
ርዕስ፦ | የትረሰብሊቲ አባሪ | |
ኮድ፦ | A-05-SRCL-B-CH | |
እትም፦ | 1.4 | |
የሚመለከተው፦ | የእርሻና የአቅርቦት ሰንሰለት ሰርቲፊኬት ባለቤቶችን | |
አፈጻጸም፦ | አስገዳጅ ይዘት | |
ተፈጻሚነት የሚጀምርበት ቀን፦ | ገና የሚወሰን (TBD) | |
የሚያበቃበት ጊዜ፦ | እስከሚቀጥለው ማሳሰቢያ ድረስ | |
የታተመበት ቀን፦ | ጳጉሜ 3፣ 2017 ዓ.ም. | |
ከሚከተለው ጋር ይገናኛል | A-1-S-B-F-V1.4 የሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው ግብርና ስታንዳርድ። | |
የሚከተለውን ይተካል፦ | ||
ይህ ሰነድ ስለ ምንድን ነው?
ይህ አባሪ በሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች እና በሬንፎረስት አሊያንስ የአቅርቦት ሰንሰለት መስፈርቶች ውስጥ በሚገኘው የትረሰብሊቲ ምዕራፍ ውስጥ ለተካተቱት መስፈርቶች ተጨማሪ አስገዳጅ ይዘቶችን ይዟል።
ይህ ሰነድ የሚከተሉትን ያካትታል፦
ለትረሰብሊቲ ኃላፊነት ስላለባቸው ተዋናዮች ዝርዝር መረጃ።
ስለ የተለያዩ የትረሰብሊቲ አማራጮች ትርጓሜዎች ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ።
ይህንን ሰነድ መቼ እና እንዴት መጠቀም ይቻላል?
ይህ ሰነድ ለሰርቲፊኬት ባለቤቶች እና ለሰርቲፊኬሽን አካላት በእርሻ ስታንዳርዶች እና በአቅርቦት ሰንሰለት መስፈርቶች ውስጥ ስለተካተቱት መሠረታዊ መስፈርቶች እና እነሱነ ስለመተግበር ተጨማሪ መረጃ ይሰጣል።
ከእትም 1.3 ወደ እትም 1.4 የተደረጉ ለውጦች
ክፍል | የተደረገው ለውጥ |
በመላው ሰነዱ | የተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ ተጨማሪ |
2.2.1 | በንግድ ምልክት/ቸርቻሪ ፋንታ በተጠናቀቀ ምርት አምራች በኩል የሚጠየቅ ትረሰብሊቲ። |
1. መግቢያ
ይህ አስገዳጅ ሰነድ ለሰርቲፊኬት ባለቤቶች (CHs) ከሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው ግብርና ስታንዳርድ እና ከተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ ጋር ለተያያዙ የምርት መጠኖች፣ የሬንፎረስት አሊያንስ የአቅርቦት ሰንሰለት የትረሰብሊቲ መስፈርቶችን ስለመተግበር መረጃ ይሰጣል።
ስለ ደንቦቹ እና መስፈርቶቹ አፈጻጸም ተጨማሪ መረጃ በሬንፎረስት አሊያንስ የትረሰብሊቲ መመሪያ ሰነድ ውስጥ ይገኛል።
ለትረሰብሊቲ መስፈርቶች ያለው ወሰን እና ተፈጻሚነት
ትረሰብሊቲ በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ተብለው የሚሸጡ ምርቶች ፍሰት እና ታማኝነት የተረጋገጠ እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን፣ የሰርቲፊኬሽን ይገባኛል ጥያቄዎችን ትክክለኛነት ያረጋግጣል። ሁሉም የእርሻ እና የአቅርቦት ሰንሰለት የሰርቲፊኬት ባለቤቶች በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ፕሮግራም (RACP) ውስጥ ከተመዘገቡ በኋላ በአውድ መሠረት በተዘጋጀው የፍተሻ ዝርዝር ውስጥ ያሉትን አስገዳጅ መስፈርቶች መከተል አለባቸው።
