የቃላት ዝርዝር ዓባሪ v1.5

Prev Next

ርዕስ፦

የቃላት ዝርዝር ዓባሪ

ኮድ፦

A-03-SCRL-B-CH

እትም፦

1.5

የሚመለከተው፦

የእርሻና የአቅርቦት ሰንሰለት ሰርቲፊኬት ባለቤቶችን

አፈጻጸም፦

አስገዳጅ ይዘት

ተፈጻሚነት የሚጀምርበት ቀን፦

የካቲት 22፣ 2018 ዓ.ም

የሚያበቃበት ጊዜ፦

እስከሚቀጥለው ማሳሰቢያ ድረስ

የታተመበት ቀን፦

ሴፕቴምበር 23፣ 2025

ከሚከተለው ጋር ይገናኛል፦

የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች እና የአቅርቦት ሰንሰለት መስፈርቶች፣ ሁሉም ተያያዥ ዓባሪዎች፣ ሰርቲፊኬሽን፣ የኦዲት ህጎች እና የእርግጠኝነት አስገዳጅ ሰነዶች።

የሚከተለውን ይተካል፦

A-03-SCRL-B-CH-V1.4 የቃላት ዝርዝር ዓባሪ።

ይህ ሰነድ ስለ ምንድን ነው?

ይህ ዓባሪ በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ፕሮግራም ውስጥ ጥቅም ላይ ለዋሉት ቃላት የቃላት ዝርዝርን ያቀርባል። በሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች፣ በአቅርቦት ሰንሰለት መስፈርቶች እና በተዛማጅ ሰነዶች ውስጥ የተካተቱት ሁሉም ቃላት በዚህ የቃላት ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል። እንዲሁም በአስገዳጅ የእርግጠኝነት ሰነዶች ውስጥ ያሉት ቃላት ትርጉሞችም ተካተዋል።

ይህንን ሰነድ መቼ እና እንዴት መጠቀም ይቻላል?

ይህ ሰነድ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች፣ የሰርቲፊኬሽን አካላት እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት በሬንፎረስት አሊያንስ አውድ ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉትን ቃላት ወጥነት ባለው መልኩ እንዲረዱ ለማረጋገጥ ታስቦ የቀረበ ነው።

ከእትም 1.4 ወደ እትም 1.5 የተደረጉ ዋና ለውጦች

ርዕስ

የተደረገው ለውጥ

የተሻሻሉ ትርጉሞች

ግልጽነት ለመስጠት የሚከተሉት የቃላት ትርጉሞች ተሻሽለዋል፦ ንቁ ንጥረ ነገር፣ አግሮኬሚካሎች፣ ጥምር እርሻ፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኮምፖስት)፣ ድርብ ሽያጭ፣ ማዳበሪያ፣ ፀረ-ፈንገስ፣ ፀረ-አረም፣ ቤተሰብ፣ አይነቱ የተጠበቀ፣ ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ፣ ፀረ-ነፍሳት፣ የተቀናጀ የተባይ አያያዝ (IPM)፣ ከፍተኛ የቅሪት ደረጃዎች (MRLs)፣ ሀገር በቀል እፅዋት፣ የተፈጥሮ ጠላቶች፣ ጊዜ ያለፈበት ፀረ-ተባይ፣ የግል መከላከያ መሳሪዎች (PPE)፣ ተባይ፣ ፀረ-ተባይ፣ ፕሪሚየም፣ የሰብል ምርታማንት ሳይቀንስ ማደስ፣ ሰብልን ሙሉ ለሙሉ ማደስ፣ ውስን የመግቢያ የጊዜ ልዩነቶች (REI)፣ የውሃ ዳርቻ ጥበቃ ቀጠና፣ ሮዴንቲሳይድ፣ ሮያሊቲ፣ የጥላ ዛፍ፣ የርጭት መበታተን እና የዱር እንስሳት ተባይ።  

አዳዲስ ቃላትና ትርጓሜዎች ታክለዋል

ከተሃድሶ ግብርና ጋር የተያያዙ የሚከተሉት ቃላት እና ትርጓሜዎች ታክለዋል፦ ባዮሎጂካል ብዝሃነት፣ ባዮሎጂካል ግብዓት፣ መሸፈኛ ሰብሎች፣ የትል ብዛት ቆጠራ፣ ሥነ ምህዳራዊ ማጨድ፣ በተባይ/በበሽታ የሚደርስ የኢኮኖሚ ጉዳት፣ የሥነ ምህዳር ጤና፣ የማዳበሪያ አተገባበር እቅድ፣ የቅጠል ምዘና፣ ቅርንጫፍ መቀጠል፣ የእጽዋት መከለያዎች፣፣ የተቀናጀ የአረም አያያዝ (IWM)፣ ማይክሮባዮሎጂያዊ አመላካቾች፣ የረቂቅ ሕዋሳት ስብስብ፣ የረቂቅ ሕዋሳት ብዛት፣ አፈር መሸፈን፣ የተፈጥሮ ዛፍ እፅዋት ሽፋን፣ ናይትሮጅን አስተካካይ ዛፎች፣ የኦርጋኒክ ንጥረ ነገር ምንጮች፣ ተሃድሶ ግብርና፣ የሰብል ማልሶ ማቋቋም፣ ተቋቋሚ የዕፅዋት ዝርያ፣ ፍሳሽ፣ ዘገይቶ የሚለቀቅ ማዳበሪያ፣ ለስላሳ አረሞች፣ የአፈር ጤና አመላካቾች፣ የአፈር ኦርጋኒክ ይዘት (SOM)፣ ጉቶ ላይ መቁረጥ፣ ሰው ሰራሽ ማዳበሪያ፣ ታጋሽ የእፅዋት ዝርያ፣ የፀረ-ተባዮች መርዛማነት፣ ትነት እና የነፋስ መከላከያዎች።

የተሰረዙ ቃላት

የሚከተሉት ቃላት ጊዜ ያለፈባቸው በመሆናቸው ተሰርዘዋል፦ የዘለቄታዊነት ተጨማሪ ክፍያ (SD) እና የዘለቄታዊነት ኢንቨስትመንት (SI)።

ሀገር በቀል እፅዋት

በመቶዎችና በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት ያለ የሰው ጣልቃ ገብነት በዝግመተ ለውጥ ምክንያት በአንድ የተወሰነ ጂኦግራፊያዊ ክልል ወይም ሥነ-ምህዳር ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኙ ሀገር በቀል የእፅዋት ዝርያዎችን ያመለክታል። እነሱ የሥነ-ምህዳር ሚዛንን እና ባዮሎጂካል ብዝሃነትን በመጠበቅ ረገድ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።[1]

ለመኖሪያነት የሚውል አካባቢ

በአስተዳደር የቀረበው የሠራተኞች አጠቃላይ የመኖሪያ ስፋት።

ለስላሳ አረሞች

በተፈጥሮ በሰብሎች መካከል የሚበቅሉ (ብዙውን ጊዜ ለስላሳ ግንድ ያላቸው) ነገር ግን በአደገኛ ሁኔታ የማይሰራጩ ወይም ለንጥረ ነገሮች፣ ለውሃ ወይም ለፀሐይ ብርሃን በከፍተኛ ደረጃ የማይወዳደሩ እፅዋት። እነሱ በተቀናጀ የአረም አያያዝ አሠራሮች ውስጥ በቀላሉ ቁጥጥር ሊደረግባቸው የሚችሉ ሲሆኑ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ሳያስከትሉ ሥነ-ምህዳራዊ እና አግሮኖሚክ ጥቅሞችን ሊሰጡ ይችላሉ። እነዚህ ጥቅሞች የአፈርን አወቃቀር ማሻሻል፣ መሸርሸርን መከላከል፣ የአበባ ዘር አስተላላፊዎችን እና የተፈጥሮ ተባይ አዳኞችን መሳብ እና የበለጠ አደገኛ የሆኑ አረሞችን መገደብ ያካትታሉ።[2]

ለውጥ (የመሬት አጠቃቀም)

የመሬት አካባቢን ተግባር ወይም ዓላማ ወደ ሌላ የመሬት አጠቃቀም መቀየር፣ ይህም ብዙውን ጊዜ በተፈጥሮ ሥነ ምህዳር የዝርያዎች ስብጥር፣ አደረጃጀት ወይም ተግባር ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል። ይህ የተፈጥሮ ሥነ ምህዳር ወደ እርሻ፣ ወደ ለእርሻ የሚያገለግል መሬት፣ ወደ የግጦሽ መሬት፣ ወደ የውሃ ማጠራቀሚያዎች፣ ወደ መሰረተ ልማት፣ ወደ ማዕድን ማውጫ እና ወደ ከተማ አካባቢዎች መለወጥን ያካትታል ነገር ግን በእነዚህ ብቻ አይወሰንም።

የደን ጭፍጨፋ አንድ የልወጣ ዓይነት ነው (ደን መለወጥ)።

መለወጥ ከፍተኛ መበላሸትን፣ ወይም በሥነ ምህዳሩ የቀድሞ የዝርያዎች ስብጥር፣ አደረጃጀት ወይም ተግባር ላይ ከፍተኛ እና ዘላቂነት ያለው ለውጥ የሚያስከትሉ የአስተዳደር አሠራሮችን ማስተዋወቅን ያጠቃልላል።

ይህንን ትርጉም የሚያሟላ በተፈጥሮ ሥነ ምህዳሮች ላይ የሚደረግ ለውጥ ህጋዊ ቢሆንም ባይሆንም መለወጥ ተብሎ ይወሰዳል።[3]

ልጅ

ከ18 ዓመት በታች የሆነ ማንኛውም ግለሰብ።[4]

ኃላፊነት የሚሰማው የንግድ ምግባር

የአካባቢን፣ የሰዎችን እና የማህበረሰብን ጥበቃ በንግድ አሠራር እና ምግባር ዋና ውስጥ መካተቱን ማረጋገጥ። ኃላፊነት የሚሰማው የንግድ ምግባር ከሁሉም በላይ የሰብዓዊ መብቶችን ማክበር፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የሠራተኛ ግንኙነት እና የፋይናንስ ተጠያቂነትን የመሳሰሉ ሕጎችን ማክበርን የሚጠይቅ ሲሆን፣ እነዚህ ሕጎች በሕጋዊ መንገድ ደካማ ተፈጻሚነት ቢኖራቸውም እንኳ መከበር አለባቸው።[5]

ሕጋዊ ተቋም/ድርጅት

ተዋናይ ይመልከቱ።

መለያየት

ሰርቲፋይድ ምርት ከሰርቲፋይድ ካልሆነ ምርት እና እርስ በእርሳቸው በአካልም ሆነ በሰነድ ተለይቶ የሚቀመጥበት የትረሰቢሊቲ ሂደት። ይህ መለያየት በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ባሉ ሁሉም የመቀበያ፣ ማቀነባበሪያ፣ ማሸግ፣ ማከማቻ እና ማጓጓዣ ደረጃዎች ይከሰታል። ሰርቲፋይድ ያልሆነ ምርት ከሰርቲፋይድ ምርት ጋር ምንም ዓይነት መቀላቀል የለም። ይህ ማለት ምንም እንኳን ከተለያዩ ሰርቲፋይድ ምንጮች/እርሻዎች (ሌሎች መነሻ አገሮችን ጨምሮ) ሊመጣ ቢችልም፣ ሙሉ የምርት ይዘቱ ሰርቲፋይድ ነው።

መልሶ አልሚ ግብርና

የሰብልን ተቋቋሚነት ለመጨመር፣ የአፈርን ጤና ለመመለስ፣ ብዝሃ ሕይወትን ለማሳደግ፣ የውሃ ዑደቶችን ለማሻሻል እና ካርቦን ለመሰብሰብ የግብርና-ሥነ-ምህዳር መርሆችን የሚጠቀም አጠቃላይና በስርዓት ላይ የተመሠረተ የእርሻ መንገድ። እነዚህ አሠራሮች የተረጋጋ ኑሮዎችን ይደግፋሉ እና ለአየር ንብረት ጥንካሬ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።[6]

መሰረታዊ መከላከያ ልብሶች

ፀረ-ተባዮችን ለሚይዙ ሰዎች የሚያገለግሉ ልብስ እና ጫማዎች፣ ይህም ረጅም እጅጌ ባለው ሸሚዝ ላይ የሚለበስ ልብስ፣ ረጅም ሱሪ፣ ካልሲ እና ጠንካራ ጫማዎች፣ ኬሚካልን የሚቋቋሙ ጓንቶች፣ የዓይን መከላከያ (ማለትም የፊት ጭንብል ወይም መነጽሮች)፣ እና የመተንፈሻ መከላከያ (ማለትም የመተንፈሻ መሣሪያ) ያካትታል።

መስኖ

የተፈጥሮ ዝናብን ለማሟላት፣ የእፅዋትን እድገት ለማመቻቸት እና የግብርና ምርታማነትን ለማስቀጠል ሲባል ውሃን ሰው ሠራሽ በሆነ መንገድ ወደ አፈር ወይም ሰብሎች ማድረስ።[7]

መሸፈኛ ሰብሎች

በምርት አካባቢው ውስጥ ለአፈር የእፅዋት ሽፋን ለመስጠት የሚበቅሉ ሳሮች፣ ጥራጥሬዎች እና ሌሎች እፅዋት። እነዚህ የአፈር መሸርሸርን መቀነስ፣ ኦርጋኒክ ይዘትን መጨመር፣ የአፈርን አወቃቀር ማሻሻል፣ እርጥበትን መያዝ፣ ናይትሮጅን ማስተካከል፣ አጥፊ አረሞችን ማፈን እና ለጥቅም ለሚውሉ ሕያዋን ፍጥረታት መኖሪያን ማሳደግ የመሳሰሉ ብዙ ጥቅሞችን ይሰጣሉ።[8]

መበላሸት

በተፈጥሮ ሥነ ምህዳር ውስጥ የሚከሰቱ ለውጦች የዝርያዎቹን ስብጥር፣ አደረጃጀት እና/ወይም ተግባርን በከፍተኛ ሁኔታ እና በአሉታዊ መልኩ የሚነኩ እንዲሁም የሥነ ምህዳሩን ምርቶችን የማቅረብ፣ ባዮሎጂካል ብዝሃነትን የመደገፍ እና/ወይም የሥነ ምህዳር አገልግሎቶችን የመስጠት አቅምን የሚቀንሱ ናቸው።[9]

መኖሪያ ቤት

ከተፈጥሯዊ የአየር ሁኔታዎች (እንደ ዝናብ፣ ውርጭ፣ ንፋስ፣ ሙቀት፣ ቅዝቃዜ፣ እርጥበት፣ የፀሐይ ብርሃን የመሳሰሉትን ያካትታል ነገር ግን በእነሱ ብቻ አይወሰንም) ጥበቃ የሚሰጥ እና ከአዳኞች የሚከላከል መጠለያ። ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ንጹህ እና ጥሩ መኖሪያ ቤት ለሰው ልጅ ደህንነት እና ለሠራተኞች መብት ወሳኝ አካል ሲሆን፣ በአካባቢ እና በግንባታ፣ በጤና እና በንጽህና እንዲሁም በምቾት እና በጨዋነት ረገድ በቂ የኑሮ ሁኔታዎችን ማቅረብ አለበት።

መካከለኛ

ለእርሻ ወይም ለአቅርቦት ሰንሰለት ሰርቲፊኬት ባለቤት የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ምርትን የሚገበያይ (የሚገዛና የሚሸጥ) እና/ወይም የሚያስተናግድ ማንኛውም ተዋናይ ነው።

በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ የአቅርቦት ሰንሰለቶች ውስጥ የተለመዱ የመካከለኛ ምሳሌዎች ከምርጥ አምራቾች ምርት አግኝተው ለእርሻ ሰርቲፊኬት ባለቤት የሚያቀርቡ እንደ ኮትዲቩዋር ውስጥ ያሉ ትናንሽ ነጋዴዎች ("pisteurs") ወይም በቱርክ ውስጥ ያሉ ("manavs") ናቸው። እነሱ አነስተኛ መጠን ስለሚያስተናግዱ፣ ሬንፎረስት አሊያንስ መካከለኛዎችን በገለልተኛነት ሰርቲፋይድ እንዲሆኑ ወይም በሬንፎረስት አሊያንስ መድረኮች ላይ እንዲመዘገቡ አይጠይቅም። ሆኖም፣ ከሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች የሚመለከታቸውን መስፈርቶች ማክበር አለባቸው፣ እና የሰርቲፊኬት ባለቤት አስተዳደር ለተገዢነታቸው ኃላፊነት መውሰድ አለበት።

መደበኛ የሥራ ሰዓታት

ከተጨማሪ ሰዓት ውጪ፣ በቀን፣ በሳምንት፣ በወር እና/ወይም በዓመት ውስጥ በሠራተኛው/ተቀጣሪው ውል መሰረት የሚሠራው የሰዓታት ብዛት ነው።

ሚስጥራዊነት

አንድ ግለሰብ/አካል ሚስጥራዊ መረጃን ከሌላኛው ወገን ግልጽ ፈቃድ ውጭ እና የሕፃናት ጉዳይ ከሆነ ደግሞ ከጠባቂዎቻቸው ፈቃድ ውጭ ለሌሎች ከማካፈል የመታቀብ ግዴታ።

ማህበረሰብ

በአንድ እርሻ፣ የእርሻዎች ስብስብ ወይም ኩባንያ መኖር ወይም አሰራር የተነሳ ተፅዕኖ የሚደርስባቸው፣ በተመሳሳይ ቦታ ወይም ክልል የሚኖሩ የሰዎች ስብስቦች። የገጠር ሠራተኞች፣ የእርሻ ነዋሪዎች፣ ጎረቤቶች፣ ሀገር በቀል ሰዎች እና በአቅራቢያ ያሉ መንደሮች ወይም ከተሞች ነዋሪዎች በተወሰነ እርሻ፣ የእርሻዎች ስብስብ ወይም ኩባንያ ተጽዕኖ ሊደረግባቸው የሚችሉ ማህበረሰቦች ሊሆኑ ይችላሉ።

ነባር ሕዝቦችን እና የአካባቢው ማህበረሰቦችን ይመልከቱ።

ማስተካከያ

የተገዢነት ጉድለትን ለማስወገድ በሰርቲፊኬት ባለቤቱ የሚወሰዱ ፈጣን እርምጃዎች። የሰርቲፊኬቱ ባለቤት የታዩትን የደንብ ጥሰቶች በሙሉ የማስተካከል ግዴታ አለበት።[10]

ማስተካከያ / መፍትሄ

አሉታዊ ተፅዕኖን ለማስተካከል እና አሉታዊ ተፅዕኖውን የሚቃወሙ ወይም የሚያስተካክሉ ዋና ውጤቶችን ለመስጠት ሁለቱንም የሚያመለክቱ በተለዋዋጭ ወይም በጥምረት ጥቅም ላይ የሚውሉ ቃላት።[11]

እነዚህ ውጤቶች እንደ ይቅርታ መጠየቅ፣ ካሳ መክፈል መልሶ ማቋቋም፣ መልሶ መገንባት፣ የገንዘብ ወይም ገንዘባዊ ያልሆነ ካሳ፣ እና የቅጣት ማዕቀቦች (ወንጀለኛ ወይም አስተዳደራዊ፣ እንደ የገንዘብ ቅጣቶች) እንዲሁም ጉዳትን መከላከል (ለምሳሌ በትዕዛዝ ወይም በድጋሚ እንደማይከሰት በማረጋገጥ) ያሉ የተለያዩ ቅርጾችን ሊይዙ ይችላሉ።

ማረጋገጫ

የተገለጹት መስፈርቶች መሟላታቸውን በተጨባጭ ማስረጃ የማረጋገጥ ሂደት።[12]

ማቀነባበር

ሰርቲፋይድ ምርትን በአካል የመለወጥ ሂደት ሲሆን፣ የተለየ ውጤት ያስገኛል (ለምሳሌ ማምረት፣ መጥበስ፣ መቀላቀል)።

ማብቂያ ቀን

በሬንፎረስት አሊያንስ የተቀመጠ የተወሰነ ቀን ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ የተወሰኑ ተግባራት፣ አሠራሮች ወይም ሁኔታዎች ተቀባይነት የሌላቸው እና ከተወሰኑ መስፈርቶች ጋር ተገዢነት ጉድለት የሚፈጥሩ ናቸው።

ማብቃት

ሰዎች/ማህበረሰቦች ሕይወታቸውን እንዲቆጣጠሩ እና ስለ መብቶቻቸው እንዲሟገቱ በእውቀት፣ በክህሎት፣ በልበ ሙሉነት እና በሀብት ማስታጠቅን ያመለክታል። ይህም የተሳትፎ እንቅፋቶችን ማስወገድ፣ እኩልነት የጎደላቸው ሁኔታዎችን መፍታት እና በመረጃ ላይ የተመሠረተ ውሳኔ ለማድረግ ዕድሎችን መስጠትን ያካትታል።[13]

ማይክሮባዮሎጂያዊ አመላካቾች

የአፈር ረቂቅ ህዋሳትን እንቅስቃሴ፣ ብዝሃነት ወይም ጤና የሚያንፀባርቁ ባህሪያት እና መለኪያዎች ናቸው። ምሳሌዎች የማይክሮባላዊ ባዮማስ፣ የኢንዛይም እንቅስቃሴ፣ የማይክሮባላዊ ብዝሃነት እና የአፈር መተንፈስን ያካትታሉ። እነዚህ አመላካቾች የአፈር ባዮሎጂያዊ ተግባር እና መሻሻልን በተመለከተ መረጃ ይሰጣሉ፣ ይህም የአፈር ለምነትን፣ የንጥረ ነገር ዑደትን እና የግብርና አሠራሮችን ተፅእኖ ለመገምገም ያገለግላሉ።

ማዳበሪያ

ለጤናማ የእፅዋት እድገት እና የአፈር ለምነት መቆየትን ለመደገፍ አስፈላጊ የሆኑትን ንጥረ ነገሮች የሚሰጥ፣ በቀጥታ በአፈር ላይ ወይም በእፅዋት ቅጠል ላይ የሚጨመር የኬሚካል ወይም የተፈጥሮ ንጥረ ነገር።[14]

ምስክር ኦዲት

የሰርቲፊኬሽን አካል ኦዲተር የውስጥ ኢንስፔክተርን (ሮችን) አፈጻጸም በውስጣዊ ኢንስፔክሽን ጊዜ የሚመለከትበትና የሚገመግምበት ግምገማ ነው። የምስክር ኦዲት ዓላማ የኦዲት ሂደቱ ብቃት ባለው፣ ገለልተኛ በሆነ እና በተቋቋሙት ስታንዳርዶች መሠረት መከናወኑን ማረጋገጥ ነው። [15]

ምርት ማጓጓዝ

የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ምርትን ከአንድ ሰርቲፊኬት ባለቤት ወደ ሌላው የሚደረግ አካላዊ መጓጓዣ።

ሠራተኛ

ገንዘብ ለማግኘት ሲል የጉልበት ሥራን የሚያከናውን ግለሰብ። ሠራተኛ በውል ሁኔታቸው ምንም ይሁን ምን የሚሰሩ ሁሉንም ዓይነት ሰዎችን ያጠቃልላል፣ ለምሳሌ ቋሚ፣ ጊዜያዊ፣ ወቅታዊ፣ ስደተኛ፣ በክፍል የሚከፈል ሥራ ሠራተኞች፣ በሰነድ የተመዘገቡ፣ ያልተመዘገቡ፣ እንዲሁም በሠራተኛ አቅራቢ በኩል የተቀጠሩ፣ በሥልጠና ላይ ያሉ ሰዎች፣ የቡድን አስተዳደር ሠራተኞች፣ ተለማማጆችን እና የሙያተኞች ተማሪዎችን ጨምሮ፣ እንዲሁም በህመም፣ በወላጅነት ፈቃድ፣ በዓል፣ በሥልጠና ወይም በኢንዱስትሪ አለመግባባት ምክንያት በቅርቡ ከሠሩበት ሥራ ወይም ድርጅት በጊዜያዊነት የቀሩ ሰዎችንም ያጠቃልላል።[16]

ሥርዓተ ፆታ

እንደ ደንቦች፣ ሚናዎች እና በሴቶችና በወንዶች ቡድኖች መካከል ያሉ ግንኙነቶች ያሉ በህብረተሰብ የተገነቡ የሴቶች እና የወንዶች ባህሪያት። ይህ ከህብረተሰብ ወደ ህብረተሰብ የሚለያይ እና ሊለወጥ የሚችል ነው።  አብዛኛዎቹ ሰዎች ወንድ ወይም ሴት ሆነው ቢወለዱም፣ ተገቢ የሆኑ ደንቦች እና ባህሪያት ይማራሉ—ይህም በቤተሰብ፣ በማህበረሰቦች እና በሥራ ቦታዎች ውስጥ ከተመሳሳይ ወይም ከተቃራኒ ጾታ ጋር እንዴት መስተጋብር መፍጠር እንዳለባቸው ይጨምራል። ሰዎች ራሳቸውን እንደ ወንድና ሴት ወይም እንደማንኛውም አካል ሊቆጥሩ ስለሚችሉ የሥርዓተ ፆታ ማንነት በወንድና በሴት ብቻ የተገደበ አይደለም።[17]

ሥርዓተ ፆታ    
እኩልነት

የሴቶች፣ የወንዶች፣ የሴት ልጆች እና የወንድ ልጆች እኩል መብቶች፣ ኃላፊነቶች እና ዕድሎች። እኩልነት ሴቶች እና ወንዶች አንድ ዓይነት ይሆናሉ ማለት አይደለም፣ ነገር ግን የሴቶች እና የወንዶች መብቶች፣ ኃላፊነቶች እና ዕድሎች ወንድ ወይም ሴት ሆነው በመወለዳቸው ላይ የተመሰረቱ አይሆንም ማለት ነው። የሥርዓተ ፆታ እኩልነት የሴቶች እና የወንዶች ፍላጎቶች፣ መስፈርቶች እና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች ግምት ውስጥ መግባታቸውን ያመለክታል፣ ይህም የተለያዩ የሴቶች እና የወንዶች ቡድኖች ልዩነትን በማወቅ ነው። የሥርዓተ ፆታ እኩልነት የሴቶች ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ወንዶችንም ሆነ ሴቶችን ሙሉ በሙሉ ሊመለከት እና ሊያሳትፍ ይገባል። በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለው እኩልነት እንደ ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰድ ሲሆን ማህበረሰብን ማዕከል ያደረገ እንዲሁም ዘላቂነት ላለው ልማት እንደ ቅድመ ሁኔታ እና እንደ አመላካች ይወሰዳል፡፡[18]

ሥርዓተ ፆታን ከግምት ውስጥ ያስገባ

የሥርዓተ ጾታ ደንቦች፣ ሚናዎች እና ግንኙነቶች ከግምት ውስጥ የሚገቡ ሲሆን፣ በዚያ ግንዛቤ መሠረት የሥርዓተ ጾታ እኩልነት የጎደለውን ሁኔታ ለመፍታት እና የወንዶችና የሴቶችን ልዩ ፍላጎቶች ለመመለስ፣ ጎጂ የሥርዓተ ጾታ ደንቦችን፣ ሚናዎችንና ግንኙነቶችን ለመለወጥ እንዲሁም በሴቶችና በወንዶች መካከል ያለውን የኃይል ግንኙነት ለውጦችን ለማበረታታት እርምጃዎች ይወሰዳሉ።

ሥነ-ምህዳራዊ ማጨድ

በታቀደለት እና ወቅቱን በጠበቀ መልኩ የመሬት ላይ እፅዋትን በሜካኒካል መቁረጥ። ይህ የሚከናወነው አረሞችን ለመቆጣጠር፣ ወራሪ ዝርያዎችን ለመግታት፣ የእፅዋትን ብዝሃነት ለመጠበቅ እና ከመጠን ያለፈ የባዮማስ ክምችትን ለማስወገድ ነው። ጊዜን፣ ድግግሞሽን እና የማጨጃን ቁመት በማስተካከል፣ እንደ የአፈር ጤና፣ የአበባ ዘር አስተላላፊ መኖሪያ፣ የተፈጥሮ ተባይ ቁጥጥር ያሉ የሥነ ምህዳር ተግባራትን ይደግፋል እንዲሁም ከሰብሎች ጋር ያለውን ውድድር ይቀንሳል።[19]

ሪፖርት የተደረገ ጉዳይ

ከሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ ከግዳጅ ሥራ፣ ከአድልዎ እና/ወይም ከሥራ ቦታ ላይ በሚፈጸም ሁከትና ትንኮሳ ጋር የተያያዘ ቅሬታ ሲሆን፣ በቅሬታ አፈታት ሥርዓት ውስጥ የገባ እና በቅሬታ ኮሚቴ የተመዘገበ ቅሬታ።

ራስን መገምገም

የሰርቲፊኬት ባለቤቱ የሚመለከታቸው የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች መስፈርቶች ላይ የሚደረግ የተገዢነት ግምገማ ነው። በየዓመቱ የሚከናወን ሲሆን የንዑስ ኮንትራክተሮችን፣ የአገልግሎት አቅራቢዎችን እና የሠራተኛ አቅራቢዎችን የተገዢነት ግምገማ (የሚመለከተው ከሆነ) ያካትታል።

የተቀላቀለ ቡድን አባላት ለሆኑ ትላልቅ እርሻዎች፣ ራስን መገምገም የሚከናወነው በቡድን አስተዳደር ውስጣዊ ኢንስፔክሽን ወይም በትልቁ እርሻ አስተዳደር ራስን መገምገም አማካኝነት ሊሆን ይችላል።

ለቡድኖች፣ ራስን መገምገም የቡድን አባላትን ውስጣዊ ኢንስፔክሽን እና የቡድን አስተዳደር በሚመለከታቸው መስፈርቶች ላይ የሚያደርገውን ራስን መገምገም ያካትታል።

ሮያሊቲ

የRA ምልክቶችን ለመጠቀም ወይም የዘላቂ ግብርና ሰርቲፋይድ እና/ወይም መልሶ አልሚ ግብርና ሰርቲፋይድ መጠኖችን ለመግዛት ወይም ለመሸጥ መብት ለማግኘት፣ ከሬንፎረስት አሊያንስ የፍቃድ ስምምነት አጠቃላይ ውሎች እና ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ በሮያሊቲ የጊዜ ሰሌዳ ላይ እንደተቀመጠው ለሬንፎረስት አሊያንስ የሚከፈል መጠን ነው።

ሮዴንቲሳይድ

ሮዴንቲሳይዶች በእፅዋት፣ በግብርና ምርቶች፣ በተከማቹ ምግቦች ወይም ተዛማጅ መገልገያዎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ አይጦችን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር ወይም ለማጥፋት የተዘጋጁ ኬሚካላዊ ወይም ባዮሎጂያዊ ንጥረ ነገሮች ናቸው። አጠቃቀማቸው ምርታማነትን ለመጠበቅ፣ የኢኮኖሚ ኪሳራዎችን ለመቀነስ፣ የምግብ ደህንነትን ለማረጋገጥ እና በምርት እና በማከማቻ ሥርዓቶች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመከላከል ያለመ ነው።

ሰርቲፊኬሽን

አንድ እርሻ፣ የእርሻዎች ቡድን ወይም የአቅርቦት ሰንሰለት ተዋናዮች ያሉት የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶችን መስፈርቶች ማሟላታቸውን ለማሳየት በሰርቲፊኬሽን አካል የሚሰጥ መደበኛ እውቅና።[20]

ሰርቲፊኬት ሊሰጠው የሚችል ሰብል

በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ፕሮግራም ሰርቲፊኬት ሊሰጣቸው ከሚችሉት የሰብሎች ዝርዝር ውስጥ ያለ ሰብል።

የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ሰብሎችን ይመልከቱ።

ሰርቲፋይድ መጠን

በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ፕሮግራም ስር በተረጋገጡ እና ሰርቲፊኬሽን ባገኙ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች የተመረቱ እና የተሸጡ የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ሰብሎች፣ ምርቶች ወይም ተዋጽኦዎች ብዛት።

ሰርቲፋይድ ምርት

ከሰርቲፋይድ እርሻ የተገኘ እና በሰርቲፋይድ አቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ያለፈ ምርት ወይም ግብዓት (ይህ ምርት ሰርቲፋይድ ተብሎ ቢሸጥም ባይሸጥም ወይም በሰርቲፊኬሽን ጥያቄ ውስጥ ቢካተትም ባይካተትም)።

ሰርቲፋይድ ሰብል

በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ እርሻ ሰርቲፊኬት ወሰን ውስጥ የተካተተ እና በሰርቲፊኬት ባለቤቱ ያደገ እና የተሰበሰበ ማንኛውም ሰብል።

ሰርቲፋይድ እርሻ

ስታንዳርዶቹን እና/ወይም ማንኛውንም ሌላ የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ፕሮግራም ሰርቲፊኬሽን መፍትሄ የሚያሟላ በመሆኑ ሰርቲፋይድ የሆነ እርሻ ወይም የእርሻዎች ስብስብ።

ሰብልን ሙሉ ለሙሉ ማደስ

የዛፍ ሰብል ጤናን፣ ምርታማነትን እና ጥግግትን ለመመለስ ወይም ለማሻሻል ያለመ የእርሻ አሠራር። የቆዩ፣ ምርታማ ያልሆኑ ዛፎችን በአንድ አካባቢ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ እና በአዲስ መተካት ወይም ባሉ ተከላዎች ውስጥ አዳዲስ እፅዋትን መጨመር ወይም በአዲስ መሬት ላይ መትከልን ያካትታል።[21]

ሰብዓዊ መብቶች

ማንኛውም ሰው የሰው ልጅ በመሆኑ ብቻ ሊያገኛቸው የሚችሉ ዓለም አቀፋዊና መሠረታዊ መብቶች ሲሆኑ - በማንኛውም ግዛት የማይሰጡ ናቸው። እነዚህ ዓለም አቀፋዊ መብቶች ለሁሉም የሰው ልጆች ከዜግነት፣ ፆታ፣ ብሔር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት፣ ቋንቋ፣ ወይም ከማንኛውም ሌላ ሁኔታ ውጪ ተፈጥሯዊ ናቸው።

ሰው ሠራሽ ማዳበሪያ

ኦርጋኒክ ያልሆነ ማዳበሪያ ይመልከቱ።

ስደተኛ ሠራተኛ

ለሥራ በአገር ውስጥ እና/ወይም ዓለም አቀፍ ድንበሮችን አቋርጦ የሚሰደድ ሰው።

ስፍራ

የሰርቲፊኬት ባለቤት (እርሻ ወይም የአቅርቦት ሰንሰለት) የሆነ፣ የተወሰነ ቁጥር እና ዓይነት አሠራሮች የሚከናወኑበት በጂኦግራፊያዊ የተለየ ሕጋዊ ተቋም።

ቀላል ሥራ

ከ12 እስከ 15 ዓመት የሆኑ ሕፃናት ለጤና እና ለእድገት ጎጂ ያልሆነ እና ትምህርታቸውን ወይም ሥልጠናቸውን የማያስተጓጉል ሥራ መሥራት የሚችሉበት ሁኔታ ነው። ልጁ በአዋቂ ሰው ቁጥጥር ሥር መሆን አለበት፣ እና ሥራው በሳምንት ከ14 ሰዓት መብለጥ የለበትም።[22]

ቀጣይነት ያለው ምርት

ከወቅታዊ ምርት ይልቅ በየዓመቱ በየጊዜው የሚሰበሰቡ ሰብሎች። [23]  

ቅሬታ

በማንኛውም ሰው በሌላ ሰው ወይም በድርጅት ድርጊቶች ወይም በሕጎቻቸው እና በፖሊሲዎቻቸው ምክንያት በቅሬታ አቅራቢው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ስላደረሱበት የሚቀርብ አቤቱታ ወይም ስጋት።

ቅርብ አደጋ

ወዲያውኑ ወይም አደጋው ከመወገዱ በፊት ሞት ወይም ከባድ የአካል ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ ተብሎ በምክንያታዊነት የሚጠበቁ ማናቸውም ሁኔታዎች፣ አጋጣሚዎች ወይም ተግባራት።

ቅርንጫፍ መቀጠል

የሁለት እፅዋት ቲሹዎች ተቀላቅለው እንደ አንድ እፅዋት አብረው እንዲያድጉ የሚያደርግ የእፅዋት የማባዛት ዘዴ። ቅርንጫፍ መቀጠል የተለያዩ እፅዋት ተፈላጊ ባህሪያትን ለማጣመር ያገለግላል፣ ለምሳሌ ለተባይ እና ለበሽታዎች የመቋቋም አቅምን፣ ምርታማነትን እና የአየር ንብረት መቋቋምን ለማሻሻል ይረዳል።[24]

ቅርንጫፎችን መቁረጥ

የሞቱ፣ የታመሙ ወይም የማያፈሩ ቅርንጫፎችን ለማስወገድ፣ ተባዮችን እና በሽታዎችን ለመቆጣጠር እና/ወይም የሰብል መጠንን ለመቆጣጠር የሚደረግ ወቅታዊ ወይም ዓመታዊ እንቅስቃሴ።

ቆሻሻ

ማንኛውም የማይፈለግ ወይም ተፈላጊ ያልሆነ ይዘት ወይም ንጥረ ነገር። በይዘት ዓይነት እና በክልላዊ አገላለጽ ላይ በመመስረት እንደ ቆሻሻ፣ ጥራጊ፣ መጣያ ወይም ከንቱ ዕቃ ተብሎ ይጠራል። አብዛኛው ቆሻሻ ከወረቀት፣ ከፕላስቲክ፣ ከብረታ ብረት፣ ከመስታወት፣ ከምግብ ቆሻሻ፣ ከኦርጋኒክ ይዘት፣ ከሰገራ እና ከእንጨት የተዋቀረ ነው። አደገኛ ቁሳቁሶችን ያካትታል። የቤት ውስጥ ወይም የኢንዱስትሪ ቆሻሻን፣ ውድቅ የተደረጉ ምርቶችን፣ የሕንፃ ፍርስራሾችን ወይም ድንጋዮችን፣ ከአፈር ቁፋሮ የተገኙ አፈርና ድንጋዮችን፣ መሬትን ከማጽዳት ወይም ከማዘጋጀት የተገኙ ጥራጊ እና አፈርን ያጠቃልላል።

ቆሻሻ ውሃ

በቤት ውስጥ፣ በኢንዱስትሪ፣ በንግድ ወይም በግብርና ዓላማዎች በሰው አጠቃቀም ምክንያት በጥራት ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳደረ ማንኛውም ውሃ።

በሥራ ቦታ ላይ የሚፈጸም ሁከትና ትንኮሳ

አንድ ጊዜ የተከሰተ ወይም ተደጋጋሚ የሆነ፣ አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊ፣ ወሲባዊ ወይም ኢኮኖሚያዊ ጉዳት የሚያስከትል ወይም ሊያስከትል የሚችል፣ እንዲሁም በሥርዓተ ፆታ ላይ የተመሰረተ ሁከትና ትንኮሳን የሚያካትት ተቀባይነት የሌላቸውን ምግባሮች እና ልምዶች ወይም ዛቻዎችን ያመለክታል።[25]

በሥርዓተ ፆታ ላይ የተመሰረተ አድልዎ

በጾታ ወይም በሥርዓተ ፆታ ማንነት ላይ ተመስርቶ የሚደረግ ማንኛውም ልዩነት፣ ማግለል ወይም ምርጫ በሥራ ወይም በሙያ ውስጥ ያለውን የእኩል ዕድል ወይም አያያዝን ዋጋ የሚያሳጣ ወይም የሚያበላሽ ውጤት ያለው። ይህ በሴቶች ላይ የሚደረግ አድልዎን ያካትታል ነገር ግን በእሱ ብቻ አይወሰንም።[26]

በሥርዓተ ፆታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት

በሰዎች ፆታ ወይም ሥርዓተ ጾታ ምክንያት በእነሱ ላይ የሚፈጸም፣ ወይም የተወሰነ ፆታ ወይም ሥርዓተ ጾታ ያላቸውን ሰዎች ባልተመጣጠነ ሁኔታ የሚጎዳ ጥቃትና ትንኮሳ ሲሆን፣ ጾታዊ ትንኮሳን ያካትታል።

በተባይ/በሽታ ምክንያት የሚደርስ የኢኮኖሚ ተጽዕኖ

በተወሰነ አካባቢ ውስጥ በተባይ/በሽታ መግባት፣ መስፈር ወይም መስፋፋት ምክንያት የሚመጡ እምቅ እና ትክክለኛ የኢኮኖሚ መዘዞች መጠን። ይህ በሰብል ምርት እና ምርታማነት ላይ መቀነስ፣ ከተጨማሪ ቁጥጥር እርምጃዎች የሚመጣ የምርት ወጪ መጨመር፣ የገበያ ተደራሽነት ገደቦች፣ የንግድ እንቅፋቶች፣ እና የግብርና ምርታማነትንና ትርፋማነትን የሚጎዳ የአካባቢ መበላሸትን ያካትታል።[27]

በክፍል የሚከፈል ሥራ

በሥራ ላይ በጠፋው ጊዜ ሳይሆን በተሠራው ክፍል ላይ ተመስርቶ የሚከፈል ሥራ።

በዘረመል የተቀየረ ህዋስ (GMO)

የዘረመል ቁሱ በተፈጥሮ በመጋባት እና/ወይም በተፈጥሯዊ ዳግም ውህደት ባልተከሰተ መንገድ የተለወጠ ህዋስ።

ቡድን

የጋራ የውስጥ አስተዳደር ሥርዓት (IMS) ያላቸው እና በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ሕጎች ስር በጋራ ሰርቲፋይድ የተደረጉ የተደራጁ አምራቾች ማህበር። የተደራጁ አምራቾች ቡድን በማህበር ወይም ህብረት ሥራ ማህበር ውስጥ ሊደራጅ ይችላል ወይም በአቅርቦት ሰንሰለት ተዋናይ (እንደ ላኪ) ወይም በሌላ ሕጋዊ ተቋም ሊተዳደር ይችላል።

ባዮሎጂካል ግብዓት

እንደ የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኮምፖስት)፣ ፍግ፣ ባዮ ማዳበሪያ፣ ባዮ ፀረ-ተባዮች፣ ረቂቅ ተህዋሲያን ኢኖኩላንቶች (ናይትሮጅን አስተካካይ ባክቴሪያዎች፣ ማይኮርራይዛል ፈንገሶች)፣ ወይም የአፈርን ለምነት ለማሻሻል፣ የእፅዋትን አመጋገብና እድገት ለመደገፍ፣ እና ተባዮችንና በሽታዎችን ለአካባቢ ዘላቂነት ባለው መንገድ ለማስተዳደር የሚያገለግሉ የእፅዋት ተዋፅዖዎች የመሳሰሉ ተፈጥሯዊ ንጥረ ነገሮች ወይም ሕያዋን ፍጥረታት።[28]

ቤተሰብ

ቤተሰብ በተለምዶ አብረው የሚኖሩ፣ የኑሮ ሁኔታዎችን የሚጋሩ እና ለዕለት ተዕለት ኑሮ ሀብቶችን የሚያዋህዱ አንድ ወይም ከዚያ በላይ ግለሰቦችን ያቀፈ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ አካል ነው። የቤተሰብ አባላት በደም ወይም በጋብቻ ሊዛመዱም ላይዛመዱም ይችላሉ። እነሱ በተለምዶ በመኖሪያው ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦችን እንዲሁም ለጊዜው በሌላ አካባቢ የሚኖሩ ጥገኞችን (ለምሳሌ ለትምህርት የወጡ ተማሪዎችን) ያካትታሉ። በተለምዶ አብረው የሚኖሩ እና ከቤተሰቡ ጋር ምግቦችን የሚካፈሉ ሠራተኞች ወይም የቤት ውስጥ ሠራተኞች ደግሞ እንደ አባላት ሊቆጠሩ ይችላሉ። የቤተሰብ ስብጥር በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ግላዊ ሁኔታዎች ምላሽ ለመስጠት ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊለወጥ ይችላል። ቤተሰቦች በወንዶች፣ በሴቶች ወይም በሕፃናት ሊመሩ ይችላሉ፤ ከእነዚህም ውስጥ የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ብዙውን ጊዜ ለበለጠ ተጋላጭነት እና የኢኮኖሚ ተግዳሮቶች ይጋለጣሉ።[29]

ብቃት ያለው ባለሙያ/ቴክኒሽያን

በተወሰነ የትምህርት ዘርፍ የተረጋገጠ የባለሙያ ዕውቀት፣ ክህሎት፣ ልምድ እና የምስክር ወረቀት ያለው ግለሰብ። እንደ ተባይ ማጥፊያ ለመርጨት አውሮፕላን ወይም ድሮን ማብረር ለመሳሰሉት ልዩ ቴክኒካዊ ተግባራት፣ ብቃት ያለው ባለሙያ/ቴክኒሽያን ተፈጻሚነት ባለው ብሔራዊ ባለሥልጣን ፈቃድ ወይም ሰርቲፊኬሽን የተሰጠው ሰው ነው።

ብዙ-ስፍራ

የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ወሰን ውስጥ እርሻ የሌለው እና ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ስፍራዎች የሚሠሩበት ማዕከላዊ አካባቢ ያለው ድርጅት።

ብዙ-እርሻ (Multi-farm)

ሰርቲፊኬሽን ምንም ይሁን ምን፣ ሥራዎቻቸውና የእርሻ ተግባራቸው በማዕከላዊነት የሚተዳደር፣ በአንድ ሕጋዊ ተቋም ባለቤትነት ሥር ያሉ ወይም የተከራዩ ሁለት ወይም ከዚያ በላይ እርሻዎች ናቸው።

ተረፈ ምርት

በግብርና ምርቶች መመረት፣ መሰናዳት ወይም ሥርጭት ጊዜ የሚመነጩ ሁለተኛ ደረጃ ውጤቶች ሲሆኑ፣ ዋነኛው ተፈላጊ ምርት ያልሆኑ ናቸው።[30]

ተቀጣሪ

የሚሠራው ሥራ እና የአፈጻጸሙ መንገድና ዘዴ ሁለቱም በኩባንያው ቁጥጥርና መመሪያ ሥር የሆነ፣ በኩባንያው ወይም በማንኛውም ተዛማጅ ሕጋዊ ተቋም የተቀጠረ ሰው[31]

ተቋቋሚ የዕፅዋት ዝርያ

ተባዮችንና በሽታዎችን መቋቋም፣ መከላከል ወይም ማባረር እና ጉዳት እንዳያደርሱ መከልከል የሚችሉ እጽዋት።  ተከላካይ ዝርያዎች የኬሚካል ተባይ መቆጣጠሪያ ፍላጎትን ይቀንሳሉ።[32]

ተባዮች

በእጽዋት፣ በእጽዋት ምርቶች ወይም በግብርና ምርት ላይ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል ማንኛውም የዕፅዋት ዝርያ (ለምሳሌ አረሞች)፣ የእንስሳት ዝርያ (ለምሳሌ ኔማቶዶች፣ ነፍሳት፣ አርቶፖዶች፣ ሮዳንትስ) ወይም በሽታ አምጪ ወኪል (ለምሳሌ ፈንገሶች፣ ባክቴሪያዎች፣ ቫይረሶች)። ተባዮች የሰብል ምርትን፣ ጥራትን ወይም ለገበያ የመቅረብ አቅምን ሊቀንሱ እና ሥነ-ምህዳራዊ ሚዛንን ሊያዛቡ ይችላሉ፣ ይህም እነሱን መቆጣጠር በዘላቂ ግብርና ውስጥ ግብርና ውስጥ መሠረታዊ ነው።[33]

ተዋናይ

በሰርቲፊኬሽኑ ወሰን ውስጥ ከማምረት እስከ መጨረሻው ምርት ድረስ ሰርቲፋይድ ከሆነው ምርት ጋር የተያያዙ ተግባራትን የሚያከናውን ማንኛውም ግለሰብ፣ ኩባንያ ወይም ድርጅት።[34]

ተገቢ ትጋት

አንድ ኩባንያ ከሁሉም አግባብነት ያላቸው ህጎች እና ደንቦች ጋር ተጠያቂነት ያለው ተገዢነትን ለማረጋገጥ እና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በአሠራሩ ወይም በአቅርቦት ሰንሰለቱ የሚፈጠሩ በአካባቢ ወይም በሰብአዊ መብቶች ላይ የሚከሰቱ አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ለማስወገድ መከተል ያለበት ቀጣይነት ያለው የስጋት አስተዳደር ሥርዓት። ተገቢ ትጋት የሚተገበረው በአንድ ኩባንያ አሠራሮች አሉታዊ የሰብአዊ መብት እና የአካባቢ ተፅዕኖዎችን እንዴት እንደሚፈታ ለመለየት፣ ለመከላከል፣ ለማቃለል እና ለመጠየቅ በሚያስችል ሂደት ነው። ይህ አራት ዋና ዋና ደረጃዎችን ያካትታል፦ ትክክለኛ እና እምቅ ተፅዕኖዎችን ግምገማ ማድረግ፣ ግኝቶችን ማዋሃድ እና በእነሱ ላይ እርምጃ መውሰድ፣ ምላሾችን መከታተል እና ተፅዕኖዎች እንዴት እንደተፈቱ መገናኘት።[35]

ተገዢነት

የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች መስፈርቶች መሟላታቸውን መወሰን።[36]

ተጋላጭ ቡድን

ከመደበኛው ህዝብ ይልቅ ከፍተኛ የድህነትና የማህበራዊ መገለል ስጋት የሚያጋጥማቸው ቡድኖች ናቸው። አናሳ ጎሳዎች፣ አገር በቀል ሰዎች፣ ስደተኞች፣ የአካል ጉዳተኞች፣ ብቸኛ አዛውንቶች፣ ሴቶች እና ሕፃናት እንደ ዝቅተኛ የትምህርት ደረጃ እና ሥራ አጥነት ወይም ያልተሟላ ሥራ መሥራት የመሳሰሉ ተጨማሪ ማኅበራዊ መገለል ሊያስከትሉ የሚችሉ ችግሮች ይገጥሟቸዋል።

ተጓዳኝ አምራች

ለንግድ ምርቶች ምርት ሲባል በአምራቾች ወይም በመሬት ባለቤቶች እና በአንድ ኩባንያ መካከል ያለ የውል ሽርክና።

ተጨማሪ ሰዓት

ከመደበኛ የሥራ ሰዓታት በላይ የተሰራ ሰዓት።

ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳር

በዝርያ ስብጥር፣ አወቃቀር እና ሥነ-ምህዳራዊ ተግባር ረገድ – ዋና ዋና የሰው ልጆች ተጽዕኖ በሌለበት በተሰጠው አካባቢ ውስጥ ከሚገኘው ወይም ከሚገኝ ሥነ-ምህዳር ጋር – በእጅጉ የሚመሳሰል ሥነ-ምህዳር ነው። ይህ አብዛኛው የተፈጥሮ ዝርያ ስብጥር፣ አወቃቀር እና ሥነ-ምህዳራዊ ተግባር የሚገኝባቸው በሰው የሚተዳደሩ ሥነ-ምህዳሮችን ያጠቃልላል። ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳሮች ሁሉንም ተፈጥሯዊ የምድር ሥነ-ምህዳሮችን (ተፈጥሯዊ ደኖችን፣ ደንማ መሬቶችን፣ ቁጥቋጦማ መሬቶችን፣ ሳቫናዎችን፣ የሣር ሜዳዎችን እና ፓራሞዎችን ጨምሮ) እና ሁሉንም ተፈጥሯዊ የውሃ ሥነ-ምህዳሮችን ያካትታሉ።

ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳሮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • በቅርብ ጊዜ ታሪክ ውስጥ ለዋና ዋና የሰው ልጆች ተጽዕኖ ያልተገዙ በብዛት "ንፁህ" የሆኑ ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳሮች

  • በጥንት ጊዜ ለዋና ዋና ተጽዕኖዎች የተጋለጡ (ለምሳሌ በግብርና፣ በእንስሳት እርባታ፣ በዛፍ ተከላ ወይም በከፍተኛ የእንጨት ቁርጥ) ነገር ግን የዋና ዋና ተጽዕኖዎች መንስኤዎች ያቆሙ ወይም በእጅጉ የቀነሱ እና የሥነ-ምህዳሩ የዝርያ ስብጥር፣ አወቃቀር እና ሥነ-ምህዳራዊ ተግባር ቀደም ሲል ከነበሩት ወይም ከሌሎች ወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳሮች ጋር ተመሳሳይነት ያገኙ እንደገና የታደሱ ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳሮች

  • አብዛኛው የሥነ-ምህዳሩ ስብጥር፣ አወቃቀር እና ሥነ-ምህዳራዊ ተግባር የሚገኝባቸው የተዳደሩ ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳሮች (እንደ "ከፊል-ተፈጥሯዊ" ተብለው ሊጠቀሱ የሚችሉ ብዙ ሥነ-ምህዳሮችን ጨምሮ)፤ ይህ ደግሞ የሚተዳደሩ ተፈጥሯዊ ደኖችን እንዲሁም በአሁን ጊዜ ወይም በታሪክ በእንስሳት የተጋጡ ሀገር በቀል የሣር ሜዳዎችን ወይም የግጦሽ መሬቶችን ያጠቃልላል።

በሰው ሰራሽ ወይም በተፈጥሮ ምክንያቶች (ለምሳሌ ማጨድ፣ እሳት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ወራሪ ዝርያዎች ወይም ሌሎች) በከፊል የተጎዱ ነገር ግን መሬቱ ወደ ሌላ አጠቃቀም ያልተለወጠ እና አብዛኛው የሥነ-ምህዳሩ ስብጥር፣ አወቃቀር እና ሥነ-ምህዳራዊ ተግባር አሁንም የሚገኝ ወይም በተፈጥሮ ወይም ለሥነ-ምህዳር መልሶ ማቋቋም በአስተዳደር እንደሚታደስ የሚጠበቅባቸው ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳሮች[37]

ተፈጥሯዊ እፅዋት

በዋናነት ከአገር በቀል ወይም በአካባቢው ተስማሚ ከሆኑ ዝርያዎች የተዋቀረ፣ የዝርያ ስብጥሩና አወቃቀሩ የሰው ጣልቃ ገብነት በሌለበት ሁኔታ በአካባቢው ያለውን ወይም ሊኖር የሚችለውን ዕፅዋት የሚመስል ነው። የተፈጥሯዊ እፅዋት መሬቱን መልሶ ለማደስ፣ ሥርዓተ-ምህዳሩን ከአሁን ወይም ከወደፊቱ የአየር ንብረት ጋር ለማላመድ፣ እና/ወይም የብዝሃ ሕይወትን ለማሳደግ ጠቃሚ ከሆኑ፣ አነስተኛ መጠን ያላቸውን ባዕድ ዝርያዎችን ለማካተት ሊተዳደር (ወይም በተሃድሶ ሁኔታ መልሶ ሊቋቋም) ይችላል። ወራሪ ዝርያዎች ካሉ፣ መገኘታቸውን ለመቀነስ እንዲቻል የተፈጥሮ ዕፅዋት ቁጥጥር ይደረግበታል።

ተፈጥሯዊ ደኖች

ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳሮች የሆኑ እና ለተሰጠው ስፍራ ሀገር በቀል የሆነ ደን የሆኑትን ብዙ ወይም አብዛኞቹን ባህሪያት የሚይዙ ደኖች፣ ይህም የዝርያ ስብጥርን፣ አወቃቀርን እና ሥነ-ምህዳራዊ ተግባርን ያካትታል። ተፈጥሯዊ ደኖች የሚከተሉትን ያካትታሉ፦

  • በቅርብ ጊዜ ታሪክ ውስጥ ለዋና ዋና የሰው ልጆች ተጽዕኖ ያልተገዙ ዋና ደኖች።

  • በጥንት ጊዜ ለዋና ዋና ተጽዕኖዎች የተጋለጡ (ለምሳሌ በግብርና፣ በእንስሳት እርባታ፣ በዛፍ ተከላ ወይም በከፍተኛ የእንጨት ቁርጥ) ነገር ግን የዋና ዋና ተጽዕኖዎች መንስኤዎች ያቆሙ ወይም በእጅጉ የቀነሱ እና የሥነ-ምህዳሩ አብዛኛውን የዝርያ ስብጥር፣ አወቃቀር እና ሥነ-ምህዳራዊ ተግባር ከቀደምት ወይም ከሌሎች ወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሥነ-ምህዳሮች ጋር ተመሳሳይነት ያገኘ እንደገና የታደሱ (ሁለተኛ እድገት) ደኖች።

  • እንደሚከተሉት ባሉ ተግባራት ፊት አብዛኛው የሥነ-ምህዳሩ ስብጥር፣ አወቃቀር እና ሥነ-ምህዳራዊ ተግባር የሚገኝባቸው የተዳደሩ ተፈጥሯዊ ደኖች፦

    1. የእንጨት ወይም የሌሎች የደን ምርቶች ማጨድ፣ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸውን ዝርያዎች ለማሳደግ የሚደረግ አስተዳደርን ጨምሮ።

    2. እንደ ዝቅተኛ-ጥንካሬ ያለው የማቃጠልና የማልማት ግብርና (swidden agriculture) በደን ቅብብል ውስጥ እንደሚታየው፣ በደን ውስጥ ያለ ዝቅተኛ-ጥንካሬ እና አነስተኛ-ልኬት ያለው እርሻ።

  • በሰው ሰራሽ ወይም በተፈጥሮ ምክንያቶች (ለምሳሌ ማጨድ፣ እሳት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣ ወራሪ ዝርያዎች ወይም ሌሎች) በከፊል የተጎዱ ነገር ግን መሬቱ ወደ ሌላ አጠቃቀም ያልተለወጠ እና መጎዳቱ የዛፍ ሽፋንን ከደን መለያ ወሰን በታች ዘላቂ ቅናሽ ወይም የሌሎች ዋና ዋና የሥነ-ምህዳር ስብጥር፣ አወቃቀር እና ሥነ-ምህዳራዊ ተግባር ዘላቂ ኪሳራ የማያስከትልባቸው ደኖች።

ተፈጥሯዊ ደኖች ከፍተኛ የካርቦን ክምችት አቀራረብ (HCSA) ዘዴን በመጠቀም ሊለዩ ይችላሉ፤ በአጠቃላይ የHCSA የመሬት-ሽፋን ምድቦች ከፍተኛ ጥቅጥቅ ደኖች (HDF)፣ መካከለኛ ጥቅጥቅ ደኖች (MDF)፣ ዝቅተኛ ጥቅጥቅ ደኖች (LDF) እና አዲስ እድገት (YR) ሁሉም እንደ የተፈጥሯዊ ደን ዓይነቶች ይቆጠራሉ።[38]

ተፈጻሚነት ያለው ህግ

በተወሰነ አውድ ወይም ሁኔታ ውስጥ ተፈጻሚነት ያላቸው ብሔራዊ እና የፀደቁ ዓለም አቀፍ ህጎች። ብሔራዊ ህጎች በአንድ አገር ውስጥ ባሉ ሁሉም የሕግ ግዛቶች (አካባቢያዊ፣ ክልላዊ እና ብሔራዊ) ህጎችን እና ደንቦችን ያካትታል። አገራት የተቀላቀሏቸው ዓለም አቀፍ ህጎችም እንደ ተፈጻሚነት ያለው ህግ ይቆጠራሉ።[39]

ታዳሽ ኃይል

ለምሳሌ ያህል ውስን አቅርቦት ካለው ቅሪተ አካል ነዳጅ በተለየ መልኩ፣ መሠረታዊ በሆነ መንገድ የማይሟጠጡ ከሆኑ ምንጮች የሚገኝ ኃይል።  ታዳሽ የኃይል ምንጮች እንጨት፣ ቆሻሻ፣ የከርሰ ምድር ሙቀት፣ ንፋስ፣ ፎቶቮልቲክ እና የፀሐይ ሙቀት ኃይልን ያካትታሉ[40]

ታጋሽ የእፅዋት ዝርያ

ተባዩ ወይም በሽታ አምጪው ተህዋሲው በእጽዋቱ ወይም በእርሻው ውስጥ ቢኖርም እንኳን፣ የምርት ወይም የጥራት ጉድለት ሳይደርስበት ተባዮችን፣ በሽታዎችን ወይም የአካባቢ ጭንቀቶችን ሊቋቋም የሚችል እጽዋት። ምንም እንኳን አንዳንድ ጉዳት ሊከሰት ቢችልም፣ እፅዋቱ ተቀባይነት ያለው አፈጻጸም ይዞ ይቆያል፣ ይህም ለዘላቂ የሰብል አያያዝ እንዲኖር አስተዋፅኦ ያደርጋል እና በኬሚካል ቁጥጥር እርምጃዎች ላይ ጥገኝነትን ይቀንሳል።

ትልቅ እርሻ

10 ወይም ከዚያ በላይ ቋሚ ሠራተኞች ያለሏቸው ሁሉም እርሻዎች። ትላልቅ እርሻዎች በግል ወይም እንደ የቡድን አካል ሆነው ሰርቲፋይድ ሊሆኑ ይችላሉ።

ትነት

እንደ ማዳበሪያ ውስጥ ያለ ንጥረ ነገር (በተለምዶ ናይትሮጅን በአሞኒያ ወይም ዩሪያ መልክ) ወይም የተወሰኑ ፀረ-ተባዮች ወደ ጋዝ ቅርጽ ተለውጠው ወደ ከባቢ አየር የሚጠፉበት ሂደት። ይህ ሂደት የንጥረ ነገር አጠቃቀም ብቃትን እና የሰብል መዋሃድን ሊቀንስ፣ የፀረ-ተባይ ውጤታማነትን ሊቀንስ እና እንደ የአየር ብክለት፣ የግሪንሃውስ ጋዝ ልቀቶች እና የኬሚካል መበታተን ለመሳሰሉት የአካባቢ ችግሮች አስተዋፅኦ ሊያደርግ ይችላል።[41]

ነባር ሕዝቦች እና የአካባቢው ማህበረሰቦች

በብዛት ተቀባይነት ካገኙት የነባር ሕዝቦች ትርጓሜዎች ውስጥ አንዱን የሚያሟሉ የተለዩ የሰዎች ስብስቦች ሲሆኑ፣ (ከሌሎች ምክንያቶች በተጨማሪ) የሚከተለውን ቡድን ከግምት ውስጥ ያስገባሉ፦[42]

  • በተሰጠው ማህበራዊ-ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ እና ታሪካዊ አውድ ውስጥ የራሱን የሰው ልማት ጽንሰ ሐሳብ እና መንገድ ተከትሏል።

  • የተለየ የቡድን ማንነት፣ ቋንቋዎች፣ ባህላዊ እምነቶች፣ ልማዶች፣ ህጎች እና ተቋማት፣ የዓለም እይታዎች እና የኑሮ ዘዴዎችን ለመጠበቅ ሞክሯል።

  • በአንድ ወቅት በታሪክ የተጠቀመባቸውና የያዛቸው፣ ልዩ ግንኙነት ያለበት እና አካላዊና ባህላዊ ሕልውናው በአብዛኛው የተመካባቸው መሬቶች፣ ተፈጥሯዊ ሀብቶች እና ግዛቶች ላይ ቁጥጥርና አስተዳደር ነበረው።

  • ራሱን እንደ ነባር ሕዝቦች አድርጎ ይለያል።

  • ከቅኝ ግዛት በፊት የነበረ ህልውናው መሬቶች ውስጥ ከነበሩት ሕዝቦች ወይም በኋላ ከተፈናቀሉ ሕዝቦች የተወለደ ነው።

ለሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች ዓላማ፣ ይህ ትርጉም ከነባር ሕዝቦች ጋር ቁልፍ ባህሪያትን የሚጋሩ ሌሎች የአካባቢው ማህበረሰቦችን ያካትታል፣ ለምሳሌ፦

  • መሬት እና የተፈጥሮ ሀብቶችን እንደ ባህል፣ ልማዶች፣ ታሪክ እና የማንነት ምንጮች አድርጎ መውሰድ።

  • የባህል እና አካላዊ ህልውናቸው ሲባል በመሬት እና በተፈጥሮ ሀብቶች ላይ መመካት፣ ይህም የመተዳደሪያ ዘዴዎች፣ ማህበራዊ ድርጅት፣ ባህል፣ ወጎች እና እምነቶችን ያካትታል።

  • የመሬት ይዞታ ሥርዓቶችን ተከትለው መሬትን መጠቀምና ማስተዳደር፣ ይህም በግዛት ባለሥልጣናት በይፋ እውቅና የተሰጣቸው ወይም ያልተሰጣቸው ሊሆን ይችላል።

ነጻ፣ ቅድሚያ እና በመረጃ የተደገፈ ፈቃድ (FPIC)

ነባር ሕዝቦች እና ሌሎች የአካባቢው ማህበረሰቦች መሬታቸውን እና ሀብታቸውን ስለመጠቀም ወይም ስለማልማት በነጻ እና በመረጃ የተደገፈ ምርጫ የማድረግ መብት። FPIC የሚተገበረው ማንኛውም የልማት ዕቅድ ከመጠናቀቁ ወይም ከመተግበሩ በፊት በሚካሄድ እና ሁሉንም የተጎዱ ቡድኖችን በሚያካትት የተሳትፎ ሂደት ነው። የFPIC ሥርዓት ማህበረሰቦች በግዳጅ ወይም በማስፈራራት ውስጥ አለመግባታቸውን ያረጋግጣል፤ ውሳኔዎች የሚወሰኑት በማህበረሰቦች በተመረጡት ተቋማት ወይም ወኪሎች አማካኝነት ነው፤ ማንኛውም እንቅስቃሴ ከመፈቀዱ ወይም ከመጀመሩ በፊት የማህበረሰቦች ፈቃድ ይፈለጋል እና በነጻ ይሰጣል፤ ማህበረሰቦች ስለታቀደው ልማት ወሰን እና በመሬታቸው፣ በመተዳደሪያ ዘዴዎቻቸው እና በአካባቢያቸው ላይ ስለሚኖረው ተጽዕኖ ሙሉ መረጃ አላቸው፤ እና በመጨረሻም ፈቃድ ለመስጠት ወይም ለመከልከል ያላቸው ምርጫ ይከበራል።[43]

ናይትሮጅን አስተካካይ ዛፎች

በከባቢ አየር ውስጥ ያለውን ናይትሮጅን እፅዋት ሊጠቀሙበት ወደሚችሉበት ቅርጽ መለወጥ የሚችሉ ዛፎች። ይህ ሂደት አፈርን ያበለጽጋል፣ የሌሎች እፅዋትን እድገት ይደግፋል እንዲሁም የሰው ሠራሽ ማዳበሪያዎችን አስፈላጊነት ይቀንሳል። የናይትሮጅን አስተካካይ ዛፎች ምሳሌዎች የጥራጥሬ የዛፍ ዝርያዎች ናቸው።[44]

ንቁ ንጥረ ነገር

በአንድ ፀረ-ተባይ ምርት ውስጥ የሚገኝ፣ ተባይን ሊገድል፣ ሊያስወግድ፣ ሊስብ፣ ሊቀንስ ወይም በሌላ መንገድ ሊቆጣጠር የሚችል የፀረ-ተባይ ተግባርን የሚሰጥ ንጥረ ነገር ወይም የንጥረ ነገሮች ድብልቅ። ሌሎች የቦዘኑ ንጥረ ነገሮች ይህንን ውጤት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊያግዙ ይችላሉ ንቁ ንጥረ ነገሮች በፀረ-ተባይ ምርቱ መለያ ላይ በስም ተለይተው ተቀምጠዋል።[45]

ንዑስ ኮንትራክተር

በሰርቲፋይድ ምርቶች ላይ አንድ ወይም ከዚያ በላይ የተወሰኑ አሠራሮችን ለማከናወን የተዋዋለ ድርጅት ወይም ግለሰብ፣ ለምሳሌ ምርቶችን ማቀነባበር፣ ማከማቸት፣ ማሸግ እና/ወይም ለምርቶች መለያ መስጠት።

ንፅህና፣ ጤና ጥበቃ

የሰውን ሰገራ በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጣል የሚያገለግሉ መገልገያዎችና አገልግሎቶች አቅርቦት። “ንጽህና አጠባበቅ” የሚለው ቃል ደግሞ እንደ ቆሻሻ አሰባሰብ እና የቆሻሻ ውኃ ማስወገጃ ባሉ አገልግሎቶች አማካኝነት ንጽህና የሰፈነባቸው ሁኔታዎችን መጠበቅን ያመለክታል።[46]

አመላካች

ከሥርዓቱ፣ ከደንበኞቹ ወይም ከሁለቱም ጋር የተያያዙ ለውጦችን እና አፈጻጸምን ለመከታተል እና ለመረዳት የሚያስችል የፍላጎት መጠናዊ ወይም ጥራት ያለው ነገር ወይም ተለዋዋጭ[47]

አምራች

ንግድ ነክ በሆነ መንገድ ወይም ራሱንና ቤተሰቡን ለመደጎም የግብርና ድርጅት የሚይዝ እና/ወይም የሚያንቀሳቅስ ሰው (ወንድ ወይም ሴት)።

አስተዳደራዊ ያልሆነ ሠራተኛ

በእርሻው/ሜዳው ወይም በሌሎች የእርሻ ስፍራዎች (ችግኝ ማፍያ፣ ማቀነባበሪያ ክፍል፣ የግዢ ማዕከሎች፣ መጋዘኖች፣ ወዘተ) አካላዊ ሥራዎችን የሚያከናውኑ ሠራተኞች እና እንደ የጥበቃ ሠራተኞች፣ ሾፌሮች፣ የጽዳት ሠራተኞች፣ ምግብ አብሳዮች፣ አትክልተኞች እና አጠቃላይ ሠራተኞች ሆነው የሚሰሩ ናቸው። በቢሮ ውስጥ ሥራቸውን የሚያከናውኑ ሠራተኞችን፣ የውስጥ ኢንስፔክተሮችን ወይም በሜዳ/ማቀነባበሪያ ክፍሎች ውስጥ ተቆጣጣሪዎች ሆነው ሥልጣን ያላቸውን አያካትትም።

አረም ማጥፊያ

የግብርና ሰብሎችን ሳይጎዱ፣ እንደ አረም እና ወራሪ ዝርያዎች ያሉ የማይፈለጉ እፅዋትን እድገት ለማጥፋት ወይም ለመግታት የተነደፉ ኬሚካላዊ ወይም ባዮሎጂያዊ ንጥረ ነገሮች።[48]

አቅራቢ

ለሌላ አካል ሸቀጦችን ወይም አገልግሎቶችን የሚያቀርብ ግለሰብ፣ ኩባንያ ወይም ድርጅት። አቅራቢዎች ለደንበኞቻቸው የሚጠበቁትን ቁሳቁሶች፣ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች መኖራቸውን በማረጋገጥ በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ።

አነስተኛ ለውጥ

በተሰጠው ቦታ አውድ ውስጥ ግዙፍ ያልሆነ በትንሽ ስፋቱ ምክንያት እና በተፈጥሮ ሥርዓተ-ምህዳሮች የጥበቃ እሴቶች ወይም ለሰዎች በሚሰጡት አገልግሎቶችና እሴቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ የማያስከትል አነስተኛ ለውጥ ነው።[49]

አነስተኛ ስጋት

የመከሰት እድሉ እጅግ በጣም ዝቅተኛ የሆነ እና ቢከሰትም በዓላማዎች ላይ አነስተኛ ተጽዕኖ የሚኖረው ስጋት። ይህ ዓይነቱ ስጋት ብዙውን ጊዜ ችላ ሊባል የሚችል እንደሆነ የሚታሰብ ሲሆን፣ ሰፊ የአስተዳደር ወይም የጉዳት ቅነሳ ጥረቶች አያስፈልገውም።[50]

አነስተኛ እርሻ

ከ10 ቋሚ ሠራተኞች በታች ያሉት ሁሉም እርሻዎች። አነስተኛ እርሻዎች በተናጠል ወይም የቡድን አካል ሆነው ሰርቲፋይድ ሊሆኑ ይችላሉ።

አደን

ለምግብ፣ ለስፖርት ወይም ለትርፍ እንስሳትን ማሳደድ እና መግደል።

አደገኛ ቁሳቁሶች

በሰዎች ወይም በአካባቢ ላይ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ ቁሳቁሶች። እነዚህም ያገለገሉ የሊድ አሲድ ባትሪዎች፣ አስቤስቶስ፣ ኃይል ቆጣቢ የሜርኩሪ መብራቶች፣ ኤሌክትሮኒክ ቆሻሻ፣ በፒኦፒኤስ (POPs - PCBs) የተበከሉ የኤሌክትሪክ ትራንስፎርመሮች፣ የሕክምና መሳሪያዎች፣ ሬዲዮአክቲቭ ቁስ፣ ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች፣ ጊዜያቸው ያለፈባቸው የሰውና የእንስሳት መድኃኒቶች፣ ያገለገሉ ዘይቶች፣ በሽታ አምጪ ባዮሎጂያዊ ቆሻሻ፣ ፀረ-ተህዋስያን/ማምከኛ፣ የእንስሳት ክፍሎችና ሬሳዎች፣ እና ቅንጣቶች (አመድ፣ አቧራ፣ የፀረ-ተባይ መርጨት ፍንጣቂዎች) ይገኙበታል።

አደጋ

በአንድ ሰው ወይም በሰዎች ላይ ጉዳት ወይም አሉታዊ የጤና ተጽዕኖ ሊያስከትል የሚችል እምቅ ምንጭ። የተለያዩ የአደጋ ዓይነቶች አሉ፤ እነዚህም 'አካላዊ አደጋዎች' (ለምሳሌ መውደቅ ወይም መሰናከል የሚያስከትሉ አደጋዎች፣ እሳት፣ ሙቅ ዕቃዎች ጋር መሥራት፣ ወይም በጥሩ ሁኔታ ያልተጠበቁ መሣሪያዎችን መጠቀም) ወይም 'የጤና አደጋዎች' (ለምሳሌ ጫጫታ፣ ንዝረት፣ የማይመች የብርሃን ደረጃ፣ ጎጂ አቧራ ወይም ውጥረት) ወይም 'ኬሚካላዊ አደጋዎች' (ለምሳሌ ከጽዳት ወኪሎች፣ ሙጫዎች እስከ ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች ያሉ ምርቶች ጋር መሥራት) ይገኙበታል።

አደጋ ላይ ያሉ እንስሳትና እፅዋት

በብሔራዊ ሕጎች ወይም ምደባ ሥርዓቶች አደጋ ላይ እንደሆኑ ወይም የመጥፋት አደጋ ላይ እንደሆኑ የተሰየሙ ዝርያዎች እና/ወይም በIUCN አደጋ ላይ ያሉ ዝርያዎች ቀይ ዝርዝር ላይ በከፍተኛ አደጋ፣ በአደጋ ላይ ወይም በቀላሉ ተጋላጭ ተብለው የተሰየሙ እና/ወይም በዓለም አቀፍ የዱር እንስሳት እና ዕፅዋት አደጋ ላይ ያሉ ዝርያዎች ንግድ ስምምነት (CITES) አባሪዎች I፣ II ወይም III ላይ የተዘረዘሩ ዝርያዎች ናቸው።

አድልዎ

በዘር፣ በቀለም፣ በጎሳ፣ በሥርዓተ ጾታ፣ በጾታዊ ዝንባሌ፣ በሃይማኖት፣ በፖለቲካዊ አስተያየት፣ በብሔር አመጣጥ ወይም በማህበራዊ ደረጃ እና በሌሎችም ላይ በመመሥረት የሚደረግ ማንኛውም ልዩነት፣ ማግለል ወይም ምርጫ በቅጥር ወይም በሥራ ላይ ያለውን የእኩል እድል ወይም የአያያዝ እኩልነትን ዋጋ የሚያሳጣ ወይም የሚያበላሽ ውጤት ያለው።[51] የአድልዎ ድርጊቶች ለእኩል ሥራ እኩል ያልሆነ ክፍያ መፈጸም፣ የተሻለ ደመወዝ ለሚከፈልባቸው ሥራዎች እና የአስተዳደር ቦታዎች እኩል ያልሆነ ተደራሽነት፣ የቅጥር ሂደት ላይ ወይም በሥራ ሂደት ውስጥ በሌላ በማንኛውም ጊዜ በግዳጅ የሚደረግ የእርግዝና ምርመራ ያካትታሉ ነገር ግን በእነዚህ ብቻ አይወሰኑም።[52]

አገልግሎት አቅራቢ

በእርሻው አካላዊ ወሰኖች ውስጥ፣ በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ወሰን ውስጥ የተካተቱ የተወሰኑ ተግባራትን ለማከናወን በእርሻ አስተዳደር ወይም በአምራች የተዋዋለ ድርጅት ወይም ግለሰብ። በትርጉሙ መሠረት፣ አገልግሎት አቅራቢዎች የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ምርት ህጋዊ ባለቤትነትን አይወስዱም።

አግሮኬሚካሎች

በግብርና ምርት ውስጥ ጥቅም ላይ የሚውሉ በንግድ የሚመረቱ፣ ብዙውን ጊዜ ሰው ሰራሽ የሆኑ ኬሚካላዊ ንጥረ ነገሮች፣ ለምሳሌ እንደ ማዳበሪያዎች፣ ፀረ-ተባዮች፣ የእድገት መቆጣጠሪያዎች፣ ፀረ-ናማቶዶች እና የአፈር ማስተካከያዎች። አግሮኬሚካሎች በሰው ጤና እና በአካባቢ ላይ ሊያስከትሉ በሚችሉት ተፅዕኖ ምክንያት ቁጥጥር ይደረግባቸዋል።[53]

አጥንት ያለው እንስሳ

አጥንት ወይም አከርካሪ ያለው ህዋስ ሲሆን፣ አጥቢ እንስሳትን፣ ወፎችን፣ ተሳቢዎችን፣ አምፊቢያዎችን እና ዓሳዎችን ያካትታል።

አፈር መሸፈን

የአፈርን እርጥበት ለመጠበቅ፣ የአፈርን ሙቀት ለመቆጣጠር፣ የአረም እድገትን ለመግታት፣ የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል እና የአፈርን አወቃቀር እና ማይክሮባዊ እንቅስቃሴን በማሳደግ የአፈርን ጤና ለማሻሻል የአፈርን ወለል ኦርጋኒክ ወይም ኦርጋኒክ ባልሆኑ ይዘቶች የመሸፈን ተግባር ነው። አንዳንድ ኦርጋኒክ የሽፋን ምሳሌዎች እንደ የሰብል ቅሪቶች፣ ገለባዎች፣ ቅጠሎች፣ የሣር ቅንጣቶች ወይም የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኮምፖስት) ያሉ ሕይወት ያላቸው ወይም የሚበሰበሱ እፅዋትን ያካትታሉ።[54]

ኤሌክትሪክ

በአጠቃላይ ኃይልን ወደ አገልግሎቶች (እንደ መብራት፣ ማሞቂያ፣ መጓጓዣ እና ለመሣሪያዎች ኃይል መስጠት) ለመለወጥ የበለጠ ጠቃሚ በሆነ መልኩ የኤሌክትሪክ ክፍያዎች ፍሰት የያዘ የኃይል ዓይነት።[55]

እርሻ

በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ተፈጻሚነት ባለው የእርሻ ጂኦግራፊያዊ ወሰን ውስጥ ለግብርና ምርት እና ማቀነባበሪያ ተግባራት የሚያገለግሉ ሁሉም መሬቶች እና መገልገያዎች። እርሻ በጋራ አስተዳደር አካል ስር እስከሆኑ ድረስ በአንድ አገር ውስጥ ያሉ በርካታ ጎረቤት ወይም በጂኦግራፊያዊ ሁኔታ የተለያዩ የእርሻ ክፍሎችን ሊያካትት ይችላል።  

ኦርጋኒክ ማዳበሪያ

የእፅዋት ንጥረ ነገሮችን የያዙ እና እንደ ማዳበሪያ የሚያገለግሉ ከእፅዋት ወይም ከእንስሳት ምንጮች የተገኙ ንጥረ ነገሮች። ምሳሌዎች የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኮምፖስት)፣ ፍግ፣ አተር እና ጭቃማ ፍሳሽ ያካትታሉ።[56]

ኦርጋኒክ ያልሆኑ ማዳበሪያዎች

በዋናነት ከኦርጋኒክ ያልሆኑ ኬሚካላዊ ውህዶች እና/ወይም ማዕድናት ተዘጋጅተው የሚገኙ ሰው ሠራሽ ወይም ሴንቴቲክ ንጥረ ነገሮች ናቸው። እንደ ናይትሮጅን፣ ፎስፈረስ እና ፖታሲየም ያሉ አስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን በቀጥታ ለሰብሎች እና ለአፈር ይሰጣሉ።[57]

ኦዲት

የሰርቲፊኬሽን መስፈርቶች ምን ያህል እንደተሟሉ ለመወሰን ማስረጃዎችን ለማግኘት እና በተጨባጭ ለመገምገም ስልታዊ፣ ገለልተኛ እና በሰነድ የተደገፈ ሂደት።[58]

ከመከር በፊት ያለው የጊዜ ልዩነት

የመጨረሻው ፀረ-ተባይ አተገባበር እና የተያዙት ሰብሎች ወይም በተያዘው አካባቢ ውስጥ የተፈቀደው መከር መካከል ያለው ጊዜ። ይህ ልዩነት በተተገበረው ፀረ-ተባይ መሰረት ይለያያል።

ከማቀነባበሪያ አሠራሮች የሚወጣ ቆሻሻ ውሃ

እንደ ወፍጮ ቤቶች (ለምሳሌ የቡና እርጥብ ወፍጮዎች፣ የዘንባባ ዘይት ወፍጮዎች፣ የሸንኮራ አገዳ ወፍጮዎች)፣ የማጠብ ሥራዎች ወይም የማሸጊያ ወይም የማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች (እንደ ጭማቂ ወይም የፈሳሽ ምግብ ፋብሪካዎች) ባሉ የማቀነባበር ሥራዎች ምክንያት ጥራቱ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያደረበት ውኃ።

ከትግበራ ውጭ የሆነ ቀጠና

ፀረ-ተባይ መድኃኒቶች የማይተገበሩበት አካባቢ። በሜትር ያለው ርቀት ከትግበራ ውጭ የሆነውን ቀጠና ስፋት ያመለክታል፣ ይህም ፀረ-ተባዩ በሚረጭበት ዘዴ ላይ ተመስርቶ እንደሚከተለው ይለያያል:

  1. በሜካኒካል፣ በእጅ-እገዛ እና በታለመለት የአተገባበር ዘዴዎች ለሚረጩ ፀረ-ተባዮች 5 ሜትር፣ ለምሳሌ በጀርባ ተይዞ የሚረጭ፡ ባንዲንግ፣ ማጥመጃ ማስቀመጥ፣ የተወሰነ የፍርፋሪ ምደባ፣ አፈር ወይም ተክል ውስጥ መርፌ፣ የዘር ሕክምናዎች፣ እና አረም መጥረግ።

  2. በስርጭት ወይም በግፊት በሚረጩ ዘዴዎች ለሚረጩ ፀረ-ተባዮች 10 ሜትር፣ ለምሳሌየመሳሪያውን ቴክኒካዊ ዝርዝሮች መሠረት በማድረግ ሞተራይዝድ ረጪዎችን ወይም ስፕሬይ ቡሞችን፣ የአየር ግፊት ረጪዎችን ወይ ፎገሮችን (እጅግ ዝቅተኛ መጠን ያለው በጭጋጋ መልኩ የሚረጭ ማሽን) ያጠቃልላሉ።

ከንብረት ውጪ ያለ መኖርያ ቤት

በጊዜያዊ ሠራተኞች ለጊዜያዊ ሥራቸው የሚጠቀሙበት የመኖሪያ ቤት ሲሆን፣ በእርሻው የግድ የማይቀርብ (ለምሳሌ፣ ይፋዊ እና ይፋዊ ያልሆኑ የድንኳን መጠለያዎች፣ ከሜዳው አጠገብ ያሉ የጋራ ማረፊያዎች)።

ከንከኪ ነጻ የሆነ አካባቢ

አግባብ ባላቸው ባለሥልጣናት የተጠቆመ፣ ከተወሰነ ጥበቃ የሚደረግለት አካባቢ ጋር የተያያዙ ዳርቻ አካባቢዎች ሲሆኑ፣ ባለሥልጣናቱ ጥበቃ የሚደረግለት አካባቢን የጥበቃ ዋጋ ለማሳደግ የአካባቢ ሀብቶች አጠቃቀም ላይ ገደቦችን እና/ወይም ልዩ የልማት እርምጃዎችን የሚወስዱባቸው ናቸው።

ከአየር ንብረት ጋር የሚስማማ ግብርና

ከተወሰነ የእርሻ ማህበረሰብ የአየር ንብረት ለውጥ ለሚመጡ ልዩ ችግሮች ለመፍታት የተዋሃዱ የተለያዩ ዘላቂነት ያላቸው ዘዴዎች ጥምረት። ይህ በሦስት ዋና ምሰሶዎች የተዋቀረ ነው፦

  • ዘላቂነት ባለው መንገድ የግብርና ምርታማነትን እና ገቢዎችን መጨመር።

  • ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር መላመድ እና የመቋቋም አቅምን መገንባት።

  • የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀቶችን መቀነስ እና/ወይም ማስወገድ፣ በሚቻልበት ቦታ።[59]

ከደን ጭፍጨፋ የጸዳ

የደን ጭፍጨፋ ምክንያት ያልሆነ ወይም አስተዋፅዖ ያላደረገ ምርት።[60]

ከፍተኛ የተረፈ ምርት ደረጃ (MRLs)

በምግብ ምርት ላይ ወይም ውስጥ እንዲኖር በህግ የተፈቀደው የፀረ-ተባይ ወይም የኬሚካል ተረፈ ምርት ከፍተኛ ክምችት። MRLs የፀረ-ተባይ መድኃኒቶች ትክክለኛ እና አስተማማኝ አጠቃቀም አመላካች ሆነው ያገለግላሉ፣ ይህም የሸማቾችን ደህንነት ማረጋገጥ፣ ዓለም አቀፍ ንግድን ማመቻቸት፣ እና ተቆጣጣሪዎች የፀረ-ተባይ ደንቦችን መከበር እንዲከታተሉ ይረዳል።[61]

ከፍተኛ የጥበቃ ዋጋ (HCV)

በብሔራዊ፣ በክልላዊ ወይም በአለምአቀፍ ደረጃ እጅግ በጣም አስፈላጊ ወይም ወሳኝ እንደሆኑ የሚታሰቡ ባዮሎጂካል፣ ሥነ-ምህዳራዊ፣ ማህበራዊ ወይም ባህላዊ እሴቶች፦

HCV1፦ በዓለም አቀፍ፣ በክልላዊ ወይም በብሔራዊ ደረጃዎች አስፈላጊ የሆኑ የባዮሎጂያዊ ልዩነት ስብስቦች ሲሆኑ ይህም ሀገር በቀል ዝርያዎችን፣ ብርቅዬ እና አደጋ ላይ ያሉ ወይም ሊጠፉ የተቃረቡ ዝርያዎችን ያካትታል።

HCV2፦ በዓለም አቀፍ፣ በክልላዊ ወይም በብሔራዊ ደረጃ ጠቃሚ የሆኑ ያልተነኩ የደን ገጽታዎች እና ትላልቅ የመልክዓ ምድር ደረጃ ሥርዓተ-ምህዳሮችና ሥርዓተ-ምህዳር ቅብብሎች ሲሆኑ፣ በተፈጥሯዊ የስርጭትና የተትረፍርፎሽ ሁኔታዎች ውስጥ አብዛኛው በተፈጥሮ የሚገኙ ዝርያዎች ሕያው የሆኑ ህዝቦችን የያዙ ናቸው።

HCV3፦ ብርቅዬ፣ አደጋ ላይ ያሉ ወይም ሊጠፉ የተቃረቡ ሥነ-ምህዳሮች፣ መኖሪያ ቤቶች ወይም መጠለያዎች።

HCV4፦ በወሳኝ ሁኔታዎች ውስጥ ያሉ መሰረታዊ የሥነ-ምህዳር አገልግሎቶች፣ ይህም የውኃ ማጠራቀሚያዎችን ጥበቃ እና በቀላሉ የሚጎዱ የአፈርና የዳገት ክፍሎች የአፈር መሸርሸርን መቆጣጠርን ያካትታል።

HCV5፦ የአካባቢው ማህበረሰቦችን ወይም ነባር ሕዝቦችን መሠረታዊ ፍላጎቶች (ለመተዳደሪያ፣ ለጤና፣ ለአመጋገብ፣ ለውሃ፣ ወዘተ) ለማሟላት መሠረታዊ የሆኑ ቦታዎችና ሀብቶች ሲሆኑ፣ ከእነዚህ ማህበረሰቦች ወይም ነባር ሕዝቦች ጋር በመነጋገር የተለዩ ናቸው።

HCV6፦ በዓለም አቀፍ ወይም በብሔራዊ ደረጃ ባህላዊ፣ የአርኪኦሎጂ ወይም ታሪካዊ አስፈላጊነት ያላቸው፣ እና/ወይም ለአካባቢ ማህበረሰቦች ወይም ለነባር ሕዝቦች ባህላዊ ባህሎች ወሳኝ የሆኑ ባህላዊ፣ ሥነ-ምህዳራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይም ሃይማኖታዊ/ቅዱስ አስፈላጊነት ያላቸው ስፍራዎች፣ ሀብቶች፣ መኖሪያ ቤቶች እና መልክዓ ምድሮች ሲሆኑ፣፣ ከእነዚህ የአካባቢው ማህበረሰቦች ወይም ነባር ሕዝቦች ጋር በመነጋገር የተለዩ ናቸው።[62]

ለHCV አካባቢዎች እና ለተፈጥሮ ሥነ ምህዳሮች ጥበቃ የሚሆን የተወሰነ የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ ሰነድ የHCV አካባቢዎችን ለመለየት የበለጠ ዝርዝር ትርጓሜዎችን እና መመሪያዎችን ያካትታል።

ወራሪ ዝርያዎች

ለተሰጠው ቦታ ሀገር በቀል ያልሆነ እና በዚያ ቦታ መገኘቱ ወይም መግባት በኢኮኖሚ፣ በአካባቢ ወይም በሰው ጤና ላይ ጉዳት የሚያስከትል ወይም ሊያስከትል የሚችል የእፅዋት ወይም የእንስሳት ዝርያ ወይም ንዑስ ዝርያ ነው።[63]

ለሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች፣ ወራሪ ዝርያዎች የሚባሉት በIUCN/SSC Invasive Species Specialist Group (ISSG) እንደ 100 የዓለም እጅግ በጣም መጥፎ ወራሪ ባዕድ ዝርያዎች ተብለው የተጠቀሱት ናቸው። የሰብል ወይም የእንስሳት ዝርያዎች እንደ ወራሪ ዝርያዎች አይቆጠሩም።

100 የዓለም እጅግ በጣም መጥፎ ወራሪ ባዕድ ዝርያዎችን ይመልከቱ

ወቅታዊ ሠራተኞች

ጊዜያዊ ሠራተኞች ይመልከቱ።

ወጣት ሠራተኛ

ከዝቅተኛው የቅጥር ዕድሜ (15 ዓመት) በላይ የሆነ፣ ነገር ግን ከ18 ዓመት በታች የሆነ፣ አደገኛ ያልሆነ እና ለእድሜው ተስማሚ ሥራ የሚያከናውን ሕፃን። የልጅ ሥራ ይመልከቱ።

ውስን የመግቢያ የጊዜ ልዩነቶች (REI)

ሠራተኞች የመከላከያ ልብስ ወይም ቁሳቁስ ሳይጠቀሙ ወደ ኬሚካል የተረጨበት አካባቢ በአስተማማኝ ሁኔታ እንደገና መግባት ከመቻላቸው በፊት ፀረ-ተባዩ ከተረጨ በኋላ ማለፍ ያለበት ዝቅተኛው ጊዜ። የጊዜ ቆይታው በፀረ-ተባyu፣ በመርዛማነቱ፣ በአዘገጃጀቱ፣ በአተገባበር ዘዴው እና በሰብሉ ላይ ይወሰናል።[64]

ዘገይቶ የሚለቀቅ ማዳበሪያ

ንጥረ ነገሮችን ሁሉንም በአንድ ጊዜ ሳይሆን በጊዜ ሂደት በዝግታ የሚለቅ የማዳበሪያ ዓይነት። ይህ የንጥረ ነገር ኪሳራን ለመቀነስ፣ ጊዜን ለመቆጠብ እና ማዳበሪያን በመደበኛነት የመተግበርን አስፈላጊነት ለመቀነስ ይረዳል። የተወሰኑ ዘገይቶ የሚለቀቁ ማዳበሪያዎች እፅዋት በሚፈልጓቸው ጊዜ ንጥረ ነገሮችን ቀስ በቀስ እንዲለቁ ሽፋን ሊደረግላቸው ወይም በተለየ ሁኔታ ሊሠሩ ይችላሉ።[65]

ዝቅተኛ ደመወዝ

አንድ ቀጣሪ ለተሰጠው ጊዜ ለተሠራው ሥራ ለደመወዝ ተቀባዮች እንዲከፍል የሚገደድበት ዝቅተኛው የካሳ መጠን ሲሆን፣ በጋራ ስምምነት ወይም በግለሰብ ውል ሊቀንስ አይችልም።

የሕፃናት ሥራ

የሕፃናት ወይም የጎልማሳዎች በሥራ ላይ መሳተፍ ጤናቸውንና የግል እድገታቸውን የማይጎዳ ወይም ትምህርታቸውን የማያስተጓጉል ከሆነ፣ በአጠቃላይ አዎንታዊ ነገር ተደርጎ ይወሰዳል። ይህም ወላጆቻቸውን በቤት ውስጥ መርዳት፣ በቤተሰብ ንግድ ላይ ማገዝ ወይም ከትምህርት ሰዓት ውጭ እና በትምህርት ቤት የእረፍት ጊዜያት የኪስ ገንዘብ ማግኘት ያሉ ተግባራትን ያካትታል። እንዲህ ያሉ ተግባራት ለህፃናት እድገት እና ለቤተሰቦቻቸው ደህንነት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፤ ክህሎትና ልምድ የሚሰጡዋቸው ከመሆኑም በላይ በአዋቂ ህይወታቸው ውስጥ ውጤታማ የማህበረሰብ አባላት እንዲሆኑ ያዘጋጃሉ።[66] ይህ የሚከተሉትን ያካትታል፦

መደበኛ ቅጥር/ሥራ፦ ከ15 ዓመት ዕድሜ ጀምሮ (በአንዳንድ በማደግ ላይ ባሉ ኢኮኖሚዎች 14) ልጆች በሳምንት ከ48 ሰዓታት የማይበልጥ አጠቃላይ ቅጥር ወይም ሥራ መጀመር ይችላሉ። ዝቅተኛው የዕድሜ ገደብ ከፍ ያለ ወይም የተፈቀደው የሥራ ሰዓት ብዛት ዝቅተኛ በሆነባቸው አገራት፣ ብሔራዊው ዝቅተኛ ዕድሜ እና ከፍተኛው የሥራ ሰዓት ተፈጻሚ ይሆናል። የሕፃናት ሥራ አደገኛ መሆን የለበትም፣ ነገር ግን ደህንነቱ የተጠበቀ እና ለዕድሜያቸው ተስማሚ መሆን አለበት፣ እንዲሁም አስገዳጅ ትምህርታቸውን ማስተጓጎል የለበትም።

ቀላል ሥራ፦ ለሕፃናት ጤና እና እድገት ጎጂ ያልሆነ፣ ትምህርታቸውን ወይም ስልጠናቸውን የማያስተጓጉል፣ በአዋቂ ቁጥጥር ስር ያለ እና በሳምንት ከ14 ሰዓታት የማይበልጥ ሥራ። ከILO ዝቅተኛ የዕድሜ ስምምነት ቁ. 138 ጋር በሚጣጣም መልኩ፣ የ12-14 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ልጆች በማደግ ላይ ባሉ ኢኮኖሚዎች ውስጥ ቀላል ሥራ ሊሠሩ ይችላሉ። ብሔራዊ ህግ ልጆች ቀላል ሥራ እንዲሠሩ በማይፈቅድባቸው አገራት፣ ብሔራዊው ለቅጥር የመግቢያ ዝቅተኛ ዕድሜ ተፈጻሚ ይሆናል።

የቤተሰብ ሥራ፦ በአነስተኛ የቤተሰብ እርሻዎቻቸው ላይ በሕፃናት የሚሰሩ የግብርና ተግባራት ሲሆኑ፣ ክህሎትን የማዳበር ዕድል የሚሰጡ፣ ቀላል እና ለዕድሜ ተስማሚ የሆኑ ተግባራትን ያቀፈ ነው። ተግባራቶቹ ለጤናቸው እና ለእድገታቸው ጎጂ ካልሆኑ፣ ትምህርታቸውን የማያስተጓጉሉ ከሆነ እና በአዋቂ ቁጥጥር ስር ከሆኑ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ ተብለው አይመደቡም።

የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ

ልጆችን ከልጅነታቸው፣ ከእምቅ ችሎታቸው እና ከክብራቸው የሚነጥቅ፣ እና ለአእምሮ፣ ለአካል፣ ለማህበራዊ ወይም ለሥነ ምግባራዊ ጎጂ እና አደገኛ የሆነ ሥራ። ይህም ትምህርት ቤት የመሄድ እድልን በመንፈግ ወይም ትምህርታቸውን ያለጊዜው እንዲያቋርጡ በማስገደድ ትምህርታቸውን የሚያስተጓጉል፤ ወይም ከመጠን በላይ ረጅም እና ከባድ ሥራን ከትምህርት ጋር እንዲያጣምሩ የሚጠይቅ ሥራን ያካትታል።[67] ይህ የሚከተሉትን ያካትታል፦

  • የከፋ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ ዓይነቶች፦ እንደ ልጆችን መሸጥና ማዘዋወር፣ ዕዳ ማስያዝ እና ባርነት፣ እና ለግዳጅ ወይም አስገዳጅ ሥራ፣ እንዲሁም ለትጥቅ ግጭት ልጆችን በግዳጅ ወይም አስገዳጅነት መመልመልን የመሳሰሉ ሁሉንም የባርነት ዓይነቶች ወይም ከባርነት ጋር የሚመሳሰሉ ድርጊቶችን ጨምሮ፤ ዝሙት ለማስፈጸም፣ የወሲብ ምስሎችን ወይም ዝግጅቶችን ለማምረት ልጆችን መጠቀም፣ ማግኘት ወይም ማቅረብ፤ ወይም ለሌሎች ህገ-ወጥ ተግባራት ልጆችን መጠቀም፣ ማግኘት ወይም ማቅረብ።[68]

  • አደገኛ ሥራ፦ የከፋ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ ዓይነቶች አደገኛ ሥራንም ያካትታሉ፤ ይህም በተፈጥሮው ወይም በሚከናወንበት ሁኔታ ምክንያት የልጆችን ጤና፣ ደህንነት ወይም ሥነ ምግባር ሊጎዳ የሚችል ነው። ይህም ከባድ ሸክሞችን መሸከም፣ አደገኛ ቦታዎች ላይ መሥራት፣ ጤናማ ባልሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ መሥራት፣ በሌሊት መሥራት፣ ወይም አደገኛ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች ወይም መሣሪያዎች ጋር መሥራት፣ ወይም ለረጅም ሰዓታት ወይም ከፍታ ላይ መሥራትን ያካትታል ነገር ግን በእነዚህ ብቻ አይወሰንም። ILO ስምምነት ቁ. 182ን የፈረሙ አገራት ለልጆች አደገኛ እንደሆኑ የሚታሰቡትን የሥራ ዓይነቶች ብሔራዊ ዝርዝር እንዲያዘጋጁ ይጠበቅባቸዋል። እነዙህ ብሔራዊ የአደገኛ የሥራ ዓይነቶች ዝርዝሮች ባሉበት ቦታ ተፈጻሚ ይሆናሉ። ብሔራዊ የአደገኛ የሥራ ዓይነቶች ዝርዝሮች በሌሉበት ጊዜ፣ እንደ የሥራ፣ የግብርና፣ የሕፃናት ደህንነት መምሪያዎች፣ እና/ወይም ብሔራዊ የ ILO ጽህፈት ቤት ምክር ካሉ ብሔራዊ የሥልጣን አካላት ምክር ሊፈለግ ይችላል።[69]

  • ከዕድሜ በታች የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ፦ ከ15 ዓመት በታች በሆኑ ሕፃናት ለእርሻው፣ ለቡድኑ ወይም ለቡድን አባላት የሚሰራ፣ ትምህርታቸውን የሚያስተጓጉል፣ በሳምንት ከ14 ሰዓታት በላይ የሚሆን ወይም "ቀላል ሥራ ወይም የቤተሰብ ሥራ" ተብሎ የማይታሰብ ሥራ። ብሔራዊ ህግ ዝቅተኛውን የሥራ ዕድሜ በ14 ዓመት ካስቀመጠ ይህ ዕድሜ ተፈጻሚ ይሆናል። ብሔራዊ ህግ ዝቅተኛውን የሥራ ዕድሜ ከ15 ዓመት በላይ ካስቀመጠ፣ ለቅጥር መግቢያነት ብሔራዊው ዝቅተኛ ዕድሜ ተፈጻሚ ይሆናል።[70]

ከዚህ በታች በሕፃናት ሥራ እና በሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ መካከል ያለውን የዕድሜ ገደብ የሚያሳይ ሥዕላዊ መግለጫ ይመልከቱ።

ሥዕላዊ መግለጫ 1. በሕፃናት ሥራ፣ በሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ እና በከፋ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ ዓይነቶች መካከል ያለውን የዕድሜ ልዩነት የሚያሳይ።[71]

ማሳሰቢያ፦ በቅንፍ ውስጥ ያሉት ቁጥሮች የኢኮኖሚ እና የትምህርት ተቋሞቻቸው በበቂ ሁኔታ ላልተሻሻሉ አባል አገራት በILO የተፈቀደ ዝቅተኛ የሥራ ዕድሜ ገደቦች ናቸው።

የመባቻ ደረጃዎች

በአንድ ተክል ወይም በእጽዋት ስብስብ ላይ በተባይ ወይም በበሽታ ምክንያት የሚደርስ፣ ተባዩን ወይም በሽታውን ለመቆጣጠር ልዩ እርምጃዎች ከመወሰዳቸው በፊት ሊታገስ የሚችል ከፍተኛው የጉዳት ደረጃ (ወይም የጉዳት ምልክቶች) ነው። ጉዳቱ ከጨመረ የኢኮኖሚ ኪሳራዎች ከቁጥጥር ወጪዎች በላይ ይሆናሉ።

የመደራጀት ነፃነት

ሠራተኞች እና ቀጣሪዎች ያለምንም ልዩነት፣ ቀደም ያለ ፈቃድ ሳያስፈልጋቸው የመረጧቸውን ድርጅቶች የመመስረት እና የመቀላቀል መብት።[72]

የመጀመሪያ ገዢ

ከመጀመሪያው የእርሻ ሰርቲፊኬት ባለቤት በኋላ ሰርቲፋይድ ምርቱን በሕጋዊ መንገድ የያዘው የሰርቲፊኬት ባለቤት።

የመጨረሻ የሸማች ምርት

ለፍጆታ ዝግጁ የሆነ እና ከማቀነባበሪያ ወይም ከማሸጊያ አንጻር ተጨማሪ ለውጥ የማያስፈልገው፣ የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ መለያ ያለው ምርት።

የማስተካከያ እርምጃ

የተገዢነት ጉድለት መንስኤዎችን ለማስወገድ እና ተደጋግሞ እንዳይከሰት ለመከላከል የሚወሰድ እርምጃ።

የማስተካከያ እርምጃዎች የተገዢነት ጉድለት ዋና መንስኤን በሚያስወግዱ የረጅም ጊዜ ዘላቂነት ባላቸው መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለባቸው።[73]

የማስተካከያ እርምጃዎች

የተገዢነት ጉድለትን ለማስወገድ በሰርቲፊኬት ባለቤቱ የሚወሰዱ ማስተካከያዎች እና የማስተካከያ እርምጃዎች ጥምረት።

የማንነት ጥበቃ

ሰርቲፋይድ የሆነውን ግብአት ወይም ምርት ወደ እርሻ ሰርቲፊኬት ባለቤት ለመለየት የሚያስችል የትረሰቢሊቲ አማራጭ። ይህ እጅግ በጣም ጥብቅ የሆነ የትረሰቢሊቲ ዓይነት ነው። ሰርቲፋይድ የሆነ ግብአት ወይም ምርት ሰርቲፋይድ ካልሆነ ግብአት ወይም ምርት ጋር ወይም እርስ በርስ አይቀላቀልም። ሰርቲፋይድ የሆነ ምርት ከተለያዩ ሰርቲፋይድ ምንጮች/እርሻዎች የመጣ ከሆነ፣ ነገር ግን ማንነቱ በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ከተጠበቀ፣ የተደባለቀ የማንነት ጥበቃ የተባለው ንዑስ ዓይነት ሊተገበር ይችላል።

የማዳበሪያ አጠቃቀም ዕቅድ

በሰብል ንጥረ ነገር መስፈርቶች እና በአፈር ለምነት ሁኔታ ላይ የተመሰረተ፣ የማዳበሪያውን ዓይነት፣ ጊዜ፣ ዘዴ እና የአጠቃቀም መጠን የሚገልጽ በሰነድ የተደገፈ ዕቅድ። ዕቅዱ የንጥረ ነገሮችን መፍሰስ እና የአካባቢን ብክለት ለመቀነስ እንደ የአየር ንብረት፣ የሰብል ዓይነት እና የአፈር ሁኔታ ያሉ የተወሰኑ ቦታዎችን ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባል።

የምርመራ ኦዲት

በሬንፎረስት አሊያንስ ወይም በሰርቲፊኬሽን አካል ሊከናወን የሚችል ያልተጠበቀ ኦዲት ሲሆን ይህም ለተለየ ቅሬታ፣ ሪፖርት ለተደረገ ክስተት ወይም የሰርቲፊኬት ባለቤቱ ተገዢነትን በተመለከተ ጠቃሚ መረጃ ለመስጠት የደረጃዎቹን መስፈርቶች ማክበር ለማረጋገጥ የሚደረግ ነው።

የምድር ትል ቆጠራ

በተወሰነ የአፈር ክልል ውስጥ የምድር ትሎችን መኖር እና ብዛት በመለካት የአፈርን አወቃቀር፣ የኦርጋኒክ ይዘትን እና ባዮሎጂካል እንቅስቃሴን ለመገምገም የሚያገለግል ተግባራዊ ባዮሎጂካል ዘዴ።[74]

የሠራተኛ አቅራቢ

ለእርሻዎች ወይም ለምርት መገልገያዎች ቋሚ፣ ጊዜያዊ ወይም ወቅታዊ ሠራተኞችን በማቅረብ የሠራተኛ ቅጥር እና ምደባ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ኤጀንሲ፣ ንዑስ ወኪል ወይም ግለሰብ። የሠራተኛ አቅራቢዎች ለትርፍ ወይም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ብዙ ዓይነት ሊሆኑ ይችላሉ።

የሠራተኞች ተወካይ

በብሔራዊ ሕግ ወይም በኩባንያ አሠራር መሠረት እንደነሱ እውቅና የተሰጣቸው ሰዎች፣ እነሱም፦

  • የሠራተኛ ማኅበር ተወካዮች፣ እነዚህም በሠራተኛ ማኅበራት ወይም በእነዚያ ማኅበራት አባላት የተሰየሙ ወይም የተመረጡ ተወካዮች ናቸው።

  • የተመረጡ ተወካዮች፣ እነሱም በብሔራዊ ሕጎች ወይም ደንቦች ወይም በጋራ ስምምነቶች ድንጋጌዎች መሠረት በድርጅቱ ሠራተኞች በነፃነት የሚመረጡ ተወካዮች ናቸው እና ተግባሮቻቸው በሚመለከተው ግዛት ውስጥ የሠራተኛ ማኅበራት ብቸኛ መብት ተብለው እውቅና የተሰጣቸውን ተግባራት የማያካትቱ ናቸው።[75]

በአስተዳደር ሚና ውስጥ ያለ ሰው የሠራተኞች ተወካይ ሆኖ ማገልገል አይችልም።

የሠራተኞች ድርጅት

መብቶቻቸውን እና ጥቅሞቻቸውን ለማስፋፋት እና ለመከላከል የተቋቋመ ማንኛውም በፈቃደኝነት ላይ የተመሰረተ፣ ነፃ የሠራተኞች ድርጅት።[76]

የሰርቲፊኬሽን አካል

የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ሥርዓትን በመጠቀም የሚንቀሳቀስ እና በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ፕሮግራም ስር ኦዲት ለማካሄድ እና ሰርቲፊኬት ለመስጠት ፈቃድ የተሰጠው ሦስተኛ ወገን የእርግጠኝነት ተገዢነት ግምገማ አካል።[77]

የሰርቲፊኬሽን ወሰን

ከተወሰነ የሰርቲፊኬት ባለቤት ጋር ተያያዥነት ያላቸው በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ፕሮግራም የተሸፈኑ ተግባራት፣ ሂደቶች፣ ምርቶች ወይም አገልግሎቶች ወሰንና ስፋት።

የሰርቲፊኬሽን ወሰን

የሰርቲፊኬሽን ወሰን ይመልከቱ።

የሰርቲፊኬት ባለቤት

ከሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬት የተሰጠው ማንኛውም ሰው። ሰርቲፊኬቱ በሬንፎረስት አሊያንስ የተሰጠ የድጋፍ ዕውቅና ወይም በሰርቲፊኬሽን አካል የተሰጠ ሰርቲፊኬት ሊሆን ይችላል። የሰርቲፊኬት ባለቤቱ የእርሻ ወይም የአቅርቦት ሰንሰለት ተዋናይ፣ ወይም ለብዙ እርሻዎች ወይም የአቅርቦት ሰንሰለት ተዋናዮች ሰርቲፊኬቱን የሚያስተዳድር ሕጋዊ ተቋም ሊሆን ይችላል።

የሰርቲፊኬት ወሰን

በሰርቲፊኬት ባለቤት ሰርቲፊኬት ስር የተሸፈኑ ተግባራት፣ ሂደቶች፣ ተዋናዮች እና ምርቶች ስብስብ።

የሰብል ልውውጥ

በተመሳሳይ የእርሻ ቦታ ላይ በተከታታይ በሚደረጉ የግብርና ወቅቶች የተለያዩ የሰብል ቤተሰቦች ዝርያዎችን በታቀደ ሥርዓት ወይም ቅደም ተከተል በመፈራረቅ የመትከል ልምምድ ሲሆን፣ ይህም የአረም፣ ተባይና በሽታ ዑደቶችን ለመግታት እና የአፈርን ለምነትና ኦርጋኒክ ይዘት ለመጠበቅ ወይም ለማሻሻል ይረዳል።[78]

የሰብል ምርታማንት ሳይቀንስ ማደስ

ያሉትን ዛፎች ሳይተኩ ለማደስ ቅርንጫፎችን መቁረጥ ወይም ጉቶ ላይ መቁረጥን የሚያካትት የዛፍ ሰብል ጥገና አሠራር። እነዚህ ተግባራት ብዙውን ጊዜ ከሁለት እስከ 10 ዓመት ባለው ዑደት ውስጥ የሚከናወኑ ሲሆን፣ የዋና ዋናዎቹን ግንድ/ዋና ቅርንጫፎች በከፊል ወይም በሙሉ ለማደስ ያለሙ ናቸው። በዑደቱ ላይ በመመስረት፣ ከ10 እስከ 50 በመቶ የሚሆነው የሰርቲፋይድ ሰብል ስፋት ላይ ይተገበራል።

የሰብል ተካፋይ እርሻ

ከሰብሉ የተወሰነ ድርሻ ወይም ከሰብል ሽያጭ የተወሰነ መቶኛ ለማግኘት ሲል የባለ መሬቱን መሬት የሚያርስ ተከራይ ገበሬ።

የሰብሎች መልሶ ማቋቋም

ያረጁ፣ በበሽታ በተጠቁ ወይም ምርታማነት ባነሰባቸው የዛፍ ሰብሎች ላይ ሳይተኩ ምርታማነትን፣ ጤናን እና ጥግግትን ለመመለስ ወይም ለማሻሻል ያለሙ የግብርና ልምምዶች ስብስብ። ቅርንጫፎችን መቀጠል፣ ጉቶ ላይ መቁረጥ እና ቅርንጫፎችን መቁረጥን ያካትታል።[79]  

የሥራ ቦታ ጤና እና ደህንነት (OHS)

የሥራ ቦታን ለሠራተኛው/ተቀጣሪው እና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሻለ ለማድረግ ያለሙ የጤና፣ የደህንነት እና የጤንነት ጉዳዮች። አደጋዎችን በመጀመሪያ መከላከል ላይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቷል። OHS ህጎችን፣ ስታንዳርዶችን፣ ፕሮግራሞችን እና ፈቃደኛ ፕሮግራሞችን ሊያካትት ይችላል።

የሥራ ውል

በቀጣሪው (እንደ እርሻ አስተዳደር፣ የቡድን አስተዳደር ወይም የኩባንያ አስተዳደር) እና በሠራተኛው/በተቀጣሪው መካከል ያለ የጽሑፍ ስምምነት። የሥራ ውሉ የሥራ መግለጫን፣ የሥራ ሰዓታትን፣ የደመወዝ መጠንን፣ የትርፍ ሰዓት ደንብን፣ ጥቅማጥቅሞችን እና ቅነሳዎችን፣ ዓመታዊ የሚከፈልበትን የዕረፍት ፈቃድን፣ በበሽታ፣ በአካል ጉዳት ወይም በአደጋ ጊዜ ከክፍያ ማጣት ጥበቃን፣ እና ለውል ማቋረጥ የሚሰጠውን ማሳሰቢያ ጊዜ ማካተት አለበት።

የሥነ-ምህዳር ጤና

የተፈጥሮ አካባቢ አጠቃላይ ደህንነት እና ተግባራዊ ሚዛንና ትክክለኛነት። ጤናማ ሥነ-ምህዳር እንደ ውኃ ማጥራት፣ የአበባ ዘር ማስተላለፍ እና የንጥረ ነገር ዑደት ያሉ ተፈጥሯዊ ሂደቶቹን በተሳካ ሁኔታ የሚያከናውን እና መስተጓጎሎችን የመቋቋም አቅም ያለው ነው።

የስጋት ቅነሳ እርምጃዎች

አሉታዊ ክስተቶች እንዳይከሰቱ ለመከላከል እና/ወይም ተጽዕኖአቸውን ለመቀነስ የተወሰዱ እርምጃዎች።[80]

የስጋት ተጋላጭነት

የአንድ ሊከሰት የሚችል አሉታዊ ሁኔታ የመከሰት ዕድል ሲሆን፣ የክስተቱን ሊከሰት የሚችልበት ዕድል እና ውጤቶቹ ክብደትን በማጣመር የሚለካ ዕድል ነው።[81]

የስጋት ግምገማ

የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች መስፈርቶችን ተገዢነት እና የሚጠበቁትን የዘላቂነት ውጤቶች ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ጉዳዮችን ለመለየት እና ለመተንተን ያለመ ሥርዓታዊ ሂደት ነው። ሬንፎረስት አሊያንስ ይህንን ትንተና ለመደገፍ የስጋት ግምገማ መሳሪያ አዘጋጅቷል።

የረቂቅ ሕዋሳት ስብስብ (አፈር)

አፈርን የሚይዙ ሕይወት ያላቸው ረቂቅ ህዋሳት ስብስብ ሲሆን፣ ባክቴሪያዎችን፣ ፈንገሶችን፣ እርሾዎችን ወይም ቫይረሶችን ያካትታል። እነዚህ ረቂቅ ህዋሳት ለንጥረ ነገሮች ዑደት፣ ለኦርጋኒክ ይዘት መበስበስ አስተዋፅኦ ያደርጋሉ እና የአፈርን አወቃቀር፣ ለምነት እና የእፅዋትን ጤና የሚነኩ ወሳኝ የአፈር ባዮሎጂያዊ ሂደቶችን ያመራሉ። በግብርና ውስጥ፣ የአፈር የረቂቅ ሕዋሳት ስብስብ ምርታማ እና ጠንካራ የሰብል ሥርዓቶችን ለመጠበቅ አስፈላጊ ነው።[82]

የረቂቅ ሕዋሳት ብዛት

የአፈርን ጤና አመላካች ሆኖ የሚያገለግል የአፈር የረቂቅ ሕዋሳት ስብስብ መኖር የቁጥር መለኪያ ነው። ይህ ስለ ባዮሎጂያዊ እንቅስቃሴ እና ስለ አፈር የንጥረ ነገር ዑደት እና የእፅዋት እድገትን የመደገፍ አቅም መረጃ ይሰጣል።[83]

የሬንፎረስት አሊያንስ የይገባኛል ጥያቄ

ስለ ሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ወይም ስለ ሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ምርት ወይም ግብዓት ምንጭ ስለመሆን የሚደረግ ማንኛውም ማጣቀሻ። የይገባኛል ጥያቄው በምርቱ ላይ ወይም ከምርቱ ውጭ፣ እና/ወይም ከምርቱ አቅርቦት ወይም ሽያጭ ጋር በተያያዘ ሊደረግ ይችላል። ይህ ሁለቱም ከንግድ-ወደ-ንግድ እና ከንግድ-ወደ-ሸማች ሊሆን ይችላል።[84]

የርጭት መበታተን

አግሮኬሚካሎች በአየር እንቅስቃሴ እና ባልታሰበ ሁኔታ ከታለመው አካባቢ ውጭ ሲቀመጡ።

የቅሪተ አካል ነዳጅ

ከመሬት በታች የተቀበሩ ኦርጋኒክ ይዘቶች በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ዓመታት በሙቀት እና ግፊት ተጽዕኖ የተፈጠሩ፣ እንደ ከሰል፣ ዘይት እና የተፈጥሮ ጋዝ ያሉ ታዳሽ ያልሆኑ ተቀጣጣይ የኃይል ምንጮች።[85]

የቅሬታ አፈታት ሥርዓት

ግለሰቦች፣ ሠራተኞች/ተቀጣሪዎች፣ ማህበረሰቦች፣ እና/ወይም ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች (ሰነድ አሳልፈው የሚሰጡ ሰዎችን ጨምሮ) በተወሰኑ የእርሻ ወይም የንግድ ሥራዎች እና/ወይም አሠራሮች ምክንያት አሉታዊ ተጽዕኖ ስለደረሰባቸው ቅሬታዎቻቸውን ማቅረብ የሚችሉበት ሂደት። የቅሬታ አፈታት ሥርዓት መደበኛ ወይም መደበኛ ያልሆነ፣ ህጋዊ ወይም ህጋዊ ያልሆነ ሊሆን ይችላል። ይህ የቅሬታ ማቅረቢያ፣ አያያዝ፣ ማስተካከያ እና ክትትል ደረጃዎችን ያካትታል።

የቅጠል ግምገማ

የእፅዋትን ፊዚዮሎጂያዊ ሁኔታ፣ የአመጋገብ ሁኔታ ወይም ለአካባቢያዊ ሁኔታዎች የሚሰጡትን ምላሽ ለመወሰን የሚደረግ የእፅዋት ቅጠሎችን ግምገማ።  የቅጠል ግምገማዎች የንጥረ ነገር እጥረት ወይም የተባይና የበሽታ ምልክቶችን በእይታ መመርመርን፣ እንዲሁም የንጥረ ነገር ትኩረትን ለመለካት የላብራቶሪ ቅጠል ቲሹ ትንተናን ሊያካትቱ ይችላሉ።

የቅጥር ክፍያ

ሠራተኞች ሥራ ለማግኘት ወይም ለቅጥር እንዲበቁ በቅጥር ሂደት ውስጥ የሚወጣ ማንኛውም ክፍያ ወይም ተያያዥ ወጪ ሲሆን፣ አስገዳጅነታቸው ወይም አሰባሰባቸው በምን መንገድ፣ በምን ሰዓት ወይም በየት ቦታ እንደተከናወነ ሳይወሰን።

የቆሻሻ ውሃ መመዘኛዎች

ወደ ውሃማ ሥነ-ምህዳሮች ለሚለቀቅ የቆሻሻ ውሃ የተቀመጡ የሬንፎረስት አሊያንስ መመዘኛዎች የሚከተሉት ናቸው፦

የቆሻሻ ውሃ ጥራት መመዘኛ

ዋጋ

ባዮኬሚካላዊ ኦክስጅን ፍላጎት (BOD5)

< 750 ሚ.ግ./ሊ

ጠቅላላ የታገዱ ጠጣሮች

< 50 ሚ.ግ./ሊ

ቅባትና ዘይቶች

< 50 ሚ.ግ./ሊ

ፒኤች (pH)

ከ 5.5 እስከ

9.0

ለመስኖ የቆሻሻ ውሃ የሬንፎረስት አሊያንስ መመዘኛዎች የሚከተሉት ናቸው፦

የቆሻሻ ውሃ ጥራት መመዘኛ

ዋጋ

የአንጀት ጥገኛ ትሎች (በአንድ ሊትር የእንቁላሎች ቁጥር የሂሳብ አማካይ)

<1

ከሰገራ የሚመጡ ኮሊፎርሞች (በ100 ሚሊ ሊትር የጂኦሜትሪክ አማካይ ቁጥር)

≤ 1000

የበቀል እርምጃ

አንድ ቀጣሪ ሠራተኛን/ተቀጣሪን በሕግ የተጠበቀ እንቅስቃሴ ውስጥ በመሳተፉ የሚቀጣበት ተግባር ነው። የበቀል እርምጃ እንደ ዝቅ ማድረግ፣ የዲሲፕሊን እርምጃ፣ ከሥራ ማባረር፣ የደመወዝ ቅነሳ፣ ወይም የሥራ ወይም የፈረቃ ለውጥ ያሉ ማንኛውንም አሉታዊ የሥራ እርምጃ ሊያካትት ይችላል። ነገር ግን የበቀል እርምጃ እንደ ሥራዎችን መለወጥ ያሉ የበለጠ ስውር ሊሆንም ይችላል።

የቡድን ሠራተኛ

ለሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ቡድን የሚሰሩ ሠራተኞች። ይህ የቡድን አስተዳደር ሠራተኞችን (እንደ የውስጥ ኢንስፔክተሮች እና ለቡድን አስተዳደር የሚሠሩ የቢሮ ሠራተኞች ያሉ)፣ በማዕከላዊ የምርት፣ የማቀነባበሪያ እና የጥገና ስፍራዎች ያሉ ሠራተኞችን ያጠቃልላል።

የተቀናጀ ተባይ አያያዝ (IPM)

የተቀናጀ ተባይ አያያዝ (IPM) ማለት የተባይ ብዛትን ለመከላከል ወይም ለመቀነስ፣ እንዲሁም ፀረ-ተባይ መድኃኒቶችንና ሌሎች ጣልቃገብነቶችን በኢኮኖሚያዊ ትርጉም ባለው ደረጃ ለመጠበቅ እና በሰው ጤናና በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ስጋት ለመቀነስ፣ ሁሉንም ያሉ የተባይ መቆጣጠሪያ ዘዴዎች በጥንቃቄ መገምገም እና ማቀናጀት ነው። IPM በግብርና ሥነ-ምህዳሮች ላይ አነስተኛ መስተጓጎል በማድረግ ጤናማ ሰብሎች እና እንስሳት እንዲያድጉ ያበረታታል፣ የተፈጥሮ ተባይ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን ያበረታታል፣ እንዲሁም የፀረ-ተባይ መድኃኒቶችን አጠቃቀም በመደበኛ የተባይ ወይም የበሽታ ወረርሽኝ ክትትል ላይ ይመሰረታል።[86]

የተቀናጀ የአረም አያያዝ (IWM)

አረሞችን ለመቆጣጠር በጣም ውጤታማ፣ ዘላቂነት ያለው እና አውድ-ተኮር መፍትሄዎችን ለማግኘት እንደ ግጦሽ፣ አረም ማጥፊያ አጠቃቀም፣ መሬትን ማሳረፍ፣ ሜካኒካዊ ቁጥጥር እና ባዮሎጂካል ቁጥጥር ያሉ ተጨማሪ የአረም መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን የሚያጣምር የመሬት አስተዳደር አቀራረብ ነው።  IWM የአረም ጫናን ለመቀነስ፣ የሰብል ምርታማነትን ለመጠበቅ፣ በአካባቢ ላይ ያለውን ተፅዕኖ ለመቀነስ እና የግብርና ሥነ-ምህዳሮችን የረዥም ጊዜ ዘላቂነት ለማሳደግ ያለመ ነው።[87]

የተገዢነት ጉድለት

በሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች ውስጥ ያለን መስፈርት ሙሉ በሙሉ አለመሟላት።[88]

የቡድን አስተዳደር

የቡድኑን የውስጥ አስተዳደር ሥርዓት የማልማትና የመተግበር እና የአባላቱ እርሻዎች ከሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች ጋር ተገዢነት እንዳላቸው የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበት ሕጋዊ ተቋም። የቡድን አስተዳደር የሚያመለክተው ይህንን ተግባር ለተደራጁ አምራቾች ማህበር ለቡድን ሰርቲፊኬሽን የሚያከናውን ኃላፊነት ያለበትን የአስተዳደር አካል፣ የቡድን አስተዳዳሪ ወይም ቴክኒካል ወኪል ነው።

የቡድን አባል

የአንድ ቡድን አካል ሆኖ ሰርቲፋይድ የሆነ አምራች። ይህ ሰው የእርሻው ትክክለኛ አስፈጻሚ ነው (ለምሳሌ አነስተኛ ገበሬ፣ አከራይ ገበሬ) እና የመሬቱ ባለቤት መሆን የለበትም።

የቡድን አባል ወኪል

ሌሎች የቡድን አባላትን ወክሎ እንዲሠራ ወይም እንዲናገር የተመረጠ ወይም የተሾመ የቡድን አባል ነው።

የባዮሎጂካል ብዝሃነት

እጽዋት፣ እንስሳት፣ ፈንገስ፣ ረቂቅ ተህዋሲያን፣ ተግባሮቻቸውን እና መስተጋብሮቻቸውን ጨምሮ የሕያዋን ፍጥረታት ብዛት፣ ይህም ለሥነ ምህዳር አገልግሎቶች፣ ጤና፣ መረጋጋት እና መቋቋም አስተዋፅዖ ያደርጋል።[89]

የቤተሰብ ሠራተኛ

የግብርና ይዞታን ወይም ሌላ ንግድን ለማካሄድ የሌላኛውን የቤተሰብ አባል የሚረዳ ሰው (ማንኛውም ጾታ) ሲሆን፣ እንደ ሠራተኞች ካልተቆጠረ እና የጋራ የቤተሰብ ፍላጎት ካለው። የሠራተኛ ልውውጥ (ሰዎች ያለክፍያ እርስ በእርስ የሚሰሩበት) እንዲሁ በዚህ ትርጉም ሥር ይወድቃል።

የቤት ውስጥ ሥራ

በአንድ ቤተሰብ ወይም በብዙ ቤተሰቦች ውስጥ ወይም ለእነሱ የሚሠራ ሥራ። የቤት ውስጥ ሥራ ተደርገው የሚወሰዱ ሙያዎች እና ተግባራት ከአገር አገር ይለያያሉ፤ እነሱም ምግብ ማብሰል፣ ማጽዳት፣ ልጆችን፣ አረጋውያንን እና አካል ጉዳተኞችን መንከባከብ፣ አትክልትን ወይም የቤት እንስሳትን መንከባከብ፣ ወይም የቤተሰብ መኪና መንዳትን ሊያካትቱ ይችላሉ።

በቤት ውስጥ ሥራ ላይ ያለ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ የሚያመለክተው የቤት ውስጥ ሥራው በተገቢው ዝቅተኛ ዕድሜ ሥር ባሉ ሕፃናት ወይም አደገኛ በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ ወይም ከባርነት ጋር በሚመሳሰል ሁኔታ ሲከናወን ነው።[90]

የተሰጡ የተጠቃሚ መብቶች

በትረሰቢሊቲ ፕላትፎርም ውስጥ ግብይቶችን ለማድረግ የአቅርቦት ሰንሰለት ሰርቲፊኬት ባለቤትን በመወከል ለእርሻ ሰርቲፊኬት ባለቤት የተሰጠ ፈቃድ።

የተስተካከለ ጉዳይ

በሬንፎረስት አሊያንስ የማስተካከያ ፕሮቶኮል መሰረት የተስተካከለ፣ የተረጋገጠ በሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ የግዳጅ ሥራ፣ አድልዎ እና/ወይም በሥራ ቦታ ላይ የሚፈጸም ጥቃትና ትንኮሳ።

የተረጋገጠ ጉዳይ

ጉዳዩ መከሰቱን ወደ መደምደሚያ የሚመሩ ምስክርነቶችን፣ ሰነዶችን እና/ወይም ከታማኝ ምንጮች የተገኙ ሪፖርቶችን ጨምሮ በማስረጃ ሊረጋገጥ በሚችል የመጀመሪያ ደረጃ ምርመራ የተረጋገጠ ጉዳይ። የሬንፎረስት አሊያንስ የማስተካከያ ሥነ-ሥርዓት የተረጋገጠ ጉዳይ ሁልጊዜም በጥልቀት በሚደረግ ምርመራ ክትትል እንዲደረግበት ይጠይቃል።

የተረፉ የደን ዛፎች

በእርሻው ላይ የነበሩ፣ የመሬቱ ዋና የተፈጥሮአዊ ሥነ-ምህዳር አካል የነበሩ እና ለባዮሎጂካል ብዝሃነት ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው ዛፎች። እነሱ ብዙውን ጊዜ በግብርና ወይም በጥምር እርሻ ሥርዓት ውስጥ ከተተከሉት እና ከሚተዳደሩት ሌሎች ዛፎች የበለጠ ዕድሜ ያላቸው እና ትልቅ ናቸው።

የተጠበቀ አካባቢ

እውቅና ባለው ተፈጥሯዊ፣ ሥነ-ምህዳራዊ እና/ወይም ባህላዊ ዋጋዎች ምክንያት በተዛማጅ ሥነ-ምህዳራዊ ንብረቶች እና ባህላዊ ዋጋዎች ተፈጥሮን ለረጅም ጊዜ ለመጠበቅ በኃላፊነት ባላቸው ባለሥልጣናት እንደ ተጠበቀ የተገለጸ ወይም የተሰየመ የመሬት አካባቢ። ምሳሌዎች ብሔራዊ ፓርኮችን፣ የዱር እንስሳት መሸሸጊያዎችን፣ ባዮሎጂያዊ ወይም ደን መጠባበቂያዎችን፣ የግል መጠባበቂያዎችን እና በዩኔስኮ ባዮስፌር መጠባበቂያዎች ወይም የዓለም ቅርስ ስፍራዎች ውስጥ ያሉ አካባቢዎችን ያካትታሉ። ምርት በሚመለከተው ሕግ መሠረት በተጠበቀ አካባቢ ውስጥ ሊፈቀድ ይችላል፣ ይህም በአስተዳደር ዕቅድ ውስጥ የተወሰነ ቀጠና (ባለብዙ አጠቃቀም ቀጠናዎች፣ የተወሰነ የተጠበቁ አካባቢዎች ምድብ (IUCN ምድቦች V፣ VI) ወይም ፈቃዶች (ለምሳሌ የተፈቀደላቸው እርሻዎች) ሊሆን ይችላል።

የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኮምፖስት)

የአፈርን ጤና እና ለምነት ለማሻሻል እንደ ኦርጋኒክ ማዳበሪያ ሆኖ ሊያገለግል የሚችል፣ ቁጥጥር ከተደረገበት የኦርጋኒክ ይዘት ባዮሎጂያዊ መበስበስ የተገኘ፣ የተረጋጋ፣ ከሁመስ ጋር የሚመሳሰል ይዘት ነው።[91]

የተፈጥሮ ዛፍ የእፅዋት ሽፋን

በእርሻው ላይ በሀገር በቀል ወይም በአካባቢው ተስማሚ በሆኑ የዛፍ ዝርያዎች ሽፋን የተሸፈኑ አካባቢዎች። እነዚህ አካባቢዎች አፈርን በመጠበቅ፣ የውሃ ማቆየትን በመጨመር፣ ባዮሎጂካል ብዝሃነትን በመደገፍ፣ አነስተኛ የአየር ንብረቶችን በመቆጣጠር እና ካርቦን በማስገባት ለሥነ-ምህዳር ጥንካሬ አስተዋፅኦ እንዲያደርጉ ይጠበቃሉ ወይም ይመሰረታሉ። የዛፍ የእፅዋት ሽፋንም በሚመለከተው ብሔራዊ ሕግ እና ዓለም አቀፍ ግዴታዎች መሰረት ይተዳደራል።[92]

የተፈጥሮ ጠላቶች

በሥነ-ምህዳሮች ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኙ እና ሌሎች ህዋሳትን የሚገድሉ፣ የመራቢያ እምቅ ኃይልን የሚቀንሱ ወይም በሌላ መንገድ የሌላ ህዋስን ብዛት የሚቀንሱ ህዋሳት ናቸው። እነሱ የተቀናጀ ተባይ አያያዝ መርሃ ግብሮች ቁልፍ አካል ሲሆኑ አዳኞችን፣ ጥገኛ ተዋህሲያንን እና በሽታ አምጪ ተህዋሲያንን ያጠቃልላሉ። ጥበቃቸው እና ማሳደጋቸው ሥነ-ምህዳራዊ ሚዛንን ለመጠበቅ እና የኬሚካል ተባይ መቆጣጠሪያ አስፈላጊነትን ለመቀነስ ይረዳል።[93]

የትረሰቢሊቲ ዓይነት

ሰርቲፋይድ መጠኖችን ለመያዝ እና ወደ መነሻው ለመከታተል የሚያገለግል ዘዴ፤ ለምሳሌ፦ የጅምላ ሚዛን፣ መለያየት፣ እና ማንነቱ ተጠብቆ መያዝ።

የትረሰቢሊቲ ፕላትፎርም

በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ የሰርቲፋይድ መጠኖች ግብይቶችን እና እንቅስቃሴዎችን ሪፖርት ለማድረግ የሚያገለግል ዲጂታል የሬንፎረስት አሊያንስ ፕላትፎርም።

የኑሮ ደመወዝ

አንድ ሠራተኛ በተወሰነ ቦታ ለሚሠራው መደበኛ የሥራ ሳምንት የሚያገኘው ክፍያ ሲሆን፣ ለሠራተኛው እና ለቤተሰቡ ጥሩ የኑሮ ደረጃ ለማቅረብ በቂ ነው። ጥሩ የኑሮ ደረጃ አካላት ምግብ፣ ውሃ፣ መኖሪያ ቤት፣ ትምህርት፣ ጤና አጠባበቅ፣ መጓጓዣ፣ ልብስ እና ሌሎች አስፈላጊ ፍላጎቶች፣ ያልተጠበቁ ክስተቶች ሲከሰቱ የሚሆኑ መጠባበቂያዎችን ያካትታሉ።[94]

የኑሮ ደመወዝ መለኪያ

ለተወሰነ ጊዜ፣ ክልል እና/ወይም ሰብል የሚሆን የኑሮ ደመወዝ ግምት።[95]

የኑሮ ገቢ

አንድ ቤተሰብ ለሁሉም የቤተሰቡ አባላት ጥሩ የኑሮ ደረጃ ለማቅረብ የሚያስፈልገው የተጣራ ዓመታዊ ገቢ። ጥሩ የኑሮ ደረጃ አካላት ምግብ፣ ውሃ፣ መኖሪያ ቤት፣ ትምህርት፣ ጤና አጠባበቅ፣ መጓጓዣ፣ ልብስ እና ሌሎች አስፈላጊ ፍላጎቶች፣ ያልተጠበቁ ክስተቶች ሲከሰቱ የሚሆኑ መጠባበቂያዎችን ያካትታሉ።

የኑሮ ገቢ አንድ ቤተሰብ የሚያገኘው ገቢ ከብዙ ምንጮች ሊመጣ እንደሚችል ይገነዘባል። ለምሳሌ፣ ለአነስተኛ ገበሬዎች፣ ገቢ ከእርሻ ውጭ ከሚደረጉ ንግዶች እና ከውጭ ከሚላክ ገንዘብ እንዲሁም ከሰብል ሽያጭ ሊገኝ ይችላል።[96]

የንግድ ምልክት ባለቤት

በተመዘገበ የንግድ ምልክት ስም ወይም መለያ ስር ምርትን ለገበያ የሚያቀርብ ግለሰብ፣ ኮርፖሬሽን ወይም የችርቻሮ ሕጋዊ ተቋም፣ ይህ በችርቻሮ ኩባንያዎች ባለቤትነት የተያዙ የግል መለያ የንግድ ምልክቶችን/የመደብር የንግድ ምልክቶችን ሊያካትት ይችላል። ይህ ሕጋዊ ተቋም ምርቱን ራሱ ወይም በሦስተኛ ወገን በኩል ሊያሰናዳ እና ሊያሽግ ይችላል፣ ነገር ግን የንግድ ምልክቱ ባለቤት እና ለእሱም ተጠያቂ የሚሆነው ይህ ሕጋዊ ተቋም ነው።

የንፋስ መከላከያዎች

የንፋስን ፍጥነት ለመቀነስ እና ሰብሎችን፣ አፈርን ወይም የእርሻ መሠረተ ልማትን ለመጠበቅ የተተከሉ የዛፎች ወይም የቁጥቋጦዎች ረድፎች።[97]

የአስተዳደር ዕቅድ

ከሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች ጋር ተገዢነት ለማግኘት የሚተገበሩትን ግቦች እና እርምጃዎች የሚገልጽ በአስተዳደር የተዘጋጀ ሰነድ። እርምጃዎቹ የስጋት ቅነሳ እርምጃዎችን፣ የሰብዓዊ መብቶች ጉዳዮችን ማስተካከልን፣ ለመጠን/ምርት የሚያገለግል የፍሰት ገበታ እና አሠራሮች፣ እና ለሠራተኞች/ተቀጣሪዎች ወይም ለቡድን አባላት አገልግሎት መስጠት (እንደ ሥልጠና፣ የቴክኒክ ድጋፍ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ እንቅስቃሴዎች) ሊያካትቱ ይችላሉ። የአስተዳደር ዕቅዱ እንደ የጊዜ ሰሌዳ፣ ድግግሞሽ፣ ኃላፊነት ያለው ሰው፣ የዒላማ ቡድን እና ሁኔታ ያሉ የእርምጃዎች ዝርዝሮችን ያመለክታል።

የአስተዳደር ወኪል

በኮሚቴዎች ውስጥ ለመሳተፍ፣ ተጠያቂ ለመሆን እና እንደ ሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች እና የቅሬታ አፈታት ሥርዓት ያሉ ርዕሶችን መተግበር ለመደገፍ በአስተዳደር የተሾመ የውሳኔ አሰጣጥ ኃይል ያለው ሰው።

የአቅርቦት ሰንሰለት ተዋናይ

ከምርቱ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ሽያጭ ድረስ ከሰርቲፋይድ ምርት ጋር የሚገናኝ ማንኛውም ድርጅት።

የአቅርቦት ሰንሰለት የስጋት ግምገማ (SCRA)

የምዝገባ ሂደቱ አንድ አካል ሲሆን፣ የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ፕላትፎርም የአቅርቦት ሰንሰለት ሰርቲፊኬት ባለቤት ሥራዎች ሊያስከትሉ የሚችሉትን ሊፈጠሩ የሚችሉ ስጋቶች የሚገመግምባቸው፣ እንዲሁም የሚፈለገውን የፍተሻ ዓይነትና ድግግሞሽ የሚወስንባቸው በጥያቄዎች ላይ የተመሰረተ ተከታታይ ሂደት ነው።

የአካባቢ ነጥብ

በጂኦግራፊያዊ መረጃ ሥርዓቶች (GIS ውሂብ) አማካይነት የተሰበሰበ የኬንትሮስ/ኬክሮስ መጋጠሚያዎች ጥምር። የአካባቢ ነጥብ አንድ ነጠላ የውሂብ ነጥብ ነው። የፖሊጎን መረጃ በማይገኝበት ጊዜ የእርሻ/እርሻ ክፍልን አካባቢ ለመወከል ሊያገለግል ይችላል።

የአየር ንብረት ለውጥ

የአየር ንብረት ለውጥ የሚያመለክተው በዓለም አቀፍ የሙቀት መጠን፣ ዝናብ፣ እርጥበት፣ የንፋስ አቅጣጫዎች እና ሌሎች የአየር ሁኔታዎች ላይ ለብዙ አሥርተ ዓመታት ወይም ከዚያ በላይ የሚከሰቱ ጉልህ ለውጦችን ነው። በአየር ሁኔታ ስርዓቶች ላይ የሚደረጉ እነዚህ ለውጦች በግብርና ሁኔታዎች፣ በአካባቢ እና በባህር ከፍታ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራሉ። አሁን ያሉት የአየር ንብረት ለውጥ አዝማሚያዎች በአብዛኛው የቅሪተ አካል ነዳጆችን ከመጠቀም እና የደን ጭፍጨፋን ጨምሮ በመሬት አጠቃቀም ለውጦች ምክንያት እንደ ካርቦን ዳይኦክሳይድ ያሉ የግሪንሀውስ ጋዞች ወደ ከባቢ አየር በመጨመራቸው በሰው እንቅስቃሴ የተከሰቱ ናቸው።[98]

የአየር ንብረት ለውጥ መላመድ

አሁን ያለው ወይም የሚጠበቀው የአየር ንብረት ለውጥ በሰብሎች፣ በእርሻ ሥርዓቶች፣ በሥነ-ምህዳሮች እና በኑሮ ላይ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅእኖ ለመቀነስ በእርሻ አሠራር እና በአመራር ላይ የሚደረጉ ማስተካከያዎች ናቸው።[99]

የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳ

የግሪንሀውስ ጋዝ ልቀትን ምንጮች በመቀነስ ወይም በከባቢ አየር ውስጥ ያሉ የግሪንሀውስ ጋዞች (GHGs) ክምችቶችን በማሳደግ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቀነስ የሚደረጉ የሰው ልጆች ጣልቃገብነቶች።[100]

የአፈር ኦርጋኒክ ይዘት (SOM)

በአፈር ውስጥ ከእፅዋት እና ከእንስሳት ቅሪቶች፣ ከሕይወት ያላቸው ህዋሳት እና ከተበላሹ ቁሳቁሶች የተገኙ ኦርጋኒክ ውህዶች ናቸው። SOM የአፈር ጤና ቁልፍ ባዮሎጂያዊ አመላካች ነው ምክንያቱም ማይክሮቢያል ሕይወትን፣ የንጥረ ነገር ዑደትን እና አጠቃላይ የሥነ-ምህዳር ተግባርን ይደግፋል። በተጨማሪም ወደ አፈር የሚመለሰውን እንደገና ጥቅም ላይ የዋለውን ባዮማስ እና ንጥረ ነገሮችን መጠን ያንፀባርቃል፣ ይህም ብዙውን ጊዜ በመቶኛ ይገለጻል።[101]

የአፈር ግምገማ

እንደ የአፈር ሸካራነት፣ የአፈር አወቃቀር፣ የአፈር-ሃይድሮሎጂ፣ የአፈር መገለጫ፣ ቶፖግራፊ፣ ኦርጋኒክ ይዘት፣ የእፅዋት ገጽታዎች እና የመሬት አጠቃቀሞችን በመመልከት የአፈርን ባህሪያት ለመተንተን ያለመ ሥርዓታዊ ሂደት። የአፈር ግምገማው ዓላማ የሰብል ምርጫን እና የአፈርና ውሃ አያያዝ እርምጃዎችን ለመደገፍ ነው።

የአፈር ጤና አመላካቾች

የአፈርን ለምነት፣ ምርታማነት እና አጠቃላይ ሥነ-ምህዳራዊ ሁኔታውን የሚያንፀባርቁ የሚለኩ የአፈር ባዮሎጂያዊ፣ ኬሚካላዊ ወይም አካላዊ ባህሪያት ናቸው። እነዚህ አመላካቾች የአፈርን የእፅዋት እድገትን የመደገፍ፣ ውሃን የመቆጣጠር፣ ንጥረ ነገሮችን ዑደት ለማድረግ እና ባዮሎጂካል ብዝሃነትን የመጠበቅ አቅምን ለመቆጣጠር ይረዳሉ።[102]

የእርሻ አስተዳደር

ለሰርቲፋይድ እርሻ የእርሻ እና የአስተዳደር ተግባራትን ለማቀድ እና ለማስተዳደር ኃላፊነት ያለው ሰው ወይም አካል። ይህ ሁሉንም የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች መስፈርቶች መተግበሩን የማረጋገጥ ኃላፊነት ያለበትን የእርሻ ሥራ አስኪያጅ ወይም አስተዳዳሪን ያካትታል። የእርሻ አስተዳደር የሚያመለክተው ይህንን ተግባር ለግለሰብ እርሻዎች ወይም በአንድ ባለቤት ስር ለሚገኙ ብዙ ስፍራ ያላቸው እርሻዎች የሚፈጽመውን ኃላፊነት ያለበትን የአስተዳደር አካል፣ የእርሻ አስተዳዳሪ ወይም ቴክኒካል ወኪል ነው።

የእርሻ ክፍል

የእርሻ አካል የሆነ፣ ተመሳሳይ አወቃቀር ያለው እና የተገለጹ ድንበሮች ያሉት ተከታታይ መሬት። እርሻ ሁለቱንም የግብርና እና የግብርና ያልሆኑ የእርሻ ክፍሎችን ሊያካትት ይችላል።  

የእርሻ ክፍሎች ሰርቲፋይድ ሰብሎችን፣ ሌሎች ሰብሎችን፣ የሕንፃ መገልገያዎችን፣ የጥበቃ አካባቢዎችን፣ ወዘተ ሊያካትቱ ይችላሉ። በእርሻ ክፍል ድንበሮች ውስጥ እንደ ተፈጥሮ እፅዋት፣ የውሃ አካላት እና ሌሎችም ያሉ ገጽታዎች ሊኖሩ ይችላሉ።  

A diagram of a farm system  AI-generated content may be incorrect.ሥዕላዊ መግለጫ 2. የእርሻ ክፍሎች ሥዕላዊ ማብራሪያ።

የእንስሳት ደህንነት አምስት ነጻነቶች

የእንስሳትን ደህንነት ለማረጋገጥ የሚከተሉትን አምስት ሁኔታዎች የሞያመሟላ መርህ፦

  1. ጥሩ አመጋገብ፦ እንስሳው ንጹህ የመጠጥ ውሃ እና ተስማሚ አመጋገብ በቀላሉ ማግኘት ስለሚችል ከረሃብ፣ ከጥም እና ከምግብ እጦት ነጻ ነው።

  2. ጥሩ መኖሪያ ቤት፦ እንስሳው ከተፈጥሮ የአየር ሁኔታ መጠለያ እና ምቹ የማረፊያ ቦታ ማግኘት ስለሚችል ከአካል እና ከሙቀት ምቾት ማጣት ነጻ ነው።

  3. ጥሩ ጤና፦ ተስማሚ በሆነ መከላከል እና/ወይም ፈጣን ምርመራ እና ህክምና ምስጋና ይግባውና እንስሳው ከህመም፣ ከጉዳት እና ከበሽታ ነጻ ነው።

  4. ተገቢ ባህሪ፦ እንስሳው በቂ ቦታ፣ ተገቢ መገልገያዎች እና ከአይነቱ ጋር የሚመሳሰሉ ሌሎች እንስሳት ስላሉ አብዛኛውን የተለመደ የባህሪ ሥርዓቱን መግለጽ ይችላል።

  5. ከፍርሃት እና ከጭንቀት ጥበቃ፦ አእምሯዊ ስቃይን ለመከላከል የሚያስፈልጉት ሁኔታዎች ስለተረጋገጡ እንስሳው ፍርሃት ወይም ጭንቀት አይሰማውም።[103]

የዕዳ ምርኮ (የመያዧ የጉልበት ሥራ)

አንድ ባለዕዳ የእሱ ወይም የእሷ ወይም በእሱ ወይም በእሷ ቁጥጥር ሥር ያለ ሰው ግላዊ አገልግሎቶችን ለዕዳው ዋስትና አድርጎ በማስያዝ የሚመጣ ደረጃ ወይም ሁኔታ ነው። የእነዚያ አገልግሎቶች ዋጋ በተመጣጣኝ ሁኔታ ሲገመት የዕዳውን ክፍያ ለመክፈል/ለመሰረዝ ጥቅም ላይ ካልዋለ፣ ወይም የእነዚያ አገልግሎቶች ርዝመትና ዓይነት ያልተገደበ እና ያልተገለጸ ከሆነ የዕዳ ምርኮ ይከሰታል። የዕዳ ምርኮ (የመያዧ የጉልበት ሥራ በመባልም ይታወቃል) በተለያዩ መንገዶች ሊገለጽ ይችላል። ይህ የግዳጅ ሥራ ዓይነት ነው።[104]

የእጽዋት መከለያዎች

በግብርና መልክዓ ምድር ውስጥ ወይም በዙሪያው የተመሰረቱ፣ እንደ ባዮሎጂካል ብዝሃነትን ማሳደግ፣ የአፈርን ጤና ማሻሻል (አነስተኛ የአየር ንብረትን ጨምሮ)፣ ከንፋስ፣ ከጎርፍ ወይም ከብክለት መከላከል፣ እና የአየር ንብረት ለውጥ ቅነሳን የሚደግፉ የካርቦን መምጠጫዎች ሆነው የሚያገለግሉ በርካታ የአካባቢ ጥቅሞችን ለመስጠት የተዋቀሩ የዛፎች፣ ቁጥቋጦዎች ወይም ዓመታዊ እፅዋት የእፅዋት ዞኖች።

የእፅዋት መከላከያዎች

የፀረ-ተባይ መርጨት መበታተንን ለመቀነስ ታስቦ የተሠራ እና የሚከተሉት ባህሪያት ያላቸው የእፅዋት መከላከያዎች፦

  • መከላከያዎቹ ቢያንስ ከሰብሉ ጋር ወይም (በመሬት ላይ በተመሰረቱ የፀረ-ተባይ አተገባበሮች ጊዜ) ከሚረጭበት መሳሪያ የአተገባበር ቫልቮች ከፍታ ጋር እኩል ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ መሆን አለባቸው (ከሁለቱ የትኛው የበለጠ እንደሆነ ይወሰናል)።

መከላከያዎቹ ዓመቱን ሙሉ ቅጠሎቻቸውን ከሚጠብቁ እፅዋት የተዋቀሩ ናቸው፣ ነገር ግን ለአየር ፍሰት የሚያልፉ ሲሆኑ፣ መከላከያው የፀረ-ተባይ ጠብታዎችን እንዲይዝ ያስችላል።

የኦርጋኒክ ንጥረ ነገር ምንጮች

ለሰብሎች ንጥረ ነገሮችን የሚያቀርቡ እና የአፈርን ለምነትና አወቃቀር የሚያሻሽሉ ከሕይወት ያላቸው ህዋሳት ወይም ከጎንዮሽ ምርቶቻቸው የተገኙ ይዘቶች ናቸው። እነዚህም የተፈጥሮ ማዳበሪያ (ኮምፖስት)፣ የእንስሳት ፍግ፣ የሰብል ቅሪቶች እና መሸፈኛ ሰብሎችን ያካትታሉ። አጠቃቀማቸው የረዥም ጊዜ የአፈር ጤናን ያሻሽላል እና በሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎች ላይ ጥገኝነትን ይቀንሳል።[105]  

የዋና መንስኤ ትንተና

የተገዢነት ጉድለቶች ወይም ችግሮች ዋና መንስኤዎችን ለመለየት የሚያገለግል ዘዴ ሲሆን፣ የተለየው ችግር በሌላ ስፍራ ተከስቶ እንደሆነ ለማወቅ የችግሩን ስፋት እና መጠን መገምገምን ያካትታል።[106]

የውሃ ውስጥ ሥነ ምህዳሮች

የሚፈስ እና የረጋ ውሃ አካላት እንዲሁም ሌሎች እርጥብ መሬቶች። ይህ የሚከተሉትን ያካትታል፦

የሚፈስ እና የረጋ ውሃ አካላት፦ በተፈጥሮ የሚገኙ ሁሉም ጅረቶች፣ ወንዞች፣ ኩሬዎች፣ ሐይቆች እና ባሕረ ገብ፣ እንዲሁም በአብዛኛው ዓመታት ቢያንስ ለሁለት ወራት ያለማቋረጥ የሚፈሱ ወይም አልፎ አልፎ የሚፈሱ እና ቢያንስ አንድ ሜትር ስፋት ያላቸው ወቅታዊ ጅረቶች። በደለል ክምችት፣ በተበከለ ፍሳሽ፣ በወንዝ ዳር የአፈር መሸርሸር፣ በሙቀት ብክለት፣ ወይም ከአንድ ሜትር በታች ከፍታ ባላቸው ግድቦች የተለወጡ ጅረቶች እና ወንዞች አሁንም እንደ የውሃ ውስጥ ተፈጥሯዊ ሥነ ምህዳሮች ይቆጠራሉ። ሰው ሰራሽ ኩሬዎች፣ የውሃ ማከሚያ ባሕረ ገብ እና የመስኖ ኩሬዎች ተፈጥሯዊ የውሃ ውስጥ ሥነ ምህዳሮች ተብለው አይቆጠሩም፣ እነዚህ የውሃ አካላት፦ ሀ) በመጥፋት ስጋት ላይ ባሉ እንስሳትና አፅዋት ካልተያዙ/ሰፍረውባቸው ካልሆነ እና/ወይም ለ) የውሃ አካሉ የዓሣ ወይም የዱር አራዊት መኖሪያ ለመሆን ተብሎ ካልተገነባ በስተቀር።

ሌሎች እርጥብ መሬቶች፦ በተፈጥሮ የሚገኙ ሁሉም ረግረጋማ ቦታዎች ሲሆኑ፣ የተፈጥሮ የውሃ ​​ሁኔታዎች ከሚከተሉት ሁለት ሁኔታዎች አንዱን ወይም ሁለቱንም የሚያስከትሉ ናቸው፦

  • አፈሩ ለአብዛኛው ዓመት በውሃ የተሞላ ከሆነ።

  • ጎርፍ ሜዳዎች፣ ኩሬዎችን፣ ጅረቶችን ወይም ውቅያኖስን የሚዋሰኑ እርጥብ ቦታዎችን ጨምሮ መሬቱ በየጊዜው ወይም በቋሚነት ጥልቀት በሌለው ውሃ የተጥለቀለቀ ከሆነ።

ለሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች ዓላማዎች፣ የሚከተሉት እንደ የውሃ ውስጥ ተፈጥሯዊ ሥነ ምህዳሮች አይቆጠሩም፦

  • በሰው እንቅስቃሴ ምክንያት በየወቅቱ ወይም በቋሚነት እርጥብ የሆኑ አካባቢዎች (ለምሳሌ የፍሳሽ ማስወገጃ ቦዮች፣ የመስኖ ኩሬዎች፣ የውሃ ማጠራቀሚያዎች፣ የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ኩሬዎች፣ የዓሣ ማጥመጃ ኩሬዎች፣ የሩዝ እርሻዎች፣ ወይም የጠጠር ማውጫ ቦታዎች)፣ የሚከተሉት ካልሆኑ በስተቀር፦

ሀ) እነዚህ የውሃ አካላት በመጥፋት ስጋት ላይ ባሉ እንስሳትና አፅዋት የተያዙ/ሰፍረውባቸው ከሆኑ።

ለ) እርጥብ መሬቱ በሰው የተፈጠረው የእርጥብ መሬት መኖሪያ ለመሆን ከሆነ።

የውሃ ዳርቻ ጥበቃ ቀጠና

በወንዞች፣ በጅረቶች እና በሌሎች የውሃ አካላት ዳርቻዎች ላይ የሚገኝ ዘላቂ እፅዋት (ዛፎች፣ ቁጥቋጦዎች እና ሳሮች) ያለው አካባቢ ሲሆን፣ ሰብሎች እና እንስሳት የማይገኙበት አካባቢ ነው። እነሱ ብክለቶችን የሚያጣሩ፣ ዳርቻዎችን የሚያረጋጉ፣ ለዱር እንስሳት መኖሪያ የሚሰጡ እና የውሃ ሙቀትን የሚቆጣጠሩ፣ አጠቃላይ የውሃ ጥራትን የሚያሻሽሉ የመከላከያ ቀጠናዎች ሆነው ያገለግላሉ።[107]

ደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ

የሰው ልጆች ወዲያውኑም ሆነ በረዥም ጊዜ የጉዳት ስጋት ሳይደርስባቸው ሊጠቀሙት የሚችሉት የጥራት ደረጃ ያለው ውሃ ነው።

በWHO መሰረት የደህንነቱ የተጠበቀ የመጠጥ ውሃ መመዘኛዎች እንደሚከተለው ናቸው፦

መመዘኛ

ዋጋ

ኢ. ኮላይ ወይም ቴርሞ-ታጋሽ ኮሊፎርም ባክቴሪያ

በማንኛውም የ100-ሚሊ ናሙና ውስጥ የማይታወቅ

ክሎሪን ተረፈ ምርት ወይም ከሌሎች የሕክምና ኬሚካሎች የተረፈ ምርት

ቢበዛ 0.5 ሚ.ግ./ሊ

ፒኤች (pH)

ሶዲየም

ናይትሬቶች

6.5 እስከ 8.5

ቢበዛ 200 ሚ.ግ./ሊ

ቢበዛ 10 ሚ.ግ./ሊ እንደ ናይትሬትስ

ሰልፌቶች

ደብዛዛነት

ቢበዛ 250 ሚ.ግ./ሊ

ከ5 NTU (Nephelometric Turbidity Unit) ያነሰ ወይም እኩል

ደመወዝ

በገንዘብ የሚገለጽ እና በጋራ ስምምነት ወይም በብሔራዊ ሕጎች ወይም ደንቦች የተወሰነ ክፍያ ወይም ገቢ። ደመወዝ በአሠሪ ለሠራተኛ/ተቀጣሪ ለተሠራ ወይም ለሚሠራ ሥራ ወይም ለተሰጠ ወይም ለሚሰጥ አገልግሎት የሚከፈል ነው።

ደን

ከ0.5 ሄክታር በላይ ስፋት ያለው፣ ከ5 ሜትር በላይ ከፍታ ያላቸው ዛፎች እና ከ10 በመቶ በላይ የዛፍ ሽፋን ያለው መሬት፣ ወይም በእነዚህ ደረጃዎች መድረስ የሚችሉ ዛፎች ያሉበት ቦታ። በዋናነት በግብርና ወይም በሌላ የመሬት አጠቃቀም ስር ያለ መሬትን አይጨምርም።  

ደን የተፈጥሮ ደኖችን እና የዛፍ እርሻዎችን ያካትታል። በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን አውድ ውስጥ ከደን ጭፍጨፋ የጸዳ የአቅርቦት ሰንሰለቶችን ለመተግበር፣ ትኩረቱ የተፈጥሮ ደኖች ልወጣን መከላከል ላይ ነው።[108]

ድህረ ምርት

ምርቱ ከተሰበሰበ በኋላ ወዲያውኑ የሚከተለው የሰብል ምርት ደረጃ። ይህ አያያዝ፣ ማጽዳት፣ ማከማቸት፣ መደርደር፣ ማቀነባበር፣ ማሸግ እና ማጓጓዝን ሊያካትት ይችላል።

ድርብ ሽያጭ

ሰርቲፋይድ ተብሎ የተመረተውን ወይም የተገዛውን ተመሳሳይ የምርት መጠን ሁለት ጊዜ የመሸጥ ልምምድ፣ አንዴ በሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርድ እና እንደገና በሌላ የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርድ፣ በሌላ ሰርቲፊኬሽን ሥርዓት ወይም እንደ ተራ ምርት መሸጥ።

ለምሳሌ፣ በአንድ እርሻ የተመረተ 100 ሜትሪክ ቶን ቡና በሁለቱም እንደ ኦርጋኒክ እና የሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው የግብርና ስታንዳርድ ሰርቲፋይድ ሊሆን ይችላል እና የሚከተለውን ሆኖ ሊሸጥ ይችላል፦

  • 100 ሜትሪክ ቶን በሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው የግብርና ስታንዳርድ ሰርቲፋይድ ብቻ፣ ወይም

  • 100 ሜትሪክ ቶን ኦርጋኒክ ብቻ፣ ወይም

  • 100 ሜትሪክ ቶን በሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው የግብርና ስታንዳርድ እና ኦርጋኒክ (በአንድ ጊዜ በአንድ ስብስብ ውስጥ) ለአንድ ገዢ።

ይሁን እንጂ፣ ያው የቡና መጠን ለብቻው 100 ሜትሪክ ቶን ኦርጋኒክ ቡና እንዲሁም 100 ሜትሪክ ቶን በሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው የግብርና ስታንዳርድ ወይም ታዳሽ (Regenerative) ግብርና ሰርቲፋይድ ቡና ተለይቶ ሊሸጥ አይችልም።

ድርብ ሽያጭ በሬንፎረስት አሊያንስ ህጎች አይፈቀድም።

ድንገተኛ አደጋ

በተወሰነ ሁኔታ እና/ወይም ቦታ ላይ ለጤና፣ ለሕይወት፣ ለመተዳደሪያ፣ ለሰብአዊ መብቶች፣ ለንብረት ወይም ለአካባቢው አፋጣኝ ስጋት የሚያስከትል ክስተት።

ድንገተኛ ኦዲት

ያልታወቀ ኦዲት በመባልም የሚታወቅ ሲሆን፣ ኦዲት ለሚደረግበት ድርጅት ቅድሚያ ማሳሰቢያ ሳይሰጥ የሚደረግ ኦዲት ነው። ይህ ዓይነቱ ኦዲት በመደበኛነት በሚደረጉ፣ የጊዜ ሰሌዳ ባላቸው ኦዲቶች ጊዜ ግልጽ ላይሆኑ የሚችሉ ልዩነቶችን ወይም የተገዢነት ጉድለት ያለባቸውን አካባቢዎች ለመለየት ይረዳል።

የውሂብ ነጥብ

ከአመላካች ጋር የተገናኘ እና በሰርቲፊኬት ባለቤት እና/ወይም በአምራች ለትንተና እንዲሰበሰብ የሚፈለግ መረጃ ወይም የተወሰነ ዋጋ።

የውስጥ አስተዳደር ሥርዓት (IMS)

ለቡድኑ ቀልጣፋ ድርጅት እና አስተዳደር ለማመቻቸት እንዲሁም ቡድኑ እና የቡድን አባላት የሚመለከታቸውን የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች መስፈርቶች ማክበራቸውን ለማረጋገጥ ያለመ በሰነድ የተደገፈ የጥራት አስተዳደር ሥርዓት ነው።

የውስጥ ኢንስፔክሽን

የእርሻ ወሰን፦ ሁሉንም የቡድን አባላት እርሻዎች እና የእርሻ ክፍሎች ከሁሉም አግባብነት ካላቸው የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች መስፈርቶች ጋር ያላቸውን ተገዢነት የሚያጣራ በቡድን አስተዳደር የተሾመ ሰው (የውስጥ ኢንስፔክተር) የሚያከናውነው የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ ወገን ኦዲት ነው።

የአቅርቦት ሰንሰለት ወሰን፦ በሰርቲፊኬሽን ወሰን ውስጥ የተሸፈኑትን ሁሉም አካላት ከሁሉም አግባብነት ካላቸው የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች መስፈርቶች ጋር ያላቸውን ተገዢነት የሚያጣራ በአስተዳደር የተሾመ ሰው (የውስጥ ኢንስፔክተር) የሚያከናውነው የመጀመሪያ ወይም ሁለተኛ ወገን ኦዲት ነው።

የውጪ ኦዲት

የሰርቲፊኬት ባለቤቶች ከሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች ጋር ያላቸውን ተገዢነት ለመገምገም በሦስተኛ ወገን ሰርቲፊኬሽን አካል የሚካሄድ ገለልተኛ ኦዲት ነው።

የዘመን መቁጠሪያ ዓመት

ከጃኑዋሪ 1 ጀምሮ እስከ ዲሴምበር 31 ድረስ ያለው፣ በግሪጎሪያን የዘመን አቆጣጠር ላይ የተመሠረተ ተከታታይ የ12 ወራት ጊዜ።

የይዘት ደህንነት መረጃ ወረቀት (MSDS)

ከምርቱ/ንጥረ ነገሩ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ለሥራ ቦታ ደህንነት እና ጤና ተገቢውን መረጃ የሚሰጥ ሰነድ። ይህ ለአስተማማኝ አጠቃቀም መመሪያዎችን፣ የአያያዝ መመሪያዎችን፣ ተገቢውን PPE፣ ከአንድ የተወሰነ ይዘት ወይም ምርት ጋር የተያያዙ እምቅ አደጋዎችን፣ እንዲሁም የመፍሰስ አያያዝ ሂደቶችን ያካትታል ነገር ግን በእነዚህ ብቻ አይወሰንም።

የደን ጭፍጨፋ

ተፈጥሯዊ ደንን ወደ ግብርና ወይም ወደ ሌላ የመሬት አጠቃቀም መለወጥ።

የአውሮፓ ህብረት የደን ጭፍጨፋ ደንብ ተገዢነት፦ ደን ወደ ግብርና አገልግሎት መለወጥ፣ በሰው ሰራሽም ሆነ በተፈጥሮ አደጋዎች (ለምሳሌ በእሳት ከዚያም ወደ እርሻ መሬት ሲለወጥ) የተፈጠሩ ሁኔታዎችን ያካትታል።[109]

የዱር እንስሳት

በዋናነት በሰው ዘንድ እንደ ከብት ወይም የቤት እንስሳት ተብለው ከሚያዙት በስተቀር ሁሉም የየብስ አከርካሪ አጥንት ያላቸው እንስሳት ዝርያዎች።

የዱር እንስሳት ተባይ

በሰብሎች፣ በእፅዋት ወይም በእፅዋት ምርቶች ጉዳት የሚያደርስ ከተፈጥሮ ሥነ-ምህዳሮች የተገኘ ማንኛውም አከርካሪ አጥንት ያለው እንስሳ ዝርያ። እነዚህ ተባዮች ምርትን ሊቀንሱ፣ የምርት ጥራትን ሊነኩ እና የግብርና ሥርዓቶችን ሊያበላሹ ይችላሉ፣ ይህም ቁጥጥርን ከጥበቃ ጋር የሚያመዛዝኑ የአስተዳደር ስልቶች አስፈላጊ ያደርገዋል።[110]

የድጋፍ ዕውቅና

የድጋፍ ዕውቅና ማለት የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ፕሮግራምን ለመቀላቀል ለአቅርቦት ሰንሰለት ሰርቲፊኬት ባለቤት በሬንፎረስት አሊያንስ በቀጥታ የሚሰጥ ፈቃድ ነው።

የጂኦሎኬሽን ውሂብ

የእርሻዎችን ጂኦግራፊያዊ አካባቢ እና የእርሻዎችን፣ የእርሻ ክፍሎችን እና ሌሎች የሰርቲፊኬት ባለቤቶችን መገልገያዎችን ድንበሮች የሚለይ ውሂብ። የጂኦሎኬሽን ውሂብ የሚወከለው በጂኦአቀማመጥ ሥርዓቶች (GPS) ካርታ በመጠቀም በተሰበሰቡ መጋጠሚያዎች ሲሆን፣ እነዚህም የግለሰብ አካባቢ ነጥቦችን (ፖስታዎችን ጨምሮ) ወይም የአግባብነት ያለውን አካባቢ ሙሉ ድንበሮችን የሚገልጹ ባለ ብዙ ጎኖችን (ፖሊጎኖችን) መጠቀም ይችላሉ።

የጅምላ ሚዛን

ተመጣጣኝ መጠን ያለው ምርት የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ሆኖ ሲገኝ፣ ሰርቲፊኬት ባለቤቱ ሰርቲፋይድ ያልሆነውን ምርት እንደ ሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ተደርጎ ሊያቀርብ የሚፈቅድ የአስተዳደር የትረሰቢሊቲ ዘዴ።

የገበያ ዋጋ

በተለመደው (ማለትም ሰርቲፋይድ ባልሆነ) መንገድ ለተመረተ ተመሳሳይ ጥራት እና ምንጭ ላለው ምርት በተለምዶ የሚከፈለው ዋጋ።

የጉልበት ሠራተኛ መብቶች/

የሠራተኛ መብቶች

ለሠራተኞች/ተቀጣሪዎች በሥራ ቦታ የተሰጡ መብቶች እና ጥበቃዎች፣ በፍትሃዊ እና ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ውስጥ መሥራታቸውን ያረጋግጣል። እነዚህ መብቶች ግለሰቦችን ከብዝበዛ፣ ከአድልዎ እና ደህንነቱ ካልተጠበቀ የሥራ አካባቢ ለመጠበቅ የተነደፉ ሲሆኑ፣ ፍትሃዊ ካሳ እና የመደራጀት ወይም የሠራተኛ ማህበራት የመፍጠር ችሎታን ያረጋግጣሉ።[111]

የግል መከላከያ መሳሪያዎች (PPE)

ሕመም ወይም ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ አደጋዎች እንዳይጋለጡ ለመቀነስ የሚለበሱ ልብሶች ወይም መሳሪያዎች። እንዲህ ያሉ አደጋዎች ኬሚካላዊ፣ ባዮሎጂያዊ፣ ራዲዮሎጂያዊ፣ አካላዊ፣ ኤሌክትሪክ፣ ሜካኒካዊ ወይም ሌላ ዓይነት ሊሆኑ ይችላሉ። የግል መከላከያ መሳሪያዎች እንደ ጓንቶች፣ የደህንነት መነጽሮች እና ጫማዎች፣ የጆሮ መዝጊያ ወይም መከላከያ፣ ጠንካራ ኮፍያዎች፣ የመተንፈሻ መሣሪያዎች፣ ወይም የሥራ ልብሶች፣ ቬስቶች እና ሙሉ የአካል ልብሶችን ያካትታል።[112]

የግዳጅ ሥራ

ማንኛውም ሰው በቅጣት ማስፈራሪያ የሚሠራው እና ግለሰቡ በፈቃደኝነት ራሱን ያላቀረበበት ሥራ ወይም አገልግሎት።

አንድ ሰው በግዳጅ ሥራ ውስጥ እንዳለ የሚመደበው ሥራው ያለፈቃድ (ያለሠራተኛው/ተቀጣሪው ነፃ እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ ፈቃድ) ከሆነ እና በማስፈራራት፣ በቅጣት ወይም በሆነ ዓይነት ግዳጅ የሚፈጸም ከሆነ ነው።

የፍቃደኝነት እጦት ዓይነቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ይችላሉ እንጂ በእነዚህ ብቻ አይወሰኑም፦

  • እንደ ባርነት ወይም የዕዳ ምርኮ በመሰለ ግብይት አማካኝነት መመልመል።

  • በILO ስምምነት 29 ላይ ከተሰጡት ልዩ ሁኔታዎች ጋር የማይጣጣም በግዛት የተጫነ ሥራ፣ ለምሳሌ በወታደራዊው የሚሰጥ ሥራ።

  • ያልተፈለገ/በግዳጅ የሚደረግ የእስር ቤት የጉልበት ሥራ።

  • የማይከፈልበት ወይም እጅግ በጣም አነስተኛ ክፍያ ያለው ሥራ።

  • ያለሠራተኛው/ተቀጣሪው ፈቃድ የሥራ ሁኔታዎችን መለወጥ (ቀጣሪ፣ ደመወዝ፣ ሰዓታት፣ የሥራ ባህሪ፣ ሁኔታዎች/አደጋዎች/ተጋላጭነቶች፣ የጊዜ ገደብ)።

  • በቀጣሪ ወይም በቅጥር ወኪል የተጫነ አዋራጅ የሥራ ወይም የኑሮ ሁኔታዎች።

  • ያልተፈለገ እና ከመጠን ያለፈ የትርፍ ሰዓት።

  • የሥራ ውልን ወይም ስምምነትን ለማቋረጥ የተገደበ ነፃነት።

የግዳጅ ዓይነቶች የሚከተሉትን ሊያካትቱ ነገር ግን በእነዚህ ብቻ አይወሰኑም፦

  • አካላዊ ወይም ጾታዊ ጥቃት።

  • አካላዊ እስራት።

  • በእንቅስቃሴ ወይም በግንኙነት ላይ ገደቦች።

  • ገንዘብ ነክ ቅጣቶች ወይም ሌሎች የገንዘብ ቅጣቶች።

  • ምግብ፣ ውሃ፣ መጸዳጃ ቤት፣ እንቅልፍ ወይም ሌሎች መሠረታዊ ፍላጎቶችን መከልከል።

  • ብቸኝነት።

  • በግዳጅ ዕፅ ወይም አልኮል መጠቀም።

  • የዕዳ ምርኮ ወይም የዕዳ ማጭበርበር፣ ቅድመ ክፍያዎችን እና ብድሮችን ማጭበርበርን ጨምሮ።

  • የቅጥር ቅድመ ሁኔታ አድርጎ የገንዘብ ማስያዣ፣ የፋይናንስ ወይም የዋስትና ማረጋገጫዎች፣ ወይም የግል ንብረቶች መጠየቅ።

  • ደመወዝ ወይም ሌሎች ጥቅማጥቅሞችን መከልከል ወይም ማዘግየት።

  • የሠራተኛው/ተቀጣሪው ፈቃድ ሳይኖር መታወቂያ ወይም ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶችን መያዝ እና/ወይም ሠራተኞች/ተቀጣሪዎች በቀላሉ እንዳያገኟቸው ማድረግ።

ከሥራ የመቀነስ፣ የመባረር፣ የሕጋዊ እርምጃ ወይም ለባለሥልጣናት ሪፖርት የማድረግ ማስፈራሪያዎች።[113]

የጠፋ ምርት

ለሽያጭ የማይቀርብ እስከሚሆነ ድረስ የተበላሸ ምርት።

የጥላ ዛፍ

ሰርቲፋይድ በሆነው ሰብል ላይ በአንድ የእርሻ ክፍል ውስጥ የጥላ ሽፋን የሚሰጡሰፋ ያሉ የእንጨት ዓይነት ያላቸው ዘላቂ ዛፎች። የጥላ ዛፎች የተለያዩ የሥነ-ምህዳር አገልግሎቶችን ይሰጣሉ፣ ለምሳሌ የባዮሎጂካል ብዝሃነት ጥበቃ እና መሻሻል፣ የአፈር ለምነት መጨመር፣ የተባዮች እና በሽታዎች ቁጥጥር፣ አነስተኛ የአየር ንብረት መቆጣጠር፣ የካርቦን ማስቀመጥ እና የውሃና አፈር ጥበቃ። የጥላ ዛፎች እንደ ፍራፍሬ፣ እንጨት ወይም ሌሎች ምርቶች ያሉ የኢኮኖሚ ጥቅሞችንም ሊሰጡ ይችላሉ።[114]

የፀረ-ተባዮች መርዛማነት

በሕይወት ባሉ ፍጥረታት፣ ሰዎችን፣ እንስሳትን፣ እፅዋትን ወይም አካባቢን ጨምሮ፣ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን የመፍጠር የፀረ-ተባይ አቅም። እንደነዚህ ያሉት ተፅዕኖዎች ተግባራዊ መዛባት፣ በሽታ አምጪ ቁስሎች ወይም አንድ አካል ለጭንቀት ምክንያቶች ምላሽ የመስጠት አቅም መቀነስ በመሆን ሊገለጡ ይችላሉ። የጉዳቱ መጠንና ዓይነት የሚወሰነው በፀረ-ተባዩ ባህሪ፣ በአሠራሩ፣ በመጠኑና ለመጋለጥ በሚደረግበት መንገድ ላይ ነው። ስለዚህ፣ የመርዝነት ደረጃ የፀረ-ተባይ አጠቃቀም ተጽዕኖን በመገምገም እና በመቀነስ ሂደት ውስጥ ቁልፍ አካል ነው።

ጂኦግራፊያዊ ክልል

ብዙ ስፍራ ላላቸው የአቅርቦት ሰንሰለት ሰርቲፊኬት ባለቤቶች ሰርቲፊኬቶች ሊሰጡ የሚችሉበትን ወሰን የሚወስን የተወሰነ የአገራት ስብስብ።

ጉልህ ስጋት

ሊከሰት የሚችልበት ዕድል ከፍተኛ የሆነ እና በዓላማዎች ላይ አስተማማኝ ተፅዕኖ ያለው ስጋት። ይህ ዓይነቱ ስጋት ከፍተኛ ጉዳት ወይም መስተጓጎል ሊያስከትል ስለሚችል ልዩ ትኩረት እና አስተዳደር ይፈልጋል።

ጉቶ ላይ መቁረጥ

ምርታማ ያልሆኑ የዛፍ ሰብል ግንዶችን ወይም ዋና ግንዶችን እንደገና በመቁረጥ ከጉቶው አዲስ እድገት እንዲኖር በማድረግ ሳይተኩ ለማደስ እና ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመ አሠራር ነው።

ጊዜ ያለፈባቸው ደንቦች፣ ህጎች

ቃሉ አግባብነት የሌለው ወይም ተፈጻሚነቱን ያጣ በመሆኑ ምክንያት በጊዜ ሂደት ተግባራዊ መሆን ላቆመ ሕግ የሚያገለግል ነው። ይህ የሚሆነው ለማውጣት ምክንያት የሆነው ምክንያት አልፎ፣ ወይም የሕጉ ርዕሰ ጉዳይ ከእንግዲህ ሳይኖር፣ ወይም ለተለወጡ ሁኔታዎች ተፈጻሚነት ሳይኖረው፣ ወይም በግልጽ ሳይሻር ወይም ሳይሰረዝ በሁሉም ሰዎች በዝምታ ችላ ሲባል ነው። አንድ ደንብ ወይም ሕግ ጊዜ ያለፈበት መሆኑን የሚያረጋግጥ ማንኛውም ውሳኔ በሬንፎረስት አሊያንስ ቅድሚያ መጽደቅ አለበት።

ጊዜ ያለፈባቸው ፀረ-ተባዮች

ምዝገባቸው የተሰረዘ፣ የተሻረ ወይም የታገደ እና ለታቀደው ዓላማ ሊውሉ የማይችሉ ፀረ-ተባዮች። ስለዚህም በቁጥጥር መስፈርቶች መሠረት በአስተማማኝ ሁኔታ መወገድ አለባቸው።[115]

ጊዜያዊ ሠራተኛ/

ተቀጣሪ

የሥራ ውል ወይም የሚጠበቀው የሥራ ጊዜ ከ12 ወራት በታች የሆነ ሠራተኛ/ተቀጣሪ።

ግምገማ-እና-ማስተካከያ

የሰርቲፊኬት ባለቤቶች የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ፣ የግዳጅ ሥራ፣ የአድልዎ እና የሥራ ቦታ ጥቃትና ትንኮሳ ስጋቶችን የሚለዩበት፣ የሚያቀዘቅዙበት እና የሚቆጣጠሩበት፣ ከዚያም የሚከሰቱ አጋጣሚዎችን የሚያስተካክሉበት የአስተዳደር ሥርዓት። ይህ አቀራረብ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች እነዚህን ጉዳዮች ለመለየት እና ለመፍታት በጊዜ ሂደት ዘላቂነት ያለው አቅም እንዲገነቡ ያነሳሳል።

ግሪንሀውስ ጋዞች (GHGs)

ሙቀትን ወይም ረዥም ሞገድ ጨረርን በከባቢ አየር ውስጥ የሚያጠምዱ ውሁድ ጋዞች። በከባቢ አየር ውስጥ መኖራቸው የምድርን ገጽ የበለጠ ያሞቀዋል። የሰው እንቅስቃሴዎች ለGHGs ዋናው ምንጭ ናቸው። የቅሪተ አካል ነዳጅ ማቃጠል፣ የደን ጭፍጨፋ፣ ከፍተኛ የእንስሳት እርባታ፣ ሰው ሰራሽ ማዳበሪያዎችን መጠቀም እና የኢንዱስትሪ ሂደቶች ሁሉም አስተዋፅኦ ያደርጋሉ።

ጤና እና ደህንነት

በሥራ ቦታዎች ወይም በሕዝብ አካባቢዎች አደጋዎችን ወይም ጉዳቶችን ለመከላከል፣ የሠራተኞች/ተቀጣሪዎች ደህንነት፣ ጤና እና ደኅንነት ጋር የተያያዙ ሕጎች፣ ደንቦች፣ መርሆዎች እና አሠራሮች።

እንዲሁም ይህ በሥራ ቦታ ውስጥ እና ከዛ ውጭ ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ደህንነት ለማግኘት የስራ ቦታ ጤና እና ደህንነት (OHS) እና ከስራ ቦታ ወጭ ጤና እና ደህንነት ተብሎም ይጠራል።

ጥላን የሚቋቋም ሰብል

ሙሉ ወይም ከፊል ጥላ ስር መኖር የሚስማማው የሰብል ዝርያ።

ጥምር እርሻ

በተመሳሳይ መሬት ላይ ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ የእንጨት እጽዋት (ዛፎች፣ ቁጥቋጦዎች፣ ፓልሞች) ከግብርና ሰብሎች ወይም ከብቶች ጋር ሆን ተብሎ የሚያዋህድ የመሬት አያያዝ ዘዴ ነው። ይህ የተለያየ ስርዓት ምርታማነትን መጨመር፣ የተሻሻለ የአፈር ጤና፣ የባዮሎጂካል ብዝሃነት መጨመር፣ የአየር ንብረት መቋቋም እና ለውሃ ጥበቃ እና ለካርቦን ክምችት አስተዋፅኦን ጨምሮ በርካታ ጥቅሞችን ይሰጣል።[116]

ጥበቃ

የተፈጥሮ ሥነ ምህዳርን በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ በሰው ከመለወጥ ወይም ከመበላሸት መጠበቅ። ተፈጥሯዊ ሥነ ምህዳሮች በማንኛውም ጥብቅ ጥበቃ፣ መልሶ መቋቋም ወይም ዘላቂነት ባለው አስተዳደር ጥምረት ሊጠበቁ ይችላሉ።

ፀረ-ተባይ

በምግብ እና በግብርና ምርቶች ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ወይም በማምረት፣ በማቀነባበር፣ በማከማቸት፣ በማጓጓዝ ወይም በገበያ ላይ ጣልቃ የሚገቡ ተባዮችን እና የማይፈለጉ የእፅዋት ወይም የእንስሳት ዝርያዎችን ለመከላከል፣ ለማጥፋት ወይም ለመቆጣጠር የታሰበ ማንኛውም ኬሚካላዊ ወይም ባዮሎጂያዊ ንጥረ ነገር ወይም የንጥረ ነገሮች ድብልቅ። ቃሉ እንደ ቅጠል ማራገፊያዎች፣ ማድረቂያዎች ወይም የፍራፍሬ ማቅጠኛ ወይም ያለጊዜው መርገፍን የሚከላከሉ ወኪሎች ሆነው የሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮችንም ያጠቃልላል።

ፀረ-ተባዮች ምርቶቹን በማከማቻ እና በማጓጓዝ ጊዜ ከጥፋት ለመጠበቅ ከሰብል መሰብሰብ በፊት ወይም በኋላ ሊተገበሩ ይችላሉ።[117]

ፀረ-ነፍሳት

በእፅዋት፣ በግብርና ምርቶች፣ በተከማቹ ምግቦች ወይም በጌጣጌጥ እፅዋት ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ነፍሳትን እና ሌሎች አርትሮፖዶችን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር ወይም ለማስወገድ የተነደፉ ኬሚካላዊ ወይም ባዮሎጂካል ንጥረ ነገሮች። አጠቃቀማቸው ምርታማነትን ለመጠበቅ፣ የምርት ኪሳራን ለመቀነስ፣ የምርት ጥራትን ለማሻሻል እና ጉዳትን ለመከላከል ያለመ ነው።[118]

ፆታ

እንደ የመራቢያ አካላት፣ ክሮሞሶሞች፣ ሆርሞኖች የመሳሰሉ የወንዶች እና የሴቶች የተለያዩ ባዮሎጂያዊ እና ፊዚዮሎጂያዊ ባህሪያት። ከቀዶ ጥገና ውጭ የሆነ፣ ሁለንተናዊ እና በአብዛኛው የማይለወጥ ነው።[119]

ጾታዊ ትንኮሳ

ለተቀባዩ የማይፈለግ እና አስጸያፊ የሆነ በፆታ ላይ የተመሰረተ ምግባር። ጾታዊ ትንኮሳ እንዲኖር እነዚህ ሁለት ሁኔታዎች መኖር አለባቸው፦

"Quid Pro Quo" (በምላሹ የሆነ ነገር) ማለት የሥራ ጥቅም - እንደ የደመወዝ ጭማሪ፣ እድገት ወይም ሥራ ላይ መቆየት - ተጎጂው በአንዳንድ ጾታዊ ባህሪ ውስጥ እንዲሳተፍ በሚያደርጉ ፍላጎቶች ላይ የተመሰረተ ሲሆን ነው።

ምግባሩ ለተጎጂው አስፈሪ ወይም አዋራጅ ሁኔታዎችን የሚፈጥርበት ጠላትነት የሰፈነበት የሥራ አካባቢ።

ጾታዊ ትንኮሳ ተብሎ ሊመደብ የሚችል ባህሪ፦

  • አካላዊ፦ ጥቃት፣ መንካት፣ አስፈላጊ ያልሆነ ቅርበት።

  • የቃል፦ ስለ አካላዊ ገጽታ፣ የአኗኗር ዘይቤ፣ ጾታዊ ንባሌ የሚሰጡ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች እና አጸያፊ የስልክ ጥሪዎች።

  • የቃል ያልሆነ፦ ማፏጨት፣ጾታዊ ስሜት ቀስቃሽ የእጅ ምልክቶች፣ የወሲባዊ ይዘት ያላቸው ቁሳቁሶችን ማሳየት።[120]

ፈንገስ ማጥፊያ

በእፅዋት፣ በግብርና ምርቶች፣ በተከማቹ ምግቦች ወይም በጌጣጌጥ እፅዋት ላይ የሚገኙ ፈንገሶችን እና ስፖሮቻቸውን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር ወይም ለማስወገድ የተነደፉ የኬሚካል ንጥረ ነገሮች ወይም ባዮሎጂካል ወኪሎች።[121]  

ፍሰት  

ወደ አፈር ውስጥ የማይገባ ነገር ግን በመሬቱ ገጽታ ላይ የሚፈስ ውሃ ነው። ፍሰት አፈርን፣ ማዳበሪያዎችን እና ፀረ-ተባይ መድኃኒቶችን ከሜዳዎች ሊወስድ ይችላል፣ ይህም የአፈር ለምነትን የሚቀንስ እና በአቅራቢያ ያሉ ወንዞችን፣ ሐይቆችን ወይም ሌሎች የውሃ አካላትን የመበከል እምቅ ኃይል ያለው ነው።[122]

ፍሳሽ

የሰገራ ንጥረ ነገሮችን የያዙ ቆሻሻ ውኃ እና ቆሻሻ ድፍድፎች። ከመጸዳጃ ቤቶች የሚወጣውን ፈሳሽ የሚያካትት ማንኛውም የቆሻሻ ውሃ ፍሰት፣ ከግሬይዋተር ጋር የተቀላቀለ ወይም ያልተቀላቀለ፣ እንደ ፍሳሽ ይቆጠራል።

ፕሪሚየም

የሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂ ግብርና እና/ወይም መልሶ አልሚ ግብርና ሰርቲፋይድ መጠኖችን ገዢዎች ለአምራች የእርሻ ሰርቲፊኬት ባለቤት የሚከፍሉት በገበያ ዋጋ፣ በጥራት ፕሪሚየሞች ወይም በሌሎች ልዩነቶች ላይ የሚጨመር ተጨማሪ የገንዘብ ክፍያ።

ፖሊጎን (ጂኦግራፊያዊ ፖሊጎኖች)

የእርሻውን/እርሻውን ክፍል የሚወክል አካባቢን የሚከብ የጂኦግራፊያዊ ወሰን። እንደነዚህ ያሉት ፖሊጎኖች ተቀርፀው የእርሻውን አስፈላጊ ውሂብ (እንደ እርሻ መታወቂያ፣ የእርሻ ስፋት (ሄክታር)፣ የምርት አካባቢ፣ ሰብል፣ ባለቤት፣ ሰርቲፊኬሽን ሁኔታ) ባሉ ባህሪያት ሊመሰጠሩ ይችላሉ።

ሌሎች መረጃዎች

ይህ ሰነድ ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመበት ቀን (ቁ. 1.0)፦ ጁን 30፣ 2020።

ሰርቲፊኬሽን ለማግኘት “አስገዳጅ” ተብለው የተጠቀሱ ሰነዶች መሟላት አለባቸው። “አስገዳጅ ያልሆኑ” ተብለው የተጠቀሱ ሰነዶች፣ አንባቢዎች መስፈርቶችንና ሌሎች አስገዳጅ ይዘቶችን እንዲረዱና እንዲተገብሩ ለመርዳት አስገዳጅ ያልሆኑ መረጃዎችን ይሰጣሉ።

የትርጉም ማሳሰቢያ

በትርጉም ውስጥ ባለው መረጃ ትክክለኛ ትርጉም ላይ ለሚነሱ ማናቸውም ጥያቄዎች፣ ግልጽነት ለማግኘት ይፋዊ የእንግሊዝኛ ቅጂን ይመልከቱ። በትርጉም ምክንያት የሚፈጠሩ ማንኛውም ስህተቶች ወይም የትርጉም ልዩነቶች አስገዳጅ አይደሉም እና ለኦዲት ወይም ለሰርቲፊኬሽን ዓላማዎች ምንም ውጤት አይኖራቸውም።

ይህንን ይዘት ከሬንፎረስት አሊያንስ ቅድሚያ የጽሑፍ ፈቃድ ውጭ ማባዛት፣ ማሻሻል፣ ማሰራጨት ወይም እንደገና ማተም በጥብቅ የተከለከለ ነው።

ተጨማሪ መረጃ?

የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬት ለማግኘት እርዳታ ለማግኘት የደንበኛ ስኬት ቡድናችንን customersuccess@ra.org ላይ ያግኙ።

ስለ ሬንፎረስት አሊያንስ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ http://www.rainforest-alliance.org ይጎብኙ፣ info@ra.org ላይ ወይም የሬንፎረስት አሊያንስ አምስተርዳም ቢሮ፣ De Ruijterkade 6፣ 1013AA Amsterdam፣ The Netherlands ያግኙን።

የግርጌ ማስታወሻዎች

  1. ምንጭ፦ ሥነ-ምህዳራዊ መልክዓ ምድር ህብረት 2025 ከሚለው የተወሰደ።

  2. ምንጭ፦ የተባይ እና የአረም አያያዝ (USDA) 2025 ከሚለው የተወሰደ።  

  3. ምንጭ፦ ቃላት እና ትርጓሜዎች፣ የተጠያቂነት ማዕቀፍ ኢኒሼቲቭ 2024 ከሚለው የተወሰደ።

  4. ምንጭ፦ የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መብቶች ስምምነት (UN CRC) አንቀጽ 1።

  5. ምንጭ፦ OECD፣ ለኢንቨስትመንት የሚሆን የፖሊሲ ማዕቀፍ፣ 2015 ከሚለው የተወሰደ።  

  6. ምንጭ፦ የUSDA እይታዎች እና ፕሮግራሞች 2025 ከሚለው የተወሰደ።

  7. ምንጭ፦ ዓለም አቀፍ የሃይድሮሎጂ የቃላት ዝርዝር፣ WMO/UNESCO, 2011

  8. ምንጭ፦ የቴክኒክ መመሪያ USDA-NRCS ማሳሰቢያ 256-10/2013 ከሚለው የተወሰደ።  

  9. ምንጭ፦ የቃላት እና ትርጓሜዎች፣ የተጠያቂነት ማዕቀፍ ተነሳሽነት 2024።

  10. ምንጭ፦ ከISO 9000:2015 የተወሰደ።  

  11. ምንጭ፦ ለዘላቂነት ሥርዓቶች የISEAL መልካም የሥራ አፈጻጸም ሕግ ከሚለው የተወሰደ።

  12. ምንጭ፦ ISO 9000:2005።

  13. ምንጭ፦ ዓለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ (IFAD) ከሚለው የተወሰደ።

  14. ምንጭ፦ የማዳበሪያ ዘላቂ አጠቃቀምና አያያዝ ዓለም አቀፍ የሥነ-ምግባር ሕግ፣ FAO 2019 ከሚለው የተወሰደ።  

  15. ምንጭ፦ ከISO/IEC 17011:2017 የተወሰደ።

  16. ምንጭ፦ ILO የጥቃት እና ትንኮሳ ስምምነት፣ 2019 (ቁጥር 190)።

  17. ምንጭ፦ የተባበሩት መንግሥታት የሴቶች ድርጅት (UN Women)፣ OSAGI የሥርዓተ ፆታ እኩልነትን ማስፈን - ጽንሰ ሀሳቦች እና ትርጓሜዎች ከሚለው የተወሰደ።

  18. ምንጭ፦ የተባበሩት መንግስታት ሴቶች፣ OSAGI የሥርዓተ ፆታ ዋና አጀንዳ ማስቀመጥ - ጽንሰ ሐሳቦች እና ትርጉሞች።  

  19. ምንጭ፦ ከFAO / USDA-NRCS 2025 የተወሰደ።

  20. ምንጭ፦ ከISO/IEC 17000:2020 የተወሰደ።  

  21. ምንጭ፦ ከአነስተኛ ይዞታ የዛፍ ሰብል ሙሉ ለሙሉ ማደስ እና መልሶ ማቋቋም (R&R) IDH -Dalberg 2015 የተወሰደ።

  22. ምንጭ፦ የILO ዝቅተኛ የዕድሜ ስምምነት ቁ. 138  

  23. ምንጭ፦ ከFAO ስታትስቲካዊ ልማት ተከታታይ የተወሰደ።

  24. ምንጭ፦ ከAGROVOC / FAO 2024 የተወሰደ።

  25. ምንጭ፦ ILO ስምምነት ቁጥር 190።

  26. ምንጭ፦ ሴቶች ላይ የሚደርስ ማንኛውም ዓይነት መድልዎ እንዲወገድ የተደረገ የተባበሩት መንግሥታት ስምምነት ከሚለው የተወሰደ።

  27. ምንጭ፦ የተባይ ስጋት ተጋላጭነት ትንተና ማዕቀፍ፣ ዓለም አቀፍ የዕፅዋት ጥበቃ ስምምነት (IPPC) ከሚለው የተወሰደ።

  28. ምንጭ፦ ከFAOTERM፣ FAO፣ 2022 የተወሰደ።

  29. ምንጭ፦ ከOECD፣ የስታቲስቲክስ ቃላት ዝርዝር፣ 2008 የተወሰደ።

  30. ምንጭ፦ ከISO 16559:2014 እና በአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ (EPA) መሠረት ከሚለው የተወሰደ።

  31. ምንጭ፦ የISO ስታንዳርዶች።  

  32. ምንጭ፦ የግብርና ባዮቴክኖሎጂ የቃላት ዝርዝር USDA 2025 ከሚለው የተወሰደ።

  33. ምንጭ፦ ከምግብ እና እርሻ ድርጅት FAO የተወሰደ።  

  34. ምንጭ፦ ከISO 9001 የተወሰደ።  

  35. ምንጭ፦ የተባበሩት መንግስታት መሪ መርሆች ሪፖርት ማዕቀፍ እና የአፈጻጸም እና የማረጋገጫ መመሪያው። Shift Project Ltd. © 2015 Shift Project Ltd., © 2015 Forvis Mazars LLP.  

  36. ምንጭ፦ ከISO 9000:2015 የተወሰደ።  

  37. ምንጭ፦ የቃላት እና ትርጓሜዎች፣ የተጠያቂነት ማዕቀፍ ተነሳሽነት 2024።

  38. ምንጭ፦ የተጠያቂነት ማዕቀፍ ተነሳሽነት ቃላት እና ትርጓሜዎች 2024 ከሚለው የተወሰደ።

  39. ምንጭ፦ የቃላት እና ትርጓሜዎች፣ የተጠያቂነት ማዕቀፍ ተነሳሽነት 2024።

  40. ምንጭ፦ የተባበሩት መንግስታት የአየር ንብረት ለውጥ ማዕቀፍ ስምምነት (UNFCCC)።

  41. ምንጭ፦ የተባበሩት ግዛቶች የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ EPA 2025 ከሚለው የተወሰደ።

  42. ምንጭ፦  ILO በነፃ ግዛቶች ውስጥ ስለሚገኙ የሀገር በቀል እና የጎሳ ሕዝቦች ስምምነት ቁጥር 169፣ በነባር ሕዝቦች ላይ ስለሚደርሰው መድልዎ ችግር የተደረገ ጥናት፣ ስለ “ነባር ሕዝቦች” ጽንሰ ሀሳብ የተባበሩት መንግሥታት የሥራ መገለጫ ሰነድ ከሚለው የተወሰደ። ሕዝቦች።

  43. ምንጭ፦ የነባር ሕዝቦች መብቶች አዋጅ።

  44. ምንጭ፦ FAO እና የዓለም ጥምር እርሻ ማዕከል 2025 ከሚለው የተወሰደ።  

  45. ምንጭ፦ በፀረ-ተባይ አያያዝ ላይ ዓለም አቀፍ የሥነ-ምግባር ሕግ FAO እና WHO 2014 እና የተባበሩት ግዛቶች የአካባቢ ጥበቃ ኤጀንሲ (EPA) ከሚለው የተወሰደ።  

  46. ምንጭ፦ ከዓለም ጤና ድርጅት፣ የጤና ርዕሶች የተወሰደ።

  47. ከOECD ግምገማ እና ውጤት ተኮር አስተዳደር 2002 ከተወሰደ ISEAL የተስተካከለ።  

  48. ምንጭ፦ ከFAOTERM-FAO እና CADDIS – EPA 2025 የተወሰደ።  

  49. ምንጭ፦ የተጠያቂነት ማዕቀፍ ኢኒሼቲቭ ቃላት እና ትርጓሜዎች 2024 ከሚለው የተወሰደ።

  50. ምንጭ፦ ከISO 31000 የተወሰደ።  

  51. ምንጭ፦ የILO አድልዎ (ቅጥር እና ሥራ) ስምምነት፣ 1958 (ቁ. 111)።

  52. ምንጭ፦ ሴቶች ላይ የሚደርስ ማንኛውም ዓይነት መድልዎ እንዲወገድ የተደረገ ስምምነት (CEDAW) ከሚለው የተወሰደ።

  53. ምንጭ፦ ከAGROVOC – FAO 2024 የተወሰደ።

  54. ምንጭ፦ FAO TECA 2020 እና የአፈር ጤና USDA ከሚለው የተወሰደ።  

  55. ምንጭ፦ የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮች መምሪያ፣ ስታትስቲክስ።

  56. ምንጭ፦ ከFAO የተወሰደ።  

  57. ምንጭ፦ AGROVOC-FAO፣ 2022 እና የቃላት አገልግሎቶች EPA 2004 ከሚለው የተወሰደ።  

  58. ምንጭ፦ ከISO 9001:2015 የተወሰደ።  

  59. ምንጭ፦ ከIPCC፣ 2018 የተወሰደ፦ ዓባሪ I፦ የMatthews, J.B.R. (ed.) የቃላት ዝርዝር ውስጥ፦ የ1.5°C የዓለም ሙቀት መጨመር።

  60. ምንጭ፦ ቃላት እና ትርጓሜዎች፣ የተጠያቂነት ማዕቀፍ ኢኒሼቲቭ 2024 ከሚለው የተወሰደ።

  61. ምንጭ፦ ኮዴክስ አልሜንታሪየስ FAO – WHO 2024 ከሚለው የተወሰደ።  

  62. ምንጭ፦ HCV አውታረመረብ።  

  63. ምንጭ፦ ዓለም አቀፍ የተፈጥሮ ጥበቃ ህብረት (IUCN) ከሚለው የተወሰደ።  

  64. ምንጭ፦ የፀረ-ተባይ ሠራተኞች ደህንነት EPA 2025 እና በፀረ-ተባይ አስተዳደር ላይ ዓለም አቀፍ የሥነ-ምግባር ሕግ FAO -WHO 2020 ከሚለው የተወሰደ።  

  65. ምንጭ፦ የFAO እና WHO የፀረ-ተባይ መግለጫዎች ልማት እና አጠቃቀም መመሪያ 2001 እና USDA የደን አገልግሎት 2012 ከሚለው የተወሰደ።  

  66. ምንጭ፦ ከILO ዝቅተኛ የሥራ ቅጥር ዕድሜ ስምምነት (ቁ. 138) የተወሰደ።

  67. ምንጭ፦ የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት (ILO)።

  68. ምንጭ፦ ILO ስምምነት፣ የከፋ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ ስምምነት፣ 1999 (ቁ. 182)።

  69. ምንጭ፦ የILO ስምምነት ቁ. 182 አንቀጽ 3 እና የILO ማሳሰቢያ ቁ. 190 አንቀጽ 3።  

  70. ምንጭ፦ የILO ዝቅተኛ የዕድሜ ስምምነት፣ 1973 (ቁ. 138)።

  71. ምንጭ፦  የILO-IOE የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛ መመሪያ መሣሪያ ለንግዶች / ለዓለም አቀፍ የሥራ ቢሮ፣ የILO ዓለም አቀፍ የሕፃናት ጉልበት ብዝበዛን የማስወገድ ፕሮግራም፤ ዓለም አቀፍ የአሰሪዎች ድርጅት - ጄኔቫ፦ ILO፣ 2015።

  72. ምንጭ፦ የILO የመደራጀት ነፃነት እና የመደራጀት መብት ጥበቃ ስምምነት ቁ. 87።

  73. ምንጭ፦ ከISO 9000:2015 የተወሰደ።  

  74. ምንጭ፦ የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ አገልግሎቶች (NRCS) USDA 2009 ከሚለው የተወሰደ።  

  75. ምንጭ፦ ILO የሠራተኞች ተወካዮች ምክር፣ 1971 (ቁጥር 143)።

  76. ምንጭ፦ ILO የመደራጀት ነፃነት እና የመደራጀት መብትን ማስጠበቅ ስምምነት ውስጥ ካለው ትርጓሜ (ILO) ስለ አመፅ እና ትንኮሳ ስምምነት፣ 2019 (ቁጥር 190) አንቀጽ 10 ላይ የተወሰደ።

  77. ምንጭ፦ ከISO – ሰርቲፊኬሽን የተወሰደ።  

  78. ምንጭ፦ ከIFOAM እና FAO ትርጉሞች ከተወሰደ።  

  79. ምንጭ፦ አነስተኛ አርሶ አደሮች የዛፍ ሰብል ዕድሳት እና ማገገሚያ IDH Dahlberg 2015 ከሚለው የተወሰደ።

  80. ምንጭ፦ ከISO 31000:2009 የተወሰደ።  

  81. ለዘላቂነት ሥርዓቶች የISEAL መልካም የሥራ አፈጻጸም ሕግ ከሚለው የተወሰደ።  

  82. ምንጭ፦ FAO የአፈር ፖርታል 2025 ከሚለው የተወሰደ።  

  83. ምንጭ፦ ረቂቅ ህዋሳት እንደ የአፈር ጤና አመላካቾች። ብሔራዊ የአካባቢ ጥናት ተቋም፣ ዴንማርክ። ቴክኒካዊ ሪፖርት ቁ. 388፣ 2002።

  84. ምንጭ፦ ለዘላቂነት ሥርዓቶች የISEAL መልካም የሥራ አፈጻጸም ሕግ ከሚለው የተወሰደ።

  85. ምንጭ፦ AR4 የአየር ንብረት ለውጥ ሪፖርት IPCC ከሚለው የተወሰደ።  

  86. ምንጭ፦ የተባይ እና ፀረ-ተባይ አያያዝ FAO እና የተቀናጀ የተባይ አያያዝ (IPM) መርሆዎች EPA 2025 ከሚለው የተወሰደ።

  87. ምንጭ፦ ዘላቂ የሰብል ምርት ማጠናከሪያ የተጠናቀረ ስብስብ FAO 2025 ከሚለው የተወሰደ።

  88. ምንጭ፦ ከISO 9000:2005 የተወሰደ።

  89. ምንጭ፦ መንግሥታትን አቀፍ የሳይንስ-ፖሊሲ የባዮሎጂያዊ ብዝሃነት እና ሥነ-ምህዳር አገልግሎት ፕላትፎርም IPBES 2025 ከሚለው የተወሰደ።

  90. ምንጭ፦ ከILO የቤት ውስጥ ሠራተኞች ስምምነት 2011 (ቁ. 189) የተወሰደ።

  91. ምንጭ፦ የማዳበሪያ ዘላቂ አጠቃቀምና አያያዝ ዓለም አቀፍ የሥነ-ምግባር ሕግ፣ FAO ከሚለው የተወሰደ።

  92. ምንጭ፦ የደን ሀብት ምዘና (FRA 2020) FAO 2018 ከሚለው የተወሰደ።

  93. ምንጭ፦ ተፈጥሮ ጠላቶች የእጅ መጽሐፍ፣ የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ-ግብርና እና የተፈጥሮ ሀብቶች 2019 ከሚለው የተወሰደ።  

  94. ምንጭ፦ ግሎባል ሊቪንግ ዌጅ ኮአሊሽን።  

  95. ምንጭ፦ ከግሎባል ሊቪንግ ዌጅ ኮአሊሽን (Global Living Wage Coalition) የተወሰደ።  

  96. ምንጭ፦ ግሎባል ሊቪንግ ዌጅ ኮአሊሽን።

  97. ምንጭ፦ ለጥበቃ እና ለተሻሻለ የግብርና ምርት የንፋስ መከላከያዎችን መጠቀም NRCS-USDA ከሚለው የተወሰደ።

  98. ምንጭ፦ ከIPCC፣ 2018 የተወሰደ፦ ዓባሪ I፦ የቃላት ዝርዝር ውስጥ፦ የ1.5°C የዓለም ሙቀት መጨመር።

  99. ምንጭ፦ ከIPCC፣ 2018 የተወሰደ፦ ዓባሪ I፦ የቃላት ዝርዝር ውስጥ፦ የ1.5°C የዓለም ሙቀት መጨመር።

  100. ምንጭ፦ ከIPCC፣ 2018 የተወሰደ፦ ዓባሪ I፦ የቃላት ዝርዝር ውስጥ፦ የ1.5°C የዓለም ሙቀት መጨመር።

  101. ምንጭ፦ የአፈር ኦርጋኒክ ይዘት፣ የአፈር ጤና መመሪያ USDA-NRCS ከሚለው የተወሰደ።  

  102. ምንጭ፦ ዓለም አቀፍ የአፈር ጤና አመልካቾች እና ግምገማ FAO 2025 ከሚለው የተወሰደ።

  103. ምንጭ፦ ምንጭ፦ የእንስሳት ደህንነት ኮሚቴ (AWC) 2019።

  104. ምንጭ፦ የቃላት እና ትርጓሜዎች፣ የተጠያቂነት ማዕቀፍ ተነሳሽነት 2024።

  105. ምንጭ፦ ለምግብ ዋስትና የሚሆን የዕፅዋት አመጋገብ FAO 2006 ከሚለው የተወሰደ።

  106. ምንጭ፦ ከISO 9001:2015 የተወሰደ።

  107. ምንጭ፦ ለግብርና መሬት የሚሆኑ የውሃ ዳርቻ ጥበቃ ቀጠና USDA-NAC 1997 ከሚለው የተወሰደ።

  108. ምንጭ፦ ቃላት እና ትርጓሜዎች፣ የተጠያቂነት ማዕቀፍ ተነሳሽነት 2024፣ እና FRA 2020፣ FAO ከሚለው የተወሰደ።  

  109. ምንጭ፦ ቃላት እና ትርጓሜዎች EUDR 2023 እና FRA 2020፣ FAO ከሚለው የተወሰደ።  

  110. ምንጭ፦ አጥንት ያላቸው ተባዮችን የመቆጣጠሪያ ኬሚካሎች እና በከተማና ገጠር አካባቢዎች ውስጥ አጠቃቀማቸው፣ የፀረ-ተባይ መርዛማነት መመሪያ መጽሐፍ 2001 ከሚለው የተወሰደ።

  111. ምንጭ፦ ILO በሥራ ቦታ መሠረታዊ መርሆዎችና መብቶች ላይ ካወጣው መግለጫ የተወሰደ።  

  112. ምንጭ፦ ከዓለም ጤና ድርጅት (WHO) የተወሰደ።  

  113. ምንጭ፦ የILO ግዳጅ ሥራ ስምምነት፣ የ ILO ፕሮቶኮል 2014 ለግዳጅ ሥራ ስምምነት፣ 1930።

  114. ምንጭ፦ የቃላት እና ትርጓሜዎች FRA 2020፣ FAO ከሚለው የተወሰደ።

  115. ምንጭ፦ ጊዜ ያለፈባቸው ፀረ-ተባዮች FAO 2025 ከሚለው የተወሰደ።

  116. ምንጭ፦ ስለ ጥምር እርሻ FAO 2025 ከሚለው የተወሰደ።  

  117. ምንጭ፦ ኮዴክስ አሊሜንታሪየስ FAO-WHO 2025 እና የአካባቢ ፀረ-ተባይ ቁጥጥር EPA 2025 ከሚለው የተወሰደ።

  118. ምንጭ፦ FAO የፀረ-ተባይ ምዝገባ መሳሪያ ስብስብ 2016 እና EPA ከሚለው የተወሰደ።

  119. ምንጭ፦ ሥርዓተ ፆታ፣ ፍትሃዊነትና ሰብአዊ መብቶች፣ የቃላት እና የመሳሪያዎች የቃላት ዝርዝር WHO፣ እና የፆታ ጽንሰ ሀሳቦች እና ትርጓሜዎች፣ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አጋር ከሚለው የተወሰደ።  

  120. ምንጭ፦ ILO በሥራ ዓለም ውስጥ ያለ የጾታዊ ትንኮሳ ከሚለው የተወሰደ።  

  121. ምንጭ፦ የአሜሪካ የዕፅዋት ፓቶሎጂ ማኅበር እና FAO ፣ 2004 ከሚለው የተወሰደ።

  122. ምንጭ፦ ከAGROVOC FAO 2022 የተወሰደ።