
ርዕስ፦ | የአመራር አባሪ |
ኮድ፦ | A-04-SCRL-B-CH |
እትም፦ | 1.2 |
የሚመለከተው፦ | የእርሻ ሰርቲፊኬት ባለቤቶች |
አፈጻጸም፦ | አስገዳጅ ይዘት |
ተፈጻሚነት የሚጀምርበት ቀን፦ | የካቲት 22፣ 2018 ዓ.ም |
የሚያበቃበት ጊዜ፦ | እስከሚቀጥለው ማሳሰቢያ ድረስ |
የታተመበት ቀን፦ | መስከረም 7፣ 2018 ዓ.ም. |
ከሚከተለው ጋር ይገናኛል፦ | |
የሚከተለውን ይተካል፦ |
ይህ ሰነድ ስለ ምንድን ነው?
ይህ አባሪ በሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች ውስጥ በሚገኘው የአመራር ምዕራፍ ውስጥ ያሉትን መስፈርቶች ከተግባራዊነት ጋር በተያያዘ ተጨማሪ አስገዳጅ ይዘቶችን ያካትታል።
ይህ ሰነድ የሚከተሉትን ያካትታል፦
ስለ ጂኦሎኬሽን ውሂብ (Geolocation data) አሰባሰብ በመሠረታዊ መስፈርቶች 1.2.10 እና 1.2.11 ላይ ተጨማሪ ዝርዝሮች።
ስለ የውስጥ ኢንስፔክተሮች ስልጠና በመሠረታዊ መስፈርት 1.3.3 ላይ ተጨማሪ ዝርዝሮች።
ስለ የውስጥ ኢንስፔክሽኖች በመሠረታዊ መስፈርት 1.4.1 ላይ ተጨማሪ ዝርዝሮች።
በመሠረታዊ መስፈርቶች 1.1.1 እና 1.4.3 ተፈጻሚነት ላይ ግልጽ ማብራሪያ።
ይህንን ሰነድ መቼ እና እንዴት መጠቀም ይቻላል?
ይህ ሰነድ ለሰርቲፊኬት ባለቤቶች እና ለሰርቲፊኬሽን አካላት በሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች ውስጥ በተካተቱት መሠረታዊ መስፈርቶች ላይ ተጨማሪ ዝርዝሮችን ይሰጣል።
ከእትም 1.1 ወደ እትም 1.2 የተደረጉ ዋና ለውጦች
ክፍል | የተደረገው ለውጥ |
በመላው ሰነዱ | የሬንፎረስት አሊያንስ ተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ ተካቷል። |
1. የጂኦሎኬሽን ውሂብ መሰብሰብ | የናሙና ሰንጠረዥ ተወግዷል እና ጽሑፉ ለግልጽነት ሲባል በድጋሚ ተረቅቋል። |
3. ማብራሪያ | በመስፈርቶች 1.1.1 እና 1.4.3 ላይ ስለ ተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ የተጠቀሱ ነጥቦችን ግልጽ ለማድረግ ይህ ክፍል ተጨምሯል። |
1. የጂኦሎኬሽን ውሂብ መሰብሰብ
1.1 መግቢያ
በሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች መስፈርቶች 1.2.10 እና 1.2.11 ላይ በተገለጸው መሠረት፣ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች የጂኦሎኬሽን ውሂብን ለሬንፎረስት አሊያንስ ፕላትፎርም ማቅረብ አለባቸው። ይህ ክፍል እነዚህን መስፈርቶች ማሟላት ስለሚቻልበት ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ይዟል።