የትረሰቢሊቲ ዓይነቶች
ሰርቲፋይድ በሆኑ የአቅርቦት ሰንሰለቶች ውስጥ የሚከተሉት የትረሰብሊቲ ዓይነቶች ከ“ከፍተኛ” እስከ “ዝቅተኛ” ተዘርዝረው ይገኛሉ፦ የማንነት ጥበቃ (IP)፣ መለያየት (SG) እና ጅምላ ሚዛን (MB)።
የማንነት ጥበቃ (IP)
ይህ በጣም ጥብቅ የሆነው የትረሰብሊቲ ዓይነት ሲሆን፣ ሰርቲፋይድ የሆነውን ምርት ምንጩን እስከ እርሻው የሰርቲፊኬት ባለቤት ድረስ ማረጋገጥ ይቻላል። ሰርቲፋይድ የሆነ ምርት ሰርቲፋይድ ካልሆነ ምርት ጋር፣ ወይም ከተለያዩ ምንጮች ከመጡ ሰርቲፋይድ ምርቶች ጋር አይቀላቀልም።
ሰርቲፋይድ የሆነ ምርት ከተለያዩ ሰርቲፋይድ ምንጮች/እርሻዎች የመጣ ከሆነ፣ ነገር ግን ማንነቱ በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ከተጠበቀ፣ የተደባለቀ የማንነት ጥበቃ (Mixed IP) የተባለው ንዑስ ዓይነት ሊተገበር ይችላል።
ለዚህ የትረሰብሊቲ ዓይነት፣ ሰርቲፋይድ የሆኑ ምርቶች ሰርቲፋይድ ካልሆኑ ምርቶች በአካልም ሆነ በሰነድ ተለይተው ይቀመጣሉ። መለያየት በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ባሉ ሁሉም የመቀበያ፣ ማቀነባበሪያ፣ ማሸግ፣ ማከማቻ እና ማጓጓዣ) ደረጃዎች ውስጥ ይከሰታል። ይህም ማለት የምንጩ ማንነት ባይታወቅም እንኳን ምርቱ ሙሉ በሙሉ ሰርቲፋይድ ነው።
የጅምላ ሚዛን (MB)
ጅምላ ሚዛን ሰርቲፋይድ እና ሰርቲፋይድ ያልሆኑ ምርቶች ሊቀላቀሉ የሚችሉበት አስተዳደራዊ የትረሰብሊቲ ዓይነት ነው። ሆኖም ግን፣ ሰርቲፋይድ ተብሎ የሚሸጠው የምርት መጠን በመጀመሪያ ሰርቲፋይድ ተብሎ ከተገዛው የምርት መጠን መብለጥ የለበትም። የአቅርቦት ሰንሰለት የሰርቲፊኬት ባለቤት (CH) ሁሉንም ሰርቲፋይድ የሆኑ እና ያልሆኑ ገቢና ወጪ ምርቶችን በሰነድ መመዝገብ እንዲሁም የሰርቲፋይድ ምርት ሽያጭ መጠን በትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ በትክክል መንጸባረቁን ማረጋገጥ አለበት።
አንድን የትረሰብሊቲ ዓይነት ወደ ሌላ ማሳደግ አይቻልም። ለምሳሌ በመለያየት (SG) ደረጃ የተገዛን ምርት በማንነት ጥበ (IP) ደረጃ መሸጥ አይቻልም። ሆኖም ግን፣ ከአንድ ከፍተኛ የትረሰብሊቲ ዓይነት ወደ ዝቅተኛ ዝቅ ማድረግ (ለምሳሌ ከመለያየት ወደ ጅምላ ሚዛን) ይፈቀዳል።
የትረሰብሊቲ ዓይነቶች ወሰን
የማንነት ጥበቃ በሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬሽን ወሰን ውስጥ በሚገኝ በማንኛውም ሰብል ላይ ተፈጻሚ ሊሆን ይችላል።
መለያየት በማንኛውም ወሰን ውስጥ ባለ ሰብል ላይ ተፈጻሚ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን በእርሻ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች (CHs) ሊተገበር አይችልም።
ጅምላ ሚዛን በአቅርቦት ሰንሰለት የሰርቲፊኬት ባለቤቶች (CHs) አማካኝነት በሚከተሉት ሰብሎች ላይ ተፈጻሚ ሊሆን ይችላል፦ ኮኮዋ፣ የተቀነባበሩ ፍራፍሬዎች (የብርቱካን ጭማቂን ጨምሮ)፣ ሐዘል ነት (hazelnut)፣ cashews፣ አልሞንድ፣ የኮኮናት ዘይት፣ አበባዎች[1]፣ እንዲሁም ዋና ዕጽዋቶች እና ቅመማ ቅመሞች[2]። የእርሻ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች (CHs) የጅምላ ሚዛን የትረሰብሊቲ ዓይነትን ለሐዘል ነት፣ cashews፣ ለአልሞንድ፣ ለኮኮናት ዘይት እና ለአበቦች ብቻ መተግበር ይችላሉ።
2. ትረሰብሊቲ
መስፈርት 2.1.1 የአቅርቦት ሰንሰለት፣ 2.1.3 እርሻ – መለያየት
ሬንፎረስት አሊያንስ በእርሻ ደረጃ የተለያዩ ስታንዳርዶችን አስተዋውቋል። ለተለያዩ የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርዶች ሰርቲፋይድ የሆኑ እና ምርቶችንም የሚይዙ የእርሻ እና የአቅርቦት ሰንሰለት የሰርቲፊኬት ባለቤቶች (CHs)፣ በሁሉም ደረጃዎች (የምርት ስብሰባ፣ ማከማቻ፣ ትራንስፖርት፣ ማቀነባበር እና ማሸግን ጨምሮ) እነዚያን ምርቶች በአካላዊ መንገድ ለያይተው ማቆየት አለባቸው።
እንዲሁም የሬንፎረስት አሊያንስ የምርት መጠኖች በሌላ የሰርቲፊኬሽን ዘዴ ሰርቲፋይድ ከሆኑ ወይም ሰርቲፋይድ ካልሆኑ ምርቶች ተለይተው መቀመጥ አለባቸው።
መስፈርት 2.1.4 የአቅርቦት ሰንሰለት፣ 2.1.5 እርሻ – ሰነድ
የገቢ እና የወጪ ሰነዶች ስለ ሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ምርት መጠኖች እንዲሁም እነዚያ የምርት መጠኖች ስለተያያዙበት የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርድ ማጣቀሻዎችን ማካተት አለባቸው። ለምሳሌ፦ የሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው ግብርና ስታንዳርድ ወይም ተሃድሶ ግብርና ስታንዳርድ።
መስፈርት 2.1.6 የአቅርቦት ሰንሰለት፣ 2.1.7 እርሻ – ሁለት ጊዜ መሸጥ (Double Selling)
ሁለት ጊዜ መሸጥ (Double Selling) ማለት አንድን ተመሳሳይ የሰርቲፋይድ ምርት መጠን ሁለት ጊዜ የመሸጥ ልምድ ነው። ይህም አንድ ጊዜ በሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርድ፣ እና በድጋሚ በሌላ የሬንፎረስት አሊያንስ ስታንዳርድ፣ በሌላ የሰርቲፊኬሽን ዘዴ ወይም እንደ ተራ ምርት መሸጥን ይጨምራል። ሁለት ጊዜ መሸጥ (Double Selling) የተከለከለ ነው።
ለምሳሌ፣ በአንድ እርሻ የተመረተ 100 ሜትሪክ ቶን ቡና በሁለቱም እንደ ኦርጋኒክ እና የሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው የግብርና ስታንዳርድ ሰርቲፋይድ ሊሆን ይችላል እና የሚከተለውን ሆኖ ሊሸጥ ይችላል፦
100 ሜትሪክ ቶን በሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው የግብርና ስታንዳርድ ሰርቲፋይድ ብቻ፣ ወይም
100 ሜትሪክ ቶን ኦርጋኒክ ብቻ፣ ወይም
100 ሜትሪክ ቶን በሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው የግብርና ስታንዳርድ እና ኦርጋኒክ (በአንድ ጊዜ በአንድ ስብስብ ውስጥ) ለአንድ ገዢ።
ይሁን እንጂ፣ ያው የቡና መጠን ለብቻው 100 ሜትሪክ ቶን ኦርጋኒክ ቡና እንዲሁም 100 ሜትሪክ ቶን በሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው የግብርና ስታንዳርድ ወይም ታዳሽ (Regenerative) ግብርና ሰርቲፋይድ ቡና ተለይቶ ሊሸጥ አይችልም።
3. በኦንላይን ፕላትፎርም ላይ የሚከናወን ትረሰብሊቲ
የሬንፎረስት አሊያንስ የትረሰብሊቲ ፕላትፎርም የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ምርት በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ያለውን እንቅስቃሴ የሚያሳይ ሲሆን፣ በሰርቲፊኬት ባለቤት (CH) ደረጃ ተፈጻሚ የሚሆን ነው። በትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ ያለው የምርት መጠን የሬንፎረስት አሊያንስ ዘላቂነት ያለው ግብርና ወይም ተሃድሶ ግብርና የምርት መጠኖችን (ወይም ሁለቱንም) የሚለይ ይሆናል። በብዙ ቦታዎች ላይ ለሚንቀሳቀሱ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች፣ የማዕከላዊ አመራር ቦታው ለትረሰብሊቲ መስፈርቶች ኃላፊነት ይወስዳል። በአጠቃላይ፣ ትረሰብሊቲ ሕጋዊ ባለቤትነትን ይከተላል። በተመሳሳይ ሰርቲፊኬት ውስጥ በተካተቱ የተለያዩ ቦታዎች መካከል ለሚደረግ የሰርቲፋይድ ምርቶች እንቅስቃሴ ትረሰብሊቲ አያስፈልግም።
በፕላትፎርሙ ላይ የሚመዘገቡ ተግባራት የሰርቲፋይድ ምርት ሽያጭን፣ መለወጥ፣ ማረጋገጥን፣ መቀላቀልን፣ መጠቀምን፣ ማስወገድን እና ደረጃ ዝቅ ማድረግን ያካትታሉ።
መስፈርት 2.1.2 የአቅርቦት ሰንሰለት፣ 2.1.9 እርሻ – ሰርቲፋይድ ምርትን መለወጥ
የሰርቲፋይድ ምርት መጠንን ለሚለውጡ እንደ ማዘጋጀት/ማቀነባበር ያሉ ተግባራት (ለምሳሌ፡ ከጥሬ ቡና ወደ የተቆላ ቡና የሚደረግ ዝግጅት/ማቀነባበር)፣ የአቅርቦት ሰንሰለት የሰርቲፊኬት ባለቤት (CH) ለሌላ አካል ከመሸጡ በፊት በትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ "መለወጥ" (conversion) የሚለውን ተግባር ማከናወን አለበት። ውጤቱ የተለየ ምርት ለሚሆን (ለምሳሌ፡ ብዙ ግብዓቶች ያሉበት ምርት) ነገር ግን መጠኑን ለማይለውጡ እንደ ማምረት ያሉ ተግባራት፣ የአቅርቦት ሰንሰለት የሰርቲፊኬት ባለቤት (CH) ለሌላ አካል ከመሸጡ በፊት በትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ "ማምረትን ማሳወቅ" (report manufacturing) የሚለውን ተግባር ማከናወን አለበት።
በትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ ለሌላ አካል እንዲሸጡ የማይፈለጉ እና በአቅርቦት ሰንሰለት የሰርቲፊኬት ባለቤት (CH) በኩል ጥቅም ላይ መዋል (redeemed) ያለባቸው ምርቶች፣ ጥቅም ላይ ከመዋላቸው በፊት እነዚህን ተግባራት ማከናወን አያስፈልግም (በክፍል 5 ስር ያለውን የለውጥ ተመኖች ይመልከቱ)። በአቅርቦት ሰንሰለት መጨረሻ ላይ ለሚኖር አማራጭ ትረሰብሊቲ (ማለትም እስከ ቸርቻሪ ድረስ ላለው ትረሰብሊቲ)፣ እነዚህ ተግባራት ከመሸጣቸው በፊት መከናወን አያስፈልጋቸውም።
መስፈርት 2.1.4 የአቅርቦት ሰንሰለት፣ 2.1.5 እርሻ – የሰርቲፋይድ ምርት የደረሱ ግብይቶችን መቆጣጠር
በአቅራቢዎች የሚሸጡ የሰርቲፋይድ ምርቶች ግብይቶች፣ ሰርቲፋይድ ምርቱን በሚገዛው የሰርቲፊኬት ባለቤት (CH) መገምገም እና መረጋገጥ[3] አለባቸው።
መስፈርት 2.2.1 የአቅርቦት ሰንሰለት እና እርሻ – የሰርቲፋይድ ምርት የሚላኩ ግብይቶችን መቆጣጠር
ሁሉም የሰርቲፋይድ ምርቶች ግብይቶች፣ ከእርሻ የሰርቲፊኬት ባለቤት (CH) ጀምሮ እስከ መጨረሻው የሸማች ምርቶች አምራች (ወይም ለትኩስ ፍራፍሬዎችና አትክልቶች አስመጪ) ድረስ በሬንፎረስት አሊያንስ ትረሰብሊቲ ፕላትፎርም ላይ ሪፖርት መደረግ አለባቸው።)። እንደ የመጨረሻ የሸማች ምርት ሆነው የሚሸጡ የምርት መጠኖች ከትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ ጥቅም ላይ መዋል4 አለባቸው።
የሰርቲፋይድ ምርት መጠኖችን ማስወገድ
ሰርቲፋይድ ተብለው ያልተሸጡ የሰርቲፋይድ ምርት መጠኖች (እንደ ተራ ምርት፣ በሌላ የሰርቲፊኬሽን ዘዴ ሰርቲፋይድ ተብለው የተሸጡ ወይም የተበላሹ ወይም የጠፉ) ከትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ መወገድ አለባቸው። የጅምላ ሚዛን ምርት መጠኖች ከትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ እንዲወገዱ አይገደዱም፤ ነገር ግን ተመጣጣኝ የሆነው የሰርቲፋይድ ምርት መጠን ሲሸጥ ለገዢው የሽያጭ ግብይት (አስፈላጊ ከሆነ) መከናወን አለበት።
መቼ ሪፖርት መደረግ እንዳለበት
ሁሉም ተግባራት በተከናወኑበት የካላንደር ሩብ ዓመት (ከጥር – መጋቢት፣ ከሚያዝያ – ሰኔ፣ ከሐምሌ – መስከረም፣ ከጥቅምት – ታህሳስ) ማብቂያ ጀምሮ ባሉት 2 ሳምንታት ውስጥ በትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ ሪፖርት መደረግ አለባቸው።
ምሳሌ 1፦ በግንቦት ወር ውስጥ አካላዊ ሽያጭ ከተከናወነ - የሰርቲፊኬት ባለቤቱ (CH) የሽያጭ ግብይቱን ቢዘገይ እስከ ሐምሌ 7 ድረስ ሪፖርት ማድረግ አለበት።
ምሳሌ 2፦ በታህሳስ ወር እንደ ተራ ምርት የተሸጠ የሰርቲፋይድ ምርት መጠን፣ በሚቀጥለው ዓመት እስከ ጥር 6 ድረስ ከትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ መወገድ አለበት።
የአቅርቦት ሰንሰለት የሰርቲፊኬት ባለቤት (CH) አቅራቢው የሽያጭ መረጃ ገና ስላልደረሰው በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለገዢው የሰርቲፋይድ ምርት ሽያጭ ማሳወቅ ካልቻለ፣ የሰርቲፊኬት ባለቤቱ አቅራቢውን ለማነጋገር ተገቢውን ጥረት ማድረጉን ማሳየት ይኖርበታል።
መስፈርት 2.2.2 የአቅርቦት ሰንሰለት፣ 2.2.4 እርሻ – ሮያሊቲ (Royalty)
በሬንፎረስት አሊያንስ የፈቃድ ስምምነት አጠቃላይ ውሎች እና ሁኔታዎች መሠረት፣ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች (CHs) ለእያንዳንዱ የሚመለከተው ሰብል እና ስታንዳርድ በሮያሊቲ ተመን ሰንጠረዥ (Royalty Schedule) መሠረት የሮያሊቲ ክፍያዎችን መፈጸም አለባቸው።
4. የጅምላ ሚዛን
መስፈርት 2.3.1 የአቅርቦት ሰንሰለት እና እርሻ – የምርት መጠን ለውጥ
በጅምላ ሚዛን ደንቦቻችን መሠረት፣ ሰርቲፋይድ ምርት መጠኖችን ወደ ተራ ምርት መጠኖች መለወጥ የሚፈቀደው ለተመሳሳይ ምርቶች ወይም በአካላዊ የዝግጅት/ማቀነባበር አቅጣጫ ብቻ ነው፤ ለምሳሌ፦
ሰርቲፋይድ የኮኮዋ ቅቤ ወደ ተራ የኮኮዋ ቅቤ
ሰርቲፋይድ የኮኮዋ ፍሬ ወደ ተራ የኮኮዋ ቅቤ
ሰርቲፋይድ በሽፋኑ ያለ ሐዘል ነት (hazelnut) ወደ ተራ የተቆላ የሐዘል ነት ፍሬ
ሰርቲፋይድ ያልተጣራ የኮኮናት ዘይት ወደ ተራ የጠራ የኮኮናት ዘይት
ወደ ኋላ መልሶ መለወጥ (Backward conversion) አይፈቀድም፤ ለምሳሌ፦
ሰርቲፋይድ ፈሳሽ ኮኮዋ ወደ ተራ የኮኮዋ ኒብስ (ተፈትገው የተሰባበሩ የኮኮዋ ፍሬዎች)
ሰርቲፋይድ ቸኮሌት ወደ ተራ የኮኮዋ ቅቤ
ሰርቲፋይድ የኮኮዋ ቅቤ ወደ ተራ የኮኮዋ ዱቄት
ሰርቲፋይድ የተፈተገ የሐዘል ነት ፍሬ ወደ ሽፋን ያለው ሐዘል ነት
መስፈርቶች 2.3.4 እና 2.3.5 የአቅርቦት ሰንሰለት እና እርሻ – የመገኛ ቦታ መጣጣም (Origin matching)
ለኮኮዋ ዘርፍ የሚከተሉት የመገኛ ቦታ መጣጣም መስፈርቶች እና ትርጓሜዎች ተፈጻሚ ይሆናሉ፦
ትርጓሜዎች
ዓመታዊ የምርት መጠን | በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ የተከናወነ የእውነተኛ ሰርቲፋይድ የፈሳሽ ኮኮዋ ሽያጭ አጠቃላይ ድምር መጠን። |
መገኛ ቦታ | ሰርቲፋይድ የኮኮዋ ፍሬዎች የተመረቱበት አገር። |
የመገኛ ቦታ አሻራ | በትረሰብሊቲ ፕላትፎርም ላይ ላለ አንድ የሰርቲፋይድ ኮኮዋ መጠን፣ የእርሻ የሰርቲፊኬት ባለቤቱ (CH) የሚገኝበት አገር። |
የመገኛ ቦታ መጣጣም | አንድ የሰርቲፋይድ ኮኮዋ መጠን በሚገዛበት ጊዜ፣ ተመጣጣኝ የሆነ ተራ የኮኮዋ መጠን እንደ ሰርቲፋይድ አድርጎ ለመሸጥ የሁለቱም መጠኖች መገኛ ቦታ አንድ መሆን አለበት (በእያንዳንዱ ግብይት ወይም በአጠቃላይ ድምር መሠረት)። |
የአቅርቦት እቅድ | የመገኛ ቦታ መጣጣም መስፈርቶችን ለማሟላት የሰርቲፋይድ ምርት አቅርቦትን ለመለወጥ የሚዘጋጅ እቅድ። ይህ እቅድ ለሬንፎረስት አሊያንስ መቅረብና በእሱ መጽደቅ አለበት። |
ወሰን
በትረሰብሊቲ ፕላትፎርም ውስጥ ለሚከናወኑ ሁሉም ግብይቶች የመገኛ ቦታ መጣጣም ግዴታ የሚሆነው፣ ለደረጃ 1 መስፈርቶች ከመጋቢት 23 ቀን 2013 ዓ.ም. ጀምሮ፣ እንዲሁም ለደረጃ 2 መስፈርቶች ከመስከረም 20 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ውል ለተፈረመባቸው ነው።
ይህም በትረሰብሊቲ ፕላትፎርም ላይ የመገኛ ቦታ አሻራቸው የሚታይ ሁሉንም የጅምላ ሚዛን ሰርቲፋይድ የኮኮዋ ምርቶችን ያጠቃልላል።
የደረጃ 1 መስፈርቶች
የኮኮዋ ፍሬዎች እና ኒብስ (ተፈትገው የተሰባበሩ የኮኮዋ ፍሬዎች)
በአቅርቦት ሰንሰለት የሰርቲፊኬት ባለቤቶች (CHs) መካከል ለሚደረግ ለእያንዳንዱ የሰርቲፋይድ የኮኮዋ ፍሬዎች እና ኒብስ (ተፈትገው የተሰባበሩ የኮኮዋ ፍሬዎች) ግዢ እና ሽያጭ ግብይት 100% የመገኛ ቦታ መጣጣም ያስፈልጋል። እንደ ሰርቲፋይድ ለሚሸጡ ፍሬዎች እና ኒብስ (ተፈትገው የተሰባበሩ የኮኮዋ ፍሬዎች) የሚዘጋጁ የግዢ እና የሽያጭ ሰነዶች፣ ለሁለቱም ለሰርቲፋይድ እና ለተራ ፍሬዎች እና ኒብስ (ተፈትገው የተሰባበሩ የኮኮዋ ፍሬዎች) እስከ አገር ደረጃ ድረስ ያለውን የመገኛ ቦታ መረጃ መያዝ አለባቸው።
ፈሳሽ ኮኮዋ
በአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ለሚከናወን የመጀመሪያው የሰርቲፋይድ ፈሳሽ ኮኮዋ ሽያጭ፣ በእያንዳንዱ የ12 ወራት ጊዜ ውስጥ ባለው አጠቃላይ ድምር (aggregate level) መሠረት የመገኛ ቦታ መጣጣም ያስፈልጋል። ኩባንያዎች ለጅምላ ሚዛን ሰርቲፋይድ ፈሳሽ ኮኮዋ የመገኛ ቦታ መጣጣም ዓመታዊ መጠናቸውን ማስላት እና የስሌቱን ማስረጃ ማያያዝ አለባቸው። በአቅርቦት ሰንሰለት የሰርቲፊኬት ባለቤት (CH) ደረጃ የሚዘጋጁ ሰነዶች፣ ለሰርቲፋይድ እና ሰርቲፋይድ ላልሆኑ የኮኮዋ ግብዓቶች እስከ አገር ደረጃ ድረስ ያለውን የመገኛ ቦታ መረጃ መያዝ አለባቸው።
ለአጠቃላይ የሰርቲፋይድ ፈሳሽ ኮኮዋ ሽያጭ እና ለዓመታዊ መጠኑ መገኛ ቦታዎች ይነጻጸራሉ፤ ቢያንስ 80% የሚሆነው መጠን የመገኛ ቦታ መጣጣም ሊኖረው ይገባል።
በ12 ወራቱ ጊዜ ውስጥ የመገኛ ቦታ መጣጣሙ ከ80% በታች ከሆነ፣ የጎደለው መጠን በሚቀጥሉት 3 ወራት ውስጥ መሟላት አለበት።
የደረጃ 2 መስፈርቶች
ከኮትዲቯር፣ ጋና እና ኢኳዶር ወደ ውጭ የሚላኩ
ከሁሉም የደረጃ 1 መስፈርቶች በተጨማሪ፣ ከምርቱ መገኛ አገር (ለኮትዲቯር፣ ጋና እና ኢኳዶር) ወደ ውጭ ለሚላክ ለእያንዳንዱ የሰርቲፋይድ ፈሳሽ ኮኮዋ፣ የኮኮዋ ቅቤ ወይም የኮኮዋ ዱቄት የሽያጭ ግብይት 100% የመገኛ ቦታ መጣጣም ያስፈልጋል። ከአስመጪው ደረጃ በላይ ላለ ለማንኛውም የአቅርቦት ሰንሰለት የሰርቲፊኬት ባለቤት (CH) የመገኛ ቦታ መጣጣም አይገደድም።
የመገኛ ቦታ ክልላዊ አቀራረብ
ከኮኮዋ ፍሬዎች እና ከኒብስ (ተፈትገው የተሰባበሩ የኮኮዋ ፍሬዎች) በስተቀር ለሌሎች ምርቶች ሁሉ፣ ከታች ባለው ሰንጠረዥ እንደተገለጸው የተወሰኑ ትናንሽ የአምራች አገራትን በማጣመር የመገኛ ቦታ መጣጣምን በክልል ደረጃ ማከናወን ይቻላል፦
ክልል | አገራት | ልዩ ሁኔታዎች |
ምዕራብ አፍሪካ | ጊኒ፣ ላይቤሪያ፣ ቶጎ፣ ሴራ ሊዮን እና ሌሎች የምዕራብ አፍሪካ አገራት | ያልተካተቱ፦ ካሜሩን፣ ኮትዲቯር፣ ጋና፣ ናይጄሪያ፣ ማዳጋስካር ወይም በማዕከላዊ እና ምስራቅ አፍሪካ ስር የተዘረዘሩ አገራት |
ማዕከላዊ እና ምስራቅ አፍሪካ | ኮንጎ፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ጋቦን፣ ሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ፣ ታንዛኒያ፣ ዩጋንዳ | ያልተካተቱ፦ ካሜሩን፣ ማዳጋስካር |
ላቲን አሜሪካ | ቤሊዝ፣ ቦሊቪያ፣ ኮስታሪካ፣ ኩባ፣ ዶሚኒካ፣ ግሬናዳ፣ ጓቲማላ፣ ሄይቲ፣ ሆንዱራስ፣ ጃማይካ፣ ሜክሲኮ፣ ኒካራጓ፣ ፓናማ፣ ሳንታ ሉቺያ፣ ትሪኒዳድ እና ቶቤጎ፣ ቬንዙዌላ ወይም ሌሎች የላቲን አሜሪካ አገራት | ያልተካተቱ፦ ብራዚል፣ ኮሎምቢያ፣ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ፣ ኢኳዶር፣ ፔሩ |
እስያ እና ኦሺኒያ | ፊጂ፣ ሕንድ፣ ማሌዥያ፣ ፓፑዋ ኒው ጊኒ፣ ፊሊፒንስ፣ ሰሎሞን ደሴቶች፣ ስሪ ላንካ፣ ታይላንድ፣ ቫኑአቱ፣ ቬትናም ወይም ሌሎች የእስያ እና ኦሺኒያ አገራት | ያልተካተቱ፦ ኢንዶኔዥያ |
5. ለጅምላ ሚዛን ምርቶች የልወጣ ተመኖች
ከታች ያለው ሰንጠረዥ ጅምላ ሚዛን ለተፈቀደባቸው ዘርፎች የልወጣ ተመኖችን ያሳያል። ለመለያየት እና ለማንነት ጥበቃ የተፈቀዱ የልወጣ ተመኖች በትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ አስቀድመው ተለይተው ተቀምጠዋል።
ሰብል/ዘርፍ | የልወጣ ተመን |
ኮኮዋ | |
ፍሬዎች ወደ ፈሳሽ ኮኮዋ | 1:0.82 |
ፍሬዎች ወደ ኒብስ (ተፈትገው የተሰባበሩ የኮኮዋ ፍሬዎች) | 1:0.82 |
ኒብስ ወደ ፈሳሽ ኮኮዋ | 1:1 |
ፈሳሽ ኮኮዋ ወደ ቅቤ እና ዱቄት ብዙ ግብዓት ያለው የኮኮዋ ምርት (የኮኮዋ መጠን) ወደ ሌላ ብዙ ግብዓት ያለው የኮኮዋ ምርት (የኮኮዋ መጠን) | 1:0.5:0.5 1:1 |
ሐዘል ነት (Hazelnut) | |
በሽፋኑ ያለ ወደ የውስጥ ፍሬ | 1:0.5 |
የውስጥ ፍሬ ወደ የተቆላ የውስጥ ፍሬ | 1:0.94 |
የውስጥ ፍሬ ወደ የተቀነባበረ የውስጥ ፍሬ (ለምሳሌ፦ የተላጠ፣ የተከተፈ፣ የተገሸለጠ ወዘተ) | 1:1 |
የተቆላ የውስጥ ፍሬ ወደ የተቀነባበረ የተቆላ የውስጥ ፍሬ | 1:1 |
ኮኮናት | |
ጥሬ ፍሬ ወደ የደረቀ የኮኮናት የውስጥ ክፍል | 1:0.25 |
የደረቀ የኮኮናት የውስጥ ክፍል ወደ ያልተጣራ የኮኮናት ዘይት | 1:0.62 |
ያልተጣራ የኮኮናት ዘይት ወደ የጠራ የኮኮናት ዘይት (RBD) | 1:0.96 |
ያልተጣራ የኮኮናት ዘይት ወደ የጠራ የኮኮናት ዘይት (ሀይድሮጂን የተደረገ) | 1:0.96 |
ካሼውስ እና አልሞንድ (Cashews & Almonds) | |
በሽፋኑ ያለ ወደ የውስጥ ፍሬ | 1:0.25 |
በሽፋኑ ያለ ወደ የውስጥ ፍሬ | 1:0.95 |
የውስጥ ፍሬ ወደ የተቆላ የውስጥ ፍሬ | 1:0.95 |
የውስጥ ፍሬ ወደ ተቀነባበረ የውስጥ ፍሬ | 1:1 |
የተቆላ የውስጥ ፍሬ ወደ የተቀነባበረ የተቆላ የውስጥ ፍሬ | 1:0.95 |
የተቆላ የውስጥ ፍሬ ወደ ፔስት (ከተፈጨ በኋላ የሚገኝ ወፍራም ፈሳሽ) | 1:1 |
ሌሎች መረጃዎች
ይህ ሰነድ ለመጀመሪያ ጊዜ የታተመበት ቀን (ቁ. 1.0)፦ ሰኔ 24፣ 2014
ሬይንፎረስት አሊያንስ እነዚህን ፈቃዶች ለተወሰኑ የሰርቲፊኬት ባለቤቶች (CH) እና እንደየሁኔታው የመገምገም፣ የማጽደቅ፣ የመከልከል ወይም የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ሰርቲፊኬሽን ለማግኘት “አስገዳጅ” ተብለው የተጠቀሱ ሰነዶች መሟላት አለባቸው። “አስገዳጅ ያልሆኑ” ተብለው የተጠቀሱ ሰነዶች፣ አንባቢዎች መስፈርቶችንና ሌሎች አስገዳጅ ይዘቶችን እንዲረዱና እንዲተገብሩ ለመርዳት አስገዳጅ ያልሆኑ መረጃዎችን ይሰጣሉ።
የትርጉም ማሳሰቢያ
በትርጉም ውስጥ ባለው መረጃ ትክክለኛ ትርጉም ላይ ለሚነሱ ማናቸውም ጥያቄዎች፣ ግልጽነት ለማግኘት ይፋዊ የእንግሊዝኛ ቅጂን ይመልከቱ። በትርጉም ምክንያት የሚፈጠሩ ማንኛውም ስህተቶች ወይም የትርጉም ልዩነቶች አስገዳጅ አይደሉም እና ለኦዲት ወይም ለሰርቲፊኬሽን ዓላማዎች ምንም ውጤት አይኖራቸውም።
ይህንን ይዘት ከሬንፎረስት አሊያንስ ቅድሚያ የጽሑፍ ፈቃድ ውጭ ማባዛት፣ ማሻሻል፣ ማሰራጨት ወይም እንደገና ማተም በጥብቅ የተከለከለ ነው።
ተጨማሪ መረጃ?
የሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፊኬት ለማግኘት እገዛ ