝገብ አለባቸው፤ ይህም በሬንፎረስት አሊያንስ ወይም በየሰርቲፊኬሽን አካል (CB) በሚደረግ ማጣራት እና ማረጋገጥ ወቅት በሬንፎረስት አሊያንስ ቅጾች ላይ የተመዘገበው ውሂብ በማስረጃ እንዲረጋገጥ ያስችላል።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በሥርዓተ ጾታ የተለዩ ሪፖርት የተደረጉ የክስተቶች ብዛት፦ ለሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ ለግዳጅ ሥራ፣ በሥርዓተ ጾታ ላይ ለተመሰረተ አድልዎ፣ ለሌሎች አድሎዎች፣ በሥራ ቦታ የሚፈጸም ጥቃት እና ትንኮሳ

መግለጫ፦

በቅሬታ አፈታት ሥርዓት ኮሚቴ አማካኝነት በሥርዓተ ጾታ ተለይተው ሪፖርት የተደረጉ አጠቃላይ የክስተቶች ብዛት ሲሆን፤ እነዚህም በሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ በግዳጅ ሥራ፣ በሥርዓተ ጾታ ላይ በተመሰረተ አድልዎ፣ በሌሎች አድሎዎች እና በስራ ቦታ የሚፈጸም ጥቃት እና ትንኮሳ ተለይተው በዓይነት የቀረቡ ናቸው።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • በሬንፎረስት አሊያንስ ፕላትፎርም ላይ ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦

  • የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ E፦ የቅሬታ አፈታት ሥርዓት።

  • የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ R፦ መገምገም እና መፍትሄ መስጠት የክትትል መመሪያ መሣሪያ።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በሥርዓተ ጾታ ተለይተው የተረጋገጡ የክስተቶች ብዛት፦ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ የግዳጅ ሥራ፣ በሥርዓተ ጾታ ላይ የተመሰረተ አድልዎ፣ ሌሎች አድሎዎች፣ በስራ ቦታ የሚፈጸም ጥቃት እና ትንኮሳ።  

መግለጫ፦

በቅሬታ አፈታት ሥርዓት ኮሚቴ አማካኝነት የተረጋገጡ እና በሥርዓተ ጾታ ተለይተው የቀረቡ አጠቃላይ የክስተቶች ብዛት ሲሆን፤ እነዚህም በሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ በግዳጅ ሥራ፣ በሥርዓተ ጾታ ላይ በተመሰረተ አድልዎ፣ በሌሎች አድሎዎች እና በስራ ቦታ የሚፈጸም ጥቃት እና ትንኮሳ ተለይተው በዓይነት የቀረቡ ናቸው።

ውሂብ መሰብሰብ፦  

  • በሬንፎረስት አሊያንስ ፕላትፎርም ላይ ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦  

  • የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ E፦ የቅሬታ አፈታት ሥርዓት።

  • ለቴምፕሌት እና ለመሣሪያ የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ R፦ መገምገም እና መፍትሄ መስጠት የክትትል መመሪያ መሣሪያ።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በሥርዓተ ጾታ ተለይተው መፍትሄ ያገኙ የክስተቶች ብዛት፦ ለሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ ለግዳጅ ሥራ፣ በሥርዓተ ጾታ ላይ ለተመሰረተ አድልዎ፣ ለሌሎች አድሎዎች፣ በስራ ቦታ የሚፈጸም ጥቃት እና ትንኮሳ

መግለጫ፦

በሥርዓተ ጾታ ተለይተው መፍትሄ ያገኙ አጠቃላይ የክስተቶች ብዛት ሲሆን፤ እነዚህም በሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ በግዳጅ ሥራ፣ በሥርዓተ ጾታ ላይ በተመሰረተ አድልዎ፣ በሌሎች አድሎዎች እና በስራ ቦታ የሚፈጸም ጥቃት እና ትንኮሳ ተለይተው በዓይነት የቀረቡ ናቸው።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • በሬንፎረስት አሊያንስ (RA) ፕላትፎርም ላይ ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፦

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

የዘላቂነት ያለው ግብርና ስታንዳርድ አመላካቾች

ዘላቂነት ያለው ግብርና ከምንጊዜውም በላይ አሁን እጅግ አስፈላጊ ሆኗል። የሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው ግብርና ስታንዳርድ አምራቾች የተሻሉ ሰብሎችን እንዲያመርቱ፣ ምርታማነትን እንዲያሳድጉ፣ ስለ ዘላቂነት ያለው አፈጻጸማቸው ጠቃሚ መረጃዎችን እንዲያገኙ እና ኢንቨስትመንታቸውን በትልልቅ ስጋቶች ላይ እንዲያተኩሩ የሚረዳ ተግባራዊ ማዕቀፍ እና የታለሙ ፈጠራዎችን ያቀርባል። የዘላቂነት ያለው ግብርና ስታንዳርድ አመላካቾች የተነደፉት የሰርቲፊኬት ባለቤቶች የዘላቂነት እድገትን እንዲከታተሉ እና በማደግ ላይ ያሉ ገበያዎችን እንዲያገኙ ለማገዝ ሲሆን፣ በተመሳሳይ ጊዜ ንግዶች በማህበራዊ እና አካባቢያዊ ተፅዕኖ ሪፖርት አቀራረብ ላይ ለሚገጥሟቸው እየጨመሩ የመጡ ግፊቶች ምላሽ የሚሰጡበትን መንገድ ያቀርባሉ።

በአንድ እርሻ ውስጥ ያሉ የጥላ ዛፎች ዝርያዎች ብዛት

መግለጫ፦

በእርሻው ውስጥ የሚገኙ አጠቃላይ የጥላ ዛፎች ዝርያዎች ብዛት።

ይህ በአንድ እርሻ ውስጥ ያለውን የጥላ ዛፍ ዝርያዎች ብዝኃነት ለመጨመር ያለመ ሲሆን፤ ዓላማውም የአፈርን ጥራት ለማሻሻል፣ ብዝኃ ሕይወትን ለመጠበቅ፣ የውሃ አካላት ጥበቃን ለማሳደግ እና የካርቦን ክምችትን በመጨመር ለአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • በሬንፎረስት አሊያንስ (RA) ሰርቲፋይድ በሆነው የሰብል ቦታ ላይ እንደ ጥላ ዛፎች የሚያገለግሉ የዛፍ ዝርያዎችን ብዛት መቁጠር።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በአንድ ሄክታር ውስጥ ያሉ የጥላ ዛፎች ብዛት