1.2 የጂኦሎኬሽን ውሂብ አሰባሰብ መስፈርቶች
የሰርቲፊኬት ባለቤቶች የሁሉንም የእርሻ ክፍሎች የጂኦሎኬሽን ውሂብ በአካባቢ ነጥብ እና በፖሊገን መልክ የማቅረብ ኃላፊነት አለባቸው። የእርሻ ክፍሎች እርስ በርሳቸው በተለያዩ ርቀቶች ላይ ሊገኙ ይችላሉ፤ እንዲሁም የግድ ጎን ለጎን መሆን የለባቸውም።
ክፍል 1.3 እና 1.4 የሰርቲፊኬት ባለቤቶች የአካባቢ ነጥብ እና የፖሊገን መረጃዎችን ለመሰብሰብ ሊጠቀሙባቸው የሚችሏቸውን ዘዴዎች ያጠቃልላሉ። የጂኦሎኬሽን ውሂብ ወደ ሬንፎረስት አሊያንስ የሰርቲፊኬሽን ፕላትፎርም ከመጫኑ በፊት በዚህ ሰነድ ውስጥ ያሉትን ሁሉንም የፎርማት መስፈርቶች ማሟላት አለበት።
1.3 የአካባቢ ነጥቦች
የአካባቢ ነጥቦች በሚከተለው መልኩ መሰብሰብ አለባቸው፦
መጋጠሚያዎች (Coordinates) በእርሻው ወይም በእርሻ ክፍሉ ውስጥ ያሉ ሁኔታዎችን (ለምሳሌ፡ ከፍተኛ ገደሎች፣ ወንዞች፣ ወጣ ገባ እና አደገኛ የመሬት ገጽታዎች) ግምት ውስጥ በማስገባት፣ በተቻለ መጠን ለእርሻው ወይም ለእርሻ ክፍሉ ማዕከል ቅርብ በሆነ ቦታ መወሰድ አለባቸው።
መጋጠሚያዎችን የሚወስደው ሰው የነጥቡን አካባቢ ምልክት ማድረግ አለበት (ለምሳሌ፡ መሬት ላይ እንጨት በመትከል፣ አቅራቢያ የሚገኝ ዛፍ ላይ ምልክት በማድረግ ወዘተ)። ይህም ውሂቡን ለማረጋገጥ ሲባል በውስጥ ኢንስፔክተሮች ወይም በውጭ ኦዲተሮች አማካኝነት ተመሳሳይ አካባቢ ጥቅም ላይ መዋሉን ለማረጋገጥ ነው።
የኬክሮስ (latitude) እና የኬንትሮስ (longitude) መጋጠሚያዎች (Coordinates) በትክክል ሪፖርት መደረግ አለባቸው፦
የኬክሮስ እና የኬንትሮስ መጋጠሚያዎች አሁን ያለውን የዓለም ጂኦዴቲክ ሥርዓት (ዴተም፦ WGS 84 – ኮድ፦ EPSG፦ 4326) በመጠቀም መሰብሰብ አለባቸው።
እንደ የቁጥር ፎርማት፣ የቁጥር እሴቶችን ብቻ የያዘ መሆን አለበት። እንደ የዲግሪ ምልክት (°) ያሉ ቁምፊዎች አይፈቀዱም።
እንደ ዲሲማል ዲግሪ መጋጠሚያ (ዲዲ ፎርማት)
ቢያንስ 4 የዲሲማል ቦታዎች ያሉት (ለምሳሌ፦ ኬክሮስ 9.7611፤ ኬንትሮስ –84.1872) መሆን አለበት።
ትክክለኛ ፖዘቲቭ እና ኔጋቲቭ እሴቶች ያሉት መሆን አለበት። በደቡባዊ ሄሚስፈር (hemisphere) ያሉ ነጥቦች ኔጋቲቭ ኬክሮስ ያላቸው ሲሆን፣ በሰሜናዊ ሄሚስፈር ያሉ ነጥቦች ደግሞ ፖዘቲቭ ኬክሮስ አላቸው። በምዕራባዊ ሄሚስፈር ያሉ ነጥቦች ኔጋቲቭ ኬንትሮስ ያላቸው ሲሆን፣ በምስራቃዊ ሄሚስፈር ያሉ ነጥቦች ደግሞ ፖዘቲቭ ኬንትሮስ አላቸው። ሆኖም የ“+” ምልክትን ማካተት አስፈላጊ አይደለም፣ የኔጋቲቭ ምልክቱን “-” ብቻ መጠቀም ይቻላል (ለምሳሌ ኬክሮስ፡ 9.7611፤ ኬንትሮስ፡ -84.1872)።
የኬክሮስ እና የኬንትሮስ እሴቶችን ቦታ ቀያይሮ መመዝገብ መወገድ አለበት።
መጋጠሚያዎቹ በሬንፎረስት አሊያንስ ፕላትፎርም ወይም በሬንፎረስት አሊያንስ በሚታዘዝ ሌላ ማንኛውም መሣሪያ ላይ እና ሬንፎረስት አሊያንስ በሚፈልገው ቴምፕሌት መሠረት መቅረብ አለባቸው።
በፕላትፎርሙ ላይ የሚቀርብ እያንዳንዱ የእርሻ ክፍል ውሂብ ነጥብ ልዩ የእርሻ ክፍል መታወቂያ ሊኖረው ይገባል።
1.4 ፖሊገኖች
በሬንፎረስት አሊያንስ የሰርቲፊኬሽን ፕላትፎርም ላይ የሚቀርብ እያንዳንዱ የእርሻ ክፍል ፖሊገን ልዩ የእርሻ ክፍል መታወቂያ ሊኖረው ይገባል።
የሰርቲፊኬት ባለቤቶች ከዚህ በታች በተቀመጡት ሁለት ዘዴዎች አንዱን በመጠቀም ፖሊገኖችን መሰብሰብ ይችላሉ። ለዝርዝር መመሪያዎች፣ ስለ ጂኦሎኬሽን ውሂብ እና የአደጋ ካርታዎች የቀረበውን የሬንፎረስት አሊያንስ መመሪያ መመልከት ይቻላል።
1.4.1 በማጣቀሻ አካባቢ ነጥቦች ላይ የተመሰረቱ ፖሊገኖች
ለፖሊገን ውሂብ የሚያገለግሉ ሁሉም የማጣቀሻ ነጥቦች በመስክ ላይ መሰብሰብ አለባቸው። ከወረቀት ወይም ከዲጂታል ካርታ ብቻ የተገኙ የፖሊገን ውሂቦች ትክክለኛ ስላልሆኑ ተቀባይነት የላቸውም። የፖሊገን ማጣቀሻ ነጥቦችን በመስክ ላይ ከሰበሰቡ በኋላ፣ ፖሊገኑን የጂኦግራፊያዊ መረጃ ሥርዓት GIS ላይ የተመሰረቱ ሶፍትዌሮችን ወይም ተመሳሳይ መሣሪያዎችን በመጠቀም መፍጠር ይቻላል።
1.4.2 በመስክ ላይ የተሰበሰቡ ፖሊገኖች
በመስክ ላይ የተሰበሰቡ የእርሻ ድንበር ፖሊገኖች፣ ማናቸውንም አለመጣጣሞች ለመለየት እና ለማስተካከል እንደ QGIS፣ Google My Maps ወይም Google Earth Pro ያሉ የጂኦግራፊያዊ መረጃ ሥርዓት (GIS) ሶፍትዌሮችን በመጠቀም መገምገም አለባቸው።
እነዚህን መሣሪያዎች እንዴት መጠቀም እንደሚቻል የሚገልጹ ተጨማሪ መረጃ ያላቸው መመሪያዎች በሬንፎረስት አሊያንስ ድር ጣቢያ ላይ ይገኛሉ፦ የሰርቲፊኬሽን ፕሮግራም።
ስለ የእርሻ ክፍል ፖሊገኖች የቀረቡ ተጨማሪ መስፈርቶች፦
የእርሻ ክፍል ፖሊገኖች ከሌላ ፖሊገን ጋር ከስፋታቸው 20% በላይ መደራረብ የለባቸውም።
የእርሻ ክፍል ፖሊገኖች ትክክለኛ ጂኦሜትሪ ሊኖራቸው ይገባል።
እርስ በርሳቸው የሚቀራረቡ የእርሻ ክፍል ፖሊገኖች የጋራ ድንበር ሊኖራቸው ይችላል።
በምስል ላይ በቀላሉ የሚታዩ ነገሮችን (እንደ መንገዶች እና ወንዞች ያሉ) የሚከተሉ ድንበሮች፣ የፖሊገን ካርታ ስራውን ይበልጥ ትክክለኛ ለማድረግ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ።
1.5 የውሂብ ሪፖርት አቀራረብ
ከዚህ በታች ያለው ሰንጠረዥ በሬንፎረስት አሊያንስ ፕላትፎርም ላይ የጂኦሎኬሽን ውሂብን ሪፖርት ለማድረግ የሚያስፈልጉትን የፋይል አይነቶች እና ፎርማቶች ያሳያል።
ሰንጠረዥ 1. ጂኦሎኬሽን ውሂብ ተቀባይነት ያላቸው ፎርማቶች እና ቴምፕሌቶች
የስታንዳርድ መስፈርቶች | መቅረብ ያለባቸው | ተቀባይነት ያለው የፋይል አይነት |
1.2.10 ሰርቲፋይድ ለሆነው ሰብል 100% የጂኦሎኬሽን ውሂብ ለእርሻ ክፍሎች) | የአካባቢ ነጥቦችን የያዘ አንድ ፋይል። | የቡድን አባል መዝገብ (GMR) ቴምፕሌት "3. Farm Unit" ታብ (የኬክሮስ እና የኬንትሮስ ዓምዶችን በመጠቀም)። |
ፖሊገኖችን የያዘ አንድ ፋይል። | KML ወይም GeoJSON | |
1.2.11 | ሁሉንም የእርሻ ክፍሎች የሚያካትት የእርሻ ቦታው ፖሊገኖች ያሉበት አንድ ፋይል። | KML ወይም GeoJSON |
1.5.1 ለውሂብ ሪፖርት አቀራረብ ግምት ውስጥ የሚገቡ ሌሎች ነጥቦች፦
ትላልቅ እርሻዎች የቡድን አካል ሲሆኑ፣ መስፈርት 1.2.11 በእነዚህ ትላልቅ እርሻዎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። የሚቀርበው የጂኦዳታ ፋይል የቡድኑ አካል የሆኑትን ሁሉንም ትላልቅ እርሻዎች ፖሊገኖች መያዝ አለበት።
የመጀመሪያው ኦዲት በሚዘጋጅበት ጊዜ፣ የሰርቲፊኬት ባለቤቱ በሰንጠረዥ 2 ላይ የተጠቀሱትን የጂኦዳታ ፋይሎች በሬንፎረስት አሊያንስ የሰርቲፊኬሽን ፕላትፎርም ላይ መጫን አለባቸው።
አንድ የሰርቲፊኬት ባለቤት ተጨማሪ የፖሊገን ፋይሎችን ማቅረብ የሚችሉት፣ በሬንፎረስት አሊያንስ ፕላትፎርም ላይ የጸደቀ የቡድን አባል መዝገብ ካቀረቡ በኋላ ብቻ ነው።
የአካባቢ ነጥቦችን በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ለእያንዳንዱ የእርሻ ክፍል የሚከተሉት የውሂብ ነጥቦች በቡድን አባል መዝገብ ታብ 3 በኩል መቅረብ አለባቸው፦
ልዩ የውስጥ እርሻ መታወቂያ (እርሻው የቡድኑ አካል መሆኑን ለመለየት)።
የእርሻ ክፍል መታወቂያ (የእርሻ ክፍሉን የየትኛው እርሻ አካል እንደሆነ ለማገናኘት)።
የእርሻ ክፍል ስፋት (በሄክታር)።
የኬክሮስ መጋጠሚያዎች (ዲዲ ፎርማት)።
የኬንትሮስ መጋጠሚያዎች (ዲዲ ፎርማት)።
የፖሊገን ፋይሎችን በሚያቀርቡበት ጊዜ ለእያንዳንዱ የእርሻ ክፍል የሚከተሉት መረጋገጥ አለባቸው፦
ፖሊገኖች ልዩ ከሆነ የእርሻ ክፍል መታወቂያ ጋር መቅረብ አለባቸው።
ፖሊገኑን ከመጫንዎ በፊት፣ የእርሻ ክፍሉ በሬንፎረስት አሊያንስ ፕላትፎርም የእርሻ መረጃ ክፍል ውስጥ አስቀድሞ ተመዝግቦ መቆየት አለበት። (ለቡድን ሰርቲፊኬት፣ የእርሻ መረጃው በቡድን አባል መዝገብ ውስጥ ከቀረበው መረጃ በቀጥታ በራሱ ጊዜ የሚሞላ ነው)።
2. የውስጥ ኢንስፔከሽኖች
2.1 የውስጥ ኢንስፔክሽኖች ወሰን
የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርድ መሠረታዊ መስፈርት 1.4.1፣ የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርድ መስፈርቶች በሁሉም የቡድኑ አባላት ዘንድ ተግባራዊ መደረጋቸውን ለማረጋገጥ አመራሩ የውስጥ ኢንስፔክሽን ሥርዓት እንዲዘረጋ ያዝዛል። አመራሩ የውስጥ ኢንስፔክሽን ሥርዓቱ በትክክል እንዲሠራ ሁሉንም አስፈላጊ ግብዓቶች ማቅረብ አለበት።
ወደ ሰርቲፊኬሽን ፕሮግራም የሚገቡ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች አመራር፣ ከመጀመሪያው የሰርቲፊኬት ኦዲት በፊት በሰርቲፊኬቱ ወሰን ውስጥ ያሉ ሁሉም ተሳታፊዎች በሚመለከቷቸው የስታንዳርድ መስፈርቶች መሠረት የውስጥ ኢንስፔክሽን መደረጉን ማረጋገጥ አለበት።
ለቀጣይ ኦዲቶች፣ የውስጥ ኢንስፔክሽኖች የሚከናወኑት በአደጋ ስጋት እንዲሁም በቀደሙት የውስጥ ኢንስፔክሽኖች እና የውጭ ኦዲቶች ውጤቶች ላይ ተመስርቶ ነው።
በተጨማሪም፣ ለቀጣይ የውስጥ ኢንስፔክሽኖች ያለው ወሰን ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ተዘርዝሯል፦
ሰንጠረዥ 2. በእርሻ ዓይነት እና መዋቅር መሠረት የውስጥ ኢንስፔክሽን ወሰን።
የእርሻ ዓይነት | የውስጥ ኢንስፔክሽን ወሰን |
ትላልቅ እርሻዎች | ሁሉም እርሻዎች ላይ በየዓመቱ ኢንስፔክሽን መደረግ አለበት።
|
አነስተኛ እርሻዎች | በየዓመቱ ቢያንስ 35% የሚሆኑት እርሻዎች ኢንስፔክሽን ይደረግባቸዋል፣ ይህም በሦስት ተከታታይ ዓመታት ውስጥ ሁሉም እርሻዎች መፈተሻቸውን ያረጋግጣል። ማሳሰቢያ፦ ሬንፎረስት አሊያንስ ለአንድ የተወሰነ ሰብል ወይም በአንድ የተወሰነ አገር ወይም ክልል ውስጥ ከፍተኛ የናሙና መጠን እንዲኖር የመጠየቅ መብቱ የተጠበቀ ነው። |
ከአንድ በላይ የእርሻ ክፍሎች ያሏቸው አነስተኛ እርሻዎች | ኢንስፔክሽን የሚደረግባቸው የእርሻ ክፍሎች ምርጫ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ የተመሰረተ ነው፦
|
ማሳሰቢያ፦ ሁሉም አዲስ አባላት ከውጭ ኦዲት በፊት በሚመለከታቸው የስታንዳርድ መስፈርቶች መሠረት ሙሉ በሙሉ ኢንስፔክት መደረግ አለባቸው።
2.2 የውስጥ ኢንስፔክተሮች ስልጠና
አመራሩ ጥራት ያለው የውስጥ ኢንስፔክሽን ለማካሄድ የውስጥ ኢንስፔክተሮች በቂ ስልጠና ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለበት። ስልጠናዎቹ የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርድ አተገባበርን እና ኦዲት አሰራርን በሚያውቁ ብቁ ባለሙያዎች መሰጠት አለባቸው።
እንዲሁም አመራሩ ሁሉም የውስጥ ኢንስፔክተሮች በሬንፎረስት አሊያንስ የመማሪያ ኔትወርክ ላይ የታዘዙትን ሁሉንም ኮርሶች መውሰዳቸውን እና አስፈላጊዎቹን ግምገማዎች ማጠናቀቃቸውን ማረጋገጥ ይኖርበታል። በተጨማሪም፣ በመስፈርት 1.3.3 መሠረት አመራሩ ለሁሉም ኢንስፔክተሮች ስለ ትክክለኛ የውስጥ ኢንስፔክሽን አሰራር ዓመታዊ ስልጠና የመስጠት እና የዓመት ግምገማዎችንም ጭምር የማካሄድ ግዴታ አለበት።
3. የ1.1.1 እና 1.4.3 መስፈርቶች ተፈጻሚነት ማብራሪያ
በተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ ሰርቲፋይድ የሆኑ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች ወይም ሰርቲፊኬሽን ለማግኘት የሚፈልጉ 1.1.1 እና 1.4.3 መስፈርቶችን ማሟላት አለባቸው። በተጨማሪም፣ የሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂ ግብርና ስታንዳርድን የሚጠቅሱ መሠረታዊ መስፈርቶች፣ የሬንፎረስት አሊያንስ ተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድን እንደሚጠቅሱ ተደርገው መወሰድ አለባቸው።
ሌሎች መረጃዎች
ይህ ሰነድ ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመበት ቀን (ቁ. 1.0)፦ ሰኔ 24፣ 2014 ዓ.ም.
ሰርቲፊኬሽን ለማግኘት “አስገዳጅ” ተብለው የተጠቀሱ ሰነዶች መሟላት አለባቸው። “አስገዳጅ ያልሆኑ” ተብለው የተጠቀሱ ሰነዶች፣ አንባቢዎች መስፈርቶችንና ሌሎች አስገዳጅ ይዘቶችን እንዲረዱና እንዲተገብሩ ለመርዳት አስገዳጅ ያልሆኑ መረጃዎችን ይሰጣሉ።
የትርጉም ማሳሰቢያ
በትርጉሙ ውስጥ ስላለው መረጃ ትክክለኛ ትርጉም ማንኛውም ጥያቄ ሲኖር፣ ለማብራሪያ የእንግሊዝኛውን ኦፊሴላዊ እትም ያማክሩ። በትርጉም ምክንያት የሚፈጠሩ ማንኛውም ስህተቶች ወይም የትርጉም ልዩነቶች አስገዳጅ አይደሉም እና ለኦዲት ወይም ለሰርቲፊኬሽን ዓላማዎች ምንም ውጤት አይኖራቸውም።
ይህንን ይዘት ከሬንፎረስት አሊያንስ ቅድሚያ የጽሑፍ ፈቃድ ውጭ ማባዛት፣ ማሻሻል፣ ማሰራጨት ወይም እንደገና ማተም በጥብቅ የተከለከለ ነው።
ተጨማሪ መረጃ?
የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬት ለማግኘት እገዛ ከፈለጉ የደንበኛ ስኬት ቡድናችንን customersuccess@ra.org ላይ ያግኙ።
ስለ ሬንፎረስት አሊያንስ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ http://www.rainforest-alliance.org ይጎብኙ፣ info@ra.org ላይ ወይም የሬንፎረስት አሊያንስ አምስተርዳም ቢሮ፣ De Ruijterkade 6፣ 1013AA Amsterdam፣ The Netherlands ያግኙን።
Env