መግለጫ፦

ሬንፎረስት አሊያንስ (RA) ሰርቲፋይድ በሆነው የሰብል ቦታ ላይ በአንድ ሄክታር ውስጥ የሚገኙ አጠቃላይ የጥላ ዛፎች ብዛት። ይህ አመላካች የአፈርን ጥራት ለማሻሻል፣ ብዝኃ ሕይወትን ለመጠበቅ፣ የውሃ አካላት ጥበቃን ለማሳደግ እና የካርቦን ክምችትን በመጨመር ለአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ አስተዋጽኦ ለማድረግ በአንድ እርሻ ውስጥ ያለውን የጥላ ዛፎች ብዛት መጨመር ላይ ትኩረት ያደርጋል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • በአንድ ሄክታር ውስጥ የሚገኙ የጥላ ዛፎችን ብዛት መቁጠር።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

የኦርጋኒክ ማዳበሪያ ሊትር / ኪሎግራም

መግለጫ፦

ይህ አመላካች ባለፈው ዓመት ውስጥ በእርሻው ላይ ለሰርቲፋይድ ሰብል ጥቅም ላይ የዋለውን ዓመታዊ የኦርጋኒክ ማዳበሪያ መጠን ይከታተላል። ዓላማውም ይህንን ውሂብ በመጠቀም በሚቀጥለው ዓመት የማዳበሪያ አጠቃቀምን ውጤታማነት ለማሻሻል የሚያስችሉ እርምጃዎችን ለመለየት እና ተግባራዊ ለማድረግ ነው። ለዚህ የውሂብ ነጥብ፣ ሬንፎረስት አሊያንስ (RA) በቃላት ዝርዝር ፍቺው መሠረት ኦርጋኒክ ማዳበሪያን ገልጿል። ይህም ለንግድ የቀረቡ ማዳበሪያዎችን ብቻ የሚመለከት ሲሆን ፍግን (manure) አያካትትም።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • በኪሎግራም (kg) እና/ወይም በሊትር (L) የተገለጸ የቁጥር እሴት ሆኖ ይሰበሰባል።

  • በእርሻው ላይ ለሬንፎረስት አሊያንስ (RA) ሰርቲፋይድ ዋና ሰብል ጥቅም ላይ የዋለ አጠቃላይ የኦርጋኒክ ማዳበሪያ መጠን።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ኦርጋኒክ ያልሆነ ማዳበሪያ ሊትር / ኪሎግራም

መግለጫ፦

ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በእርሻው ላይ ለሰርቲፋይድ ሰብል ጥቅም ላይ የዋለውን ዓመታዊ የኦርጋኒክ ያልሆነ ማዳበሪያ መጠን ለመከታተል ነው። ይህ ውሂብ በሚቀጥለው ዓመት የማዳበሪያ አጠቃቀምን ውጤታማነት ለማሻሻል የሚያስችሉ ዕድሎችን አስቀድሞ ለመለየት እና ተግባራዊ ለማድረግ ጥቅም ላይ ይውላል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • በሬንፎረስት አሊያንስ (RA) ሰርቲፋይድ ዋና ሰብል ላይ ጥቅም ላይ የዋለ አጠቃላይ የኦርጋኒክ ያልሆነ ማዳበሪያ መጠን።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በተባይ ማጥፊያ፣ ሮዴንቲሳይድ፣ በፀረ-ፈንገስ፣ በፀረ-አረም እና በሌሎች የተከፋፈሉ ፀረ-ተባዮች ሊትር / ኪሎግራም

መግለጫ፦

ባለፈው ዓመት ውስጥ በእርሻው ላይ ጥቅም ላይ የዋለ አጠቃላይ የፀረ-ተባዮች መጠን።
ዓላማውም ዓመታዊ የፀረ-ተባይ አጠቃቀምን በትክክል በመከታተል ዘላቂ የሆነ የተባይ መከላከያ ዘዴዎችን ማረጋገጥ፣ ኃላፊነት የተሞላበት አጠቃቀምን ማበረታታት፣ የአካባቢ ተፅዕኖን መቀነስ፣ እንዲሁም ከፍተኛ መርዛማነት ያላቸውን እና የታገዱ ምርቶች አጠቃቀምን መቀነስ ነው።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • በሊትር እና/ወይም በኪሎግራም የተገለጸ የቁጥር እሴት ሆኖ ይሰበሰባል።

  • የሰርቲፊኬት ባለቤቱ (CH) የፀረ-ተባይ አጠቃቀም እና የርጭት መዝገቦችን በመጠቀም፣ ባለፈው ዓመት ለሰርቲፋይድ ሰብል ጥቅም ላይ የዋለውን አጠቃላይ የፀረ-ተባይ መጠን መረጃ ይሰበስባል። ውሂቡ በተባይ ማጥፊያ፣ በሮዴንቲሳይድ፣ በፀረ-ፈንገስ፣ በፀረ-አረም እና በሌሎች ምድብ ይከፈላል።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ለመስኖ አገልግሎት የዋለ የውሃ መጠን (በሊትር)

መግለጫ፦

ለመስኖ አገልግሎት የዋለ አጠቃላይ የውሃ መጠን።

ዓላማው ከ1ኛው ዓመት ጀምሮ የመስኖ ውሃ አጠቃቀምን በመከታተል ውጤታማ የውሃ አጠቃቀምን ማበረታታት ሲሆን፤ ይህም አምራቾች የውሃ ፍጆታቸውን እንዲቆጣጠሩ፣ የውሃ ሀብቶችን በአግባቡ እንዲጠቀሙ እና ዘላቂ የግብርና አሰራሮችን እንዲደግፉ ያስችላቸዋል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

ማሳሰቢያ፦ ይህ የውሂብ ነጥብ ተግባራዊ የሚሆነው በእርሻው ላይ የመስኖ አጠቃቀም መኖሩ ሪፖርት ሲደረግ ብቻ ነው።

  • ለመስኖ አገልግሎት የዋለውን አጠቃላይ የውሃ መጠን በሊትር የሚገልጽ የቁጥር እሴት።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ለሰብል ማቀነባበሪያ የሚውል የውሃ መጠን (በሊትር)

መግለጫ፦

ባለፈው ዓመት ውስጥ ሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ የሆነን ሰብል ለማቀነባበር ጥቅም ላይ የዋለ አጠቃላይ የውሃ መጠን። ዓላማው ለማቀነባበሪያ የሚውል የውሃ አጠቃቀምን በመከታተል ውጤታማ የውሃ አያያዝን ማበረታታት ሲሆን፤ ይህም አምራቾች የውሃ ፍጆታቸውን እንዲቆጣጠሩ፣ የውሃ ሀብቶችን በአግባቡ እንዲጠቀሙ እና ዘላቂነት ያላቸው የግብርና አሠራሮችን እንዲደግፉ ያስችላቸዋል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

ማሳሰቢያ፦ ለቡድን አመራር፣ ይህ ተፈጻሚ የሚሆነው ቡድኖቹ ማዕከላዊ የዝግጅት ተቋማት ካሏቸው ብቻ ነው።

  • ለሰብል ማቀነባበሪያ በሊትር የዋለውን አጠቃላይ የውሃ መጠን የሚገልጽ የቁጥር እሴት።

  • በማቀነባበሪያው ቦታ ላይ በተገጠመ የውሃ ቆጣሪ ንባብ መሠረት (በማቀነባበሪያው ድግግሞሽ መሠረት) የውሃ ፍጆታ እሴቶችን መመዝገብ። የመለኪያ አሃዱን ያረጋግጡ፣ እና አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ውሂቡን (በሊትር) ለማግኘት አስፈላጊ የሆኑ የለውጥ ተመኖችን ይጠቀሙ።

  • በሰብል ማቀነባበሪያው ቦታ ላይ የቆጣሪ ሥርዓት ከሌለ፣ ለማቀነባበሪያ ተግባራት የተሰበሰበውን የውሃ መጠን ይለኩ።  

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ለሰብል ማቀነባበሪያ የሚውል እንጨት

መግለጫ፦

ባለፈው ዓመት ውስጥ ሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ የሆነን ሰብል ለማቀነባበር የዋለ አጠቃላይ የእንጨት መጠን። ዓላማው የእንጨት አጠቃቀምን በመከታተል ውጤታማ የእንጨት አያያዝን ማበረታታት ሲሆን፤ ይህም አምራቾች የፍጆታ መጠናቸውን እንዲቆጣጠሩ ያስችላቸዋል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

ማሳሰቢያ፦ ለቡድን አመራር፣ ይህ ተፈጻሚ የሚሆነው ቡድኖቹ ማዕከላዊ የዝግጅት ተቋማት ካሏቸው ብቻ ነው።

  • ለማቀነባበሪያ የዋለውን አጠቃላይ የእንጨት መጠን በኪሎግራም የሚገልጽ የቁጥር እሴት።

  • ለማቀነባበሪያ ተግባራት በተገዛው/ጥቅም ላይ በዋለው መጠን መሠረት የእንጨት ፍጆታን መመዝገብ።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በተፈጥሮ እፅዋት የተሸፈነ የእርሻ ቦታ ስፋት መቶኛ

መግለጫ፦

በተፈጥሮ እፅዋት ተሸፍኖ የሚቆይ አጠቃላይ የእርሻ ቦታ ስፋት።

ዓላማው የተፈጥሮ እፅዋት ሽፋንን በየጊዜው መጠበቅ እና መከታተል ሲሆን፣ እድገቱንም ለመከታተል ዓመታዊ ሪፖርት ማቅረብ ነው። የተፈጥሮ እፅዋት ሽፋኑ ከአጠቃላይ ቦታው በ10% በታች፣ ወይም ጥላ ለሚቋቋሙ ሰብሎች በ15% በታች ከሆነ፣ የማሻሻያ ግቦችን ማውጣት እና እነዚህን ደረጃዎች በጊዜ ሂደት ለማሳካት እና ለማስቀጠል የሚያስችሉ እርምጃዎችን መተግበር ያስፈልጋል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • አምራቹ በተፈጥሮ እፅዋት የተሸፈነውን ቦታ (የጂኦሎኬሽን ውሂብ ወይም ፖሊጎኖችን ወይም ሌላ የታወቀ ዘዴን በመጠቀም) መለካት እና ይህንን መረጃ በውሂብ ነጥብ ቅጽ ላይ ሪፖርት ማድረግ አለበት።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው

የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ M፦ ተፈጥሯዊ ስነ-ምህዳሮች እና እፅዋት፤ ለጥበቃ በተለዩ መሬቶች እና በምርት ቦታዎች (ለምሳሌ በጥምር አርሻ ጥላ ስር ያለ ሽፋን) ውስጥ የተፈጥሮ እፅዋትን እንዴት መለካት እንደሚቻል መመሪያ ይሰጣል።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ዓመታዊ ጠቅላላ የቅሪተ አካል ነዳጅ አጠቃቀም

መግለጫ፦

ሰርቲፋይድ የሆኑ ምርቶችን ለማምረት እና ለማቀነባበር ጥቅም ላይ የዋለውን ጠቅላላ የቅሪተ አካል ነዳጅ መጠን ይለካል። ይህም እንደ ናፍጣ፣ ቤንዚን፣ ፈሳሽ የፔትሮሊየም ጋዝ (LPG) (ፕሮፔን)፣ የድንጋይ ከሰል፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ እንዲሁም ዘይትን የመሳሰሉ የነዳጅ ምንጮችን ያጠቃልላል። በነዳጅ መጠን (በሊትር፣ በኩቢክ ሜትር) ወይም በክብደት (በኪሎግራም) ሪፖርት የሚደረግ ሲሆን፣ ይህም ለቋሚ ፍጆታ (እንደ ቦይለር፣ ሜካኒካል ማድረቂያዎች) ወይም ለተንቀሳቃሽ ፍጆታ (እንደ ትራክተሮች) ሊሆን ይችላል። የባዮ-ነዳጅ (biofuels) አጠቃቀም በዚህ ውስጥ መካተት የለበትም። ዓላማው ውጤታማነትን ለማሻሻል ወይም አጠቃቀምን ለመቀነስ የሚያስችሉ መንገዶችን ለመፈለግ እንዲቻል የተለመደውን የእርሻ ነዳጅ አጠቃቀም መገምገም ነው።

ውሂብ መሰብሰብ፦

ማሳሰቢያ፦ ይህ በቡድን አመራር ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው ቡድኖች ለዝግጅት/ለማቀነባበሪያ የቅሪተ አካል ነዳጅ የሚጠቀሙ ከሆነ ብቻ ነው

  • ለማቀነባበር እና ለማምረት የዋለ የቅሪተ አካል ነዳጅ አጠቃቀም።

  • የቁጥር እሴት ከመለኪያ አሃዱ ጋር፦ በሊትር፣ በኪሎግራም፣ እና በኩቢክ ሜትር።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው

የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ N፦ የኃይል ቆጣቢነት፤ በሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው ግብርና ስታንዳርድ የእርሻ መስፈርቶች መሠረት ይህንን መረጃ ለመመዝገብ እንዲረዳ ለሰርቲፊኬት ባለቤቶች መመሪያዎችን ይሰጣል።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ዓመታዊ ጠቅላላ የኤሌክትሪክ አጠቃቀም (በኪሎዋት በሰዓት)

መግለጫ፦

ጠቅላላ የኤሌክትሪክ አጠቃቀም ውሂብ የሚያመለክተው ሰርቲፋይድ የሆኑ ምርቶችን ለማምረት እና ለማቀነባበር (ለምሳሌ ለማቀነባበሪያ ማሽኖች) የዋለ የኤሌክትሪክ መጠንን ነው። ይህም በእርሻ ላይ የሚገኙ የታዳሽ ኃይል ምንጮችን (የፀሐይ፣ የንፋስ፣ የውሃ ኃይል) እና የሕዝብ የኤሌክትሪክ መስመርን ያጠቃልላል፤ መጠኑም ጥቅም ላይ በዋለው የኤሌክትሪክ መጠን ኪሎዋት በሰዓት (kWh) ሪፖርት ይደረጋል።  ዓላማው ውጤታማነትን ለማሻሻል ወይም ፍጆታን ለመቀነስ የሚያስችሉ መንገዶችን ለመፈለግ እንዲቻል የተለመደውን የእርሻ የኤሌክትሪክ አጠቃቀም መገምገም ነው።  

ውሂብ መሰብሰብ፦

ማሳሰቢያ፦ ይህ በቡድን አመራር ላይ ተፈጻሚ የሚሆነው፣ ቡድኖች ለማቀነባበር ሥራዎች ኃይልን የሚጠቀሙ ከሆነ ብቻ ነው

  • በኪሎዋት በሰዓት (kWh) የሚገለጽ የቁጥር እሴት

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው

የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ N፦ የኃይል ቆጣቢነት፤ በሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው ግብርና ስታንዳርድ የእርሻ መስፈርቶች መሠረት ይህንን መረጃ ለመመዝገብ እንዲረዳ ለሰርቲፊኬት ባለቤቶች መመሪያዎችን ይሰጣል።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

የታዳሽ ኃይል ምንጭ ዓይነቶች፦ የፀሐይ፣ የንፋስ፣ የውሃ፣ ባዮ-ነዳጅ ኃይል

መግለጫ፦

የታዳሽ ኃይል አጠቃቀም (አዎ ወይም አይደለም) እና ጥቅም ላይ የዋሉ ዓይነቶች (የፀሐይ፣ የንፋስ፣ የውሃ፣ ወይም ባዮ-ነዳጅ ኃይል)። ዓላማው የግሪን ሃውስ ጋዝ (GHG) ልቀትን እና የአየር ብክለትን ለመቀነስ የታዳሽ ኃይል ምንጮችን የመጠቀም ዕድሎችን መለየት ወይም ሪፖርት ማድረግ ሲሆን፤ ይህም ለአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ እና ለአካባቢው ማህበረሰቦች ደህንነት አስተዋፅኦ ያደርጋል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እርሻው(ዎቹ) ማንኛውንም የታዳሽ ኃይል ምንጮችን የሚጠቀሙ መሆኑን መለየት እና እነሱን መመዝገብ።  

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

የተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ (RAS) አመልካቾች

ተሃድሶ ግብርና የአፈርን ጤና ለማሻሻል፣ ብዝኃ ሕይወትን ለመጨመር እና ምርታማነትን ለማሳደግ ከተፈጥሮ ጋር አብሮ የሚሰራ የእርሻ ዘዴ ሲሆን፣ የረጅም ጊዜ ዘላቂነት ያለው መሆኑን ያረጋግጣል። አምራቾች የአየር ንብረት ለውጥን እና ኢኮኖሚያዊ ፈተናዎችን በተሻለ ሁኔታ ለመቋቋም የሚያስችሉ ይበልጥ ጠንካራ እርሻዎችን እንዲገነቡ ይረዳል።

በተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ (RAS) በኩል የተሰበሰበው ውሂብ ዕቅዶችን ማዘጋጀት፣ የእርሻ ቦታዎችን ዲዛይን ማሻሻል እና የአቅርቦት ሰንሰለት ተሳትፎን ለማሳወቅ የሚያገለግል ሲሆን፤ በአካባቢ ጤና፣ በእርሻ አመራር እና በገበሬዎች መተዳደሪያ ላይ ቀጣይነት ያለው ማሻሻያ የሚያስፈልጋቸውን ቦታዎች ለይቶ ያሳያል።

በተሃድሶ ግብርና ሰርቲፊኬሽን በኩል የሚጠበቁ ዋና ዋና ውጤቶች፦

  • የአፈር ጤና፦ የተሻሻለ ኦርጋኒክ ይዘት፣ የአፈር መዋቅር እና ለምነት፣ እንዲሁም ሊገኝ የሚችል የምርት ዕድገት።

  • የግብዓት አጠቃቀም ውጤታማነት፦ የውጭ ግብዓቶች አጠቃቀም መቀነስ እና የተሻለ የንጥረ ነገር ዑደት፣ ይህም ወጪን ለመቆጠብ ይረዳል።

  • የአየር ንብረትን የመቋቋም አቅም፦ የአየር ንብረት መለዋወጥን፣ ተባዮችን እና በሽታዎችን የመቋቋም ጠንካራ ብቃት።

  • የገበያ ዕድሎች፦ ልዩ የገበያ አማራጮችን ማግኘት እና በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ እውቅናን ማግኘት።

  • የአርሶ አደሮች ደህንነት እና ትስስር፦ የተሻሻለ መተዳደሪያ እና ከሌሎች አምራቾች ጋር የሚኖር ጠንካራ ግንኙነት።

በእያንዳንዱ እርሻ ውስጥ የሚገኙ የጥላ ዛፎች ዝርያዎች ብዛት

መግለጫ፦

በእርሻው ውስጥ የሚገኙ አጠቃላይ የጥላ ዛፎች ዝርያዎች ብዛት።

ይህ በአንድ እርሻ ውስጥ ያለውን የጥላ ዛፍ ዝርያዎች ብዝኃነት ለመጨመር ያለመ ሲሆን፤ ዓላማውም የአፈርን ጥራት ለማሻሻል፣ ብዝኃ ሕይወትን ለመጠበቅ፣ የውሃ አካላት ጥበቃን ለማሳደግ እና የካርቦን ክምችትን በመጨመር ለአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ አስተዋጽኦ ለማድረግ ነው።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • በሬንፎረስት አሊያንስ (RA) ሰርቲፋይድ በሆነው የሰብል ቦታ ውስጥ በጥላነት የሚያገለግሉ የዛፍ ዝርያዎችን ብዛት መቁጠር።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

*የሰርቲፊኬት ባለቤት በዘላቂ ግብርና ስታንዳርድ መሠረት ሰርቲፋይድ ከሆነ፣ ይህ አመልካች ሪፖርት የሚደረገው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በአንድ ሄክታር ውስጥ ያሉ የጥላ ዛፎች ብዛት

መግለጫ፦

ሬንፎረስት አሊያንስ (RA) ሰርቲፋይድ በሆነው የሰብል ቦታ ላይ በአንድ ሄክታር ውስጥ የሚገኙ አጠቃላይ የጥላ ዛፎች ብዛት። ይህ የአፈርን ጥራት ለማሻሻል፣ ብዝኃ ሕይወትን ለመጠበቅ፣ የውሃ አካላት ጥበቃን ለማጠናከር እና የካርቦን ክምችትን በመጨመር ለአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ አስተዋፅኦ ለማድረግ በእያንዳንዱ እርሻ ውስጥ የሚገኙ የጥላ ዛፎችን ብዛት በመጨመር ላይ ያተኩራል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • በሬንፎረስት አሊያንስ (RA) ሰርቲፋይድ በሆነው የሰብል ቦታ ውስጥ በሄክታር የሚገኙ የጥላ ዛፎችን ብዛት መቁጠር።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

*የሰርቲፊኬት ባለቤት በዘላቂ ግብርና ስታንዳርድ መሠረት ሰርቲፋይድ ከሆነ፣ ይህ አመልካች ሪፖርት የሚደረገው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በእርሻ ላይ የሚገኙ የሀገር በቀል ዛፍ ዝርያዎች ብዛት  

መግለጫ፦

ይህ አመልካች በእርሻው ላይ የሚገኙ (በተፈጥሮ የበቀሉ ወይም ሆን ተብሎ የተተከሉ) የተለያዩ ሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎችን ጠቅላላ ብዛት ይለካል። ይህም በእርሻ ላይ ያለውን የዛፍ ዝርያ ስብጥር (diversity) እና የአካባቢው ስነ-ምህዳር ምን ያህል እየተጠበቀ ወይም እንደገና እየለማ መሆኑን የሚያንጸባርቅ ሲሆን፣ በተጨማሪም የብዝኃ ሕይወት ጥበቃን በማበረታታት የእርሻውን የመቋቋም አቅም ያጠናክራል። ሀገር በቀል ዛፎች በጥምር አርሻ ሥርዓቶች ውስጥ፣ በእርሻ ድንበሮች ላይ፣ ለእንጨት ተብለው በተተከሉ ጥቃቅን ደኖች ውስጥ ወይም በደን እና የእንስሳት እርባታ (silvopasture) ባሉ የምርት ሥርዓቶች ውስጥ ተካተው ሊገኙ ይችላሉ።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • በእርሻው ላይ የሚገኙ የተለያዩ ሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎችን ጠቅላላ ብዛት መቁጠር።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በጥምር አርሻ ስር የሚገኝ የእርሻ ቦታ በመቶኛ

መግለጫ፦

ይህ አመልካች በጥምር አርሻ ሥርዓት የሚተዳደረውን ጠቅላላ የእርሻ ቦታ መጠን ይለካል። ይህም ብዝኃ ሕይወትን ለመጨመር፣ የአፈርን ጤና ለማሻሻል፣ የውሃ አካላትን ለመጠበቅ እና አጠቃላይ የእርሻውን የመቋቋም አቅም ለማጠናከር የግብርና-ሥነ-ምህዳር (agroecological) ልምዶች ምን ያህል ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ያንጸባርቃል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • ከአጠቃላይ የእርሻ ስፋት አንጻር በመቶኛ የሚሰበሰብ።

  • ለአነስተኛ እርሻ ቡድኖች፣ በቡድን ውሂብ አሰባሰቡ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም እርሻዎች አማካይ በመቶኛ ሪፖርት ማድረግ።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በተፈጥሮ እፅዋት የተሸፈነ የእርሻ ቦታ ስፋት መቶኛ

መግለጫ፦

በተፈጥሮ እፅዋት ተሸፍኖ የሚቆይ አጠቃላይ የእርሻ ቦታ ስፋት።

ይህ አመልካች በተፈጥሮ እጽዋትነት ተጠብቆ የቆየውን ወይም እንደገና እንዲያገግም የተደረገውን አጠቃላይ የእርሻ ቦታ መጠን ይለካል። ይህም ሀገር በቀል ደኖችን፣ የጥምር አርሻ ሥርዓቶችን፣ በወንዞች ዳርቻ የሚገኙ የጥበቃ ቀጠናዎችን (riparian buffers)፣ ወይም በእርሻ ስራ ያልተለወጡ ወይም ያልተጎዱ ማንኛውንም ያልታረሱ ቦታዎችን ያካትታል። የተፈጥሮ እጽዋትን መጠበቅ ለብዝኃ ሕይወት ጥበቃ ይረዳል፣ የአፈር እና የውሃ ጤናን ያሻሽላል፣ እንዲሁም አጠቃላይ የእርሻውን የመቋቋም አቅም ያጠናክራል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • ከአጠቃላይ የእርሻ ቦታ አንጻር በመቶኛ የሚሰበሰብ።

  • ለአነስተኛ እርሻ ቡድኖች፣ በቡድን ውሂብ አሰባሰቡ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም እርሻዎች አማካይ በመቶኛ ሪፖርት ማድረግ።

  • አምራቹ በተፈጥሮ እጽዋት የተሸፈነውን ቦታ ፖሊጎን (polygons) ወይም ሌሎች ተቀባይነት ያላቸውን ዘዴዎች በመጠቀም መለካት እና በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ፕላትፎርም (RACP) ላይ ባለው የአመልካች ዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ማድረግ አለበት።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

*የሰርቲፊኬት ባለቤት በዘላቂ ግብርና ስታንዳርድ መሠረት ሰርቲፋይድ ከሆነ፣ ይህ አመልካች ሪፖርት የሚደረገው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ኦርጋኒክ ያልሆኑ ማዳበሪያዎች መጠን በሊትር ወይም በኪሎግራም

መግለጫ፦

ባለፈው ዓመት በዋናው ሰርቲፋይድ ሰብል ላይ ጥቅም ላይ የዋለው የኦርጋኒክ ያልሆኑ (ሰው ሠራሽ) ማዳበሪያ መጠን በኪሎግራም (kg) ወይም በሊትር (L)። ይህንን መከታተል አምራቾች የንጥረ ነገር አያያዝን ለማሻሻል፣ ከልክ ያለፈ የግብዓት አጠቃቀምን ለመቀነስ እንዲሁም ለአፈር እና ለአካባቢ ጤና ድጋፍ ለማድረግ ይረዳቸዋል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • በኪሎግራም (kg) እና/ወይም በሊትር (L) የሚገለጽ የቁጥር እሴት ሆኖ የሚሰበሰብ።

  • በዋናው ሰብል ላይ ጥቅም ላይ የዋለው ጠቅላላ የኦርጋኒክ ያልሆነ ማዳበሪያ መጠን።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

*የሰርቲፊኬት ባለቤት በዘላቂ ግብርና ስታንዳርድ መሠረት ሰርቲፋይድ ከሆነ፣ ይህ አመልካች ሪፖርት የሚደረገው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

የኦርጋኒክ ማዳበሪያዎች መጠን በሊትር ወይም በኪሎግራም

መግለጫ፦

ባለፈው ዓመት ጥቅም ላይ የዋለው የኦርጋኒክ ማዳበሪያ መጠን።

ኦርጋኒክ ማዳበሪያዎች ለሰብሎች ንጥረ ነገር የሚሰጡ ከዕፅዋት ወይም ከእንስሳት ምንጭ የሚገኙ ቁሶችን ያካትታሉ፤ ለምሳሌ፦ ኮምፖስት፣ ፍግ፣ በአፈር ውስጥ የሚገኝ የደረቁ እፅዋት ክምችት (peat) እና ፈሳሽ ፍግ (slurry) ናቸው። የኦርጋኒክ ማዳበሪያ አጠቃቀምን መከታተል ኃላፊነት የተሞላበት የንጥረ ነገር አያያዝን ይደግፋል፣ የአፈርን ጤና ያሻሽላል፣ እንዲሁም ዘላቂ የእርሻ ልምዶችን ያበረታታል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • በኪሎግራም (kg) እና/ወይም በሊትር (L) የሚገለጽ የቁጥር እሴት ሆኖ የሚሰበሰብ።

  • በዋናው ሰብል ላይ ጥቅም ላይ የዋለው ጠቅላላ የኦርጋኒክ ማዳበሪያ መጠን።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

የፀረ-ተባይ አጠቃቀም ብዛት

መግለጫ፦

ይህ አመላካች ባለፈው ዓመት ውስጥ በሰብል ላይ ስንት ጊዜ ፀረ-ተባዮች እንደተረጩ ይለካል። የፀረ-ተባይ አጠቃቀም ድግግሞሽን መከታተል አምራቾች መረጃን መሠረት ያደረገ ውሳኔ እንዲያስተላልፉ እና እንደ የተቀናጀ የተባይ አያያዝ (IPM) ያሉ ልምዶችን እንዲተገብሩ ይረዳቸዋል። ይህም በተፈጥሯዊ መንገድ ተባዮችን ለመቆጣጠር እንዲሁም ጤናማ እና ጠንካራ ሰብሎችንና አፈርን ለማግኘት ይረዳል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • በእያንዳንዱ ንቁ ንጥረ ነገር መሠረት የፀረ-ተባይ አጠቃቀም ድግግሞሽ።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ጥቅም ላይ የዋለ የፀረ-ተባይ መጠን (በኪሎግራም/በሄክታር)፣ በእያንዳንዱ ንቁ ንጥረ ነገር ተለይቶ የቀረበ)

መግለጫ፦

ይህ አመላካች ባለፈው ዓመት በሰብል ላይ ጥቅም ላይ የዋለውን የፀረ-ተባይ መጠን፣ በእያንዳንዱ ንቁ ንጥረ ነገር ለይቶ ይለካል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • በእያንዳንዱ ንቁ ንጥረ ነገር መሠረት ጥቅም ላይ የዋለ ጠቅላላ የፀረ-ተባይ መጠን።

  • በአንድ ሄክታር በኪሎግራም (Kg/ha) ሪፖርት የሚደረግ።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በልዩ ሁኔታ እንዲያገለግሉ የተፈቀዱ ንቁ ንጥረ ነገሮች ብዛት

መግለጫ፦

ይህ አመላካች ባለፈው ዓመት በሰብል ላይ ጥቅም ላይ የዋሉትን እና በሬንፎረስት አሊያንስ (RA) ልዩ የአጠቃቀም ፖሊሲ (EUP) እና/ወይም በአስቸኳይ ጊዜ የአጠቃቀም ጥያቄ መሠረት የተፈቀዱ የፀረ-ተባይ ንቁ ንጥረ ነገሮችን ብዛት ይለካል። የልዩ የአጠቃቀም ፖሊሲ (EUP) አጠቃቀምን መከታተል ኃላፊነት የተሞላበት የፀረ-ተባይ አያያዝን ለማረጋገጥ ይረዳል፣ ከተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ ጋር መጣጣምን ይደግፋል፣ እንዲሁም ይበልጥ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ዘላቂ የተባይ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን ያበረታታል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • በልዩ የአጠቃቀም ፖሊሲ (EUP) ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ ንቁ ንጥረ ነገሮች እና/ወይም ፈቃድ ተሰጥቷቸው ጥቅም ላይ የዋሉ የድንገተኛ ጊዜ የአጠቃቀም ጥያቄዎች ብዛት።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

የማደስ ወይም የመልሶ መልማት ልምዶች የተተገበሩበት የምርት ቦታ በመቶኛ

መግለጫ፦

ይህ አመላካች የእርሻውን ሁኔታ መሠረት ያደረጉ የማደስ ወይም የመልሶ መልማት ልምዶች (ቅርንጫፍ መቁረጥን ጨምሮ) የተተገበሩበትን የምርት ቦታ መጠን ይለካል። እነዚህን ልምዶች መከታተል የሰብል ጤናን፣ ምርታማነትን እና የረጅም ጊዜ የእርሻ መቋቋም አቅምን ለማሻሻል ይረዳል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • የማደስ ወይም የመልሶ መልማት ልምዶች የተተገበሩበት የምርት ቦታ አማካይ መቶኛ።

  • በመቶኛ ሪፖርት ይደረጋል።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

በሽፋን ሰብሎች፣ በአፈር መሸፈን እና/ወይም ለስላሳ አረሞች የተሸፈነ የምርት ቦታ መቶኛ

መግለጫ፦

በሽፋን ሰብሎች፣ በኦርጋኒክ የአፈር መሸፈን ወይም በተፈጥሮ በሚበቅሉ ለስላሳ አረሞች አማካኝነት የአፈር ሽፋኑ ተጠብቆ የቆየበት የምርት ቦታ መጠን። የአፈር ሽፋንን መጠበቅ እና መከታተል የአፈርን ጤና ይደግፋል፣ መሸርሸርን ይከላከላል፣ እርጥበትን ይጠብቃል፣ እንዲሁም አምራቹ የረጅም ጊዜ የእርሻ መቋቋም አቅምን ለሚያሳድጉ የተሃድሶ ግብርና ልምዶች ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • በሽፋን ሰብሎች፣ በአፈር ሽፋን እና/ወይም በለስላሳ አረሞች የተሸፈነ የምርት ቦታ አማካይ መቶኛ።

  • በመቶኛ ሪፖርት ይደረጋል።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

የአፈር መሸርሸር መቶኛ

መግለጫ፦

ይህ አመላካች በአፈር መሸርሸር የተጎዳውን የምርት ቦታ መጠን ይለካል።

የአፈር መሸርሸርን መከታተል እንደ እርከን ተከላ፣ አፈር መሸፈን፣ ጥምር አርሻ (agroforestry) እና የሽፋን ሰብሎችን የመሳሰሉ የአፈር ጥበቃ ልምዶች ምን ያህል ውጤታማ እንደሆኑ ለመገምገም ይረዳል፣ ይህም የተሻሻለ የአፈር ጤና እና የረጅም ጊዜ የእርሻ መቋቋም አቅምን ይደግፋል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • በአፈር መሸርሸር የተጎዳ የምርት ቦታ አማካይ የመቶኛ መጠን።

  • በመቶኛ ሪፖርት ይደረጋል።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

የአፈር ኦርጋኒክ ይዘት መቶኛ፣ እና/ወይም የምድር ትል ብዛት፣ እና/ወይም የረቂቅ ህዋሳት ብዛት

መግለጫ፦

በተሃድሶ ግብርና የአሠራር ዘዴ የአፈርን ጤና ለመከታተል፣ አምራቾች ከሚከተሉት አመላካቾች ውስጥ በአንዱ ወይም ከዚያ በላይ በሆኑት ላይ ሪፖርት ለማድረግ መምረጥ ይችላሉ፦ የአፈር ኦርጋኒክ ይዘት፣ የምድር ትል ብዛት እና/ወይም የረቂቅ ህዋሳት ብዛት። እነዚህ አመልካቾች እያንዳንዳቸው የአንድ ጤናማ እና ሕይወት ያለው የአፈር ሥርዓት አስፈላጊ ገጽታዎችን ያንፀባርቃሉ።

ውሂብ መሰብሰብ፦

  • እንደ ቁጥራዊ እሴት ይሰበሰባል።

  • የአፈር ኦርጋኒክ ይዘት በመቶኛ ሪፖርት ይደረጋል።

  • የምድር ትል ብዛት (በኪ.ግ/በሄክታር) ሪፖርት ይደረጋል።

  • የረቂቅ ህዋሳት ብዛት በአንድ ግራም አፈር ውስጥ ባለው ቁጥር ሪፖርት ይደረጋል።

  • ለአነስተኛ እርሻ ቡድኖች፣ ሪፖርት ለማድረግ ከመረጡት(ጧቸው) ማንኛውም አመላካች(ቾች) አማካይ መሆን አለበት።

  • ሪፖርት የተደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ለመስኖ አገልግሎት የዋለ አጠቃላይ የውሃ መጠን (በሊትር)

መግለጫ፦

በእርሻ ቦታው ላይ ለመስኖ አገልግሎት የዋለ አጠቃላይ የውሃ መጠን (በሊትር)። ከመጀመሪያው ዓመት ጀምሮ ለመስኖ የሚያገለግል የውሃ አጠቃቀምን በመከታተል ውጤታማ የውሃ አያያዝን ማሳደግ፣ አምራቾች የውሃ ፍጆታቸውን እንዲቆጣጠሩ፣ የውሃ ሀብታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ እና ዘላቂነት ያለው የግብርና አሠራሮችን እንዲደግፉ ያስችላቸዋል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

ማሳሰቢያ፦ ተፈጻሚ የሚሆነው በእርሻው ላይ የመስኖ ልምድ ካለ እና ሪፖርት ከተደረገ ብቻ ነው።

  • ለመስኖ አገልግሎት የዋለውን አጠቃላይ የውሃ መጠን በሊትር የሚገልጽ የቁጥር እሴት።

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

*የሰርቲፊኬት ባለቤት በዘላቂ ግብርና ስታንዳርድ መሠረት ሰርቲፋይድ ከሆነ፣ ይህ አመልካች ሪፖርት የሚደረገው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ለማቀነባበሪያ አገልግሎት የዋለ አጠቃላይ የውሃ መጠን (በሊትር)

መግለጫ፦

ባለፈው ዓመት የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ሰብልን ለማቀነባበር ጥቅም ላይ የዋለ አጠቃላይ የውሃ መጠን። ለማቀነባበሪያ የሚውል የውሃ አጠቃቀምን መከታተል ውጤታማ የውሃ አያያዝን ያሳድጋል፤ እንዲሁም አምራቾች የውሃ ፍጆታቸውን እንዲቆጣጠሩ፣ የውሃ ሀብታቸውን በአግባቡ እንዲጠቀሙ እና ዘላቂነት ያለው የግብርና አሠራሮችን እንዲደግፉ ያስችላቸዋል።

ውሂብ መሰብሰብ፦

ማሳሰቢያ፦ ለቡድን አመራር፣ ይህ ተፈጻሚ የሚሆነው ቡድኖቹ ማዕከላዊ የዝግጅት ተቋማት ካሏቸው ብቻ ነው።

  • በሊትር የሚገለጽ የቁጥር እሴት።

  • በማቀነባበሪያ ቦታው (ቦታዎቹ) ላይ በተገጠመው የአመራር ምዝገባ ሥርዓት መሠረት ጥቅም ላይ የዋለውን አጠቃላይ የውሃ መጠን ይመዝግቡ። የመለኪያ አሃዱን ያረጋግጡ እና አስፈላጊ ከሆነ ወደ ሊትር ይለውጡ።

  • ምንም ዓይነት የመመዝገቢያ ሥርዓት ከሌለ፣ ለማቀነባበሪያ ተግባራት የተሰበሰበውን የውሃ መጠን ይለኩ።  

  • ሪፖርት የሚደረገው ውሂብ ካለፈው ዓመት የተገኘ ነው።

*የሰርቲፊኬት ባለቤት በዘላቂ ግብርና ስታንዳርድ መሠረት ሰርቲፋይድ ከሆነ፣ ይህ አመልካች ሪፖርት የሚደረገው አንድ ጊዜ ብቻ ነው።

ተፈጻሚነት፦

የቡድን ሰርቲፊኬሽን

የግል ሰርቲፊኬሽን

አነስተኛ እርሻዎች (S-farms)

ትላልቅ እርሻዎች (L-farms)

የቡድን አመራር

አነስተኛ/ትልቅ (S/L)

ሌሎች መረጃዎች

ይህ ሰነድ ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመበት ቀን (ቁ. 1.0)፦ የካቲት 24፣ 2017 ዓ.ም.

ሰርቲፊኬሽን ለማግኘት “አስገዳጅ” ተብለው የተጠቀሱ ሰነዶች መሟላት አለባቸው። “አስገዳጅ ያልሆኑ” ተብለው የተጠቀሱ ሰነዶች፣ አንባቢዎች መስፈርቶችንና ሌሎች አስገዳጅ ይዘቶችን እንዲረዱና እንዲተገብሩ ለመርዳት አስገዳጅ ያልሆኑ መረጃዎችን ይሰጣሉ።

የትርጉም ማሳሰቢያ

በትርጉሙ ውስጥ ስላለው መረጃ ትክክለኛ ትርጉም ማንኛውም ጥያቄ ሲኖር፣ ለማብራሪያ የእንግሊዝኛውን ኦፊሴላዊ እትም ያማክሩ። በትርጉም ምክንያት የሚፈጠሩ ማንኛውም ስህተቶች ወይም የትርጉም ልዩነቶች አስገዳጅ አይደሉም እና ለኦዲት ወይም ለሰርቲፊኬሽን ዓላማዎች ምንም ውጤት አይኖራቸውም።

ይህንን ይዘት ከሬንፎረስት አሊያንስ ቅድሚያ የጽሑፍ ፈቃድ ውጭ ማባዛት፣ ማሻሻል፣ ማሰራጨት ወይም እንደገና ማተም በጥብቅ የተከለከለ ነው።

ተጨማሪ መረጃ?

የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬት ለማግኘት እርዳታ ለማግኘት የደንበኛ ስኬት ቡድናችንን customersuccess@ra.org ላይ ያግኙ።

ስለ ሬንፎረስት አሊያንስ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ http://www.rainforest-alliance.org ይጎብኙ፣ info@ra.org ላይ ወይም የሬንፎረስት አሊያንስ አምስተርዳም ቢሮ፣ De Ruijterkade 6፣ 1013AA Amsterdam፣ The Netherlands ያግኙን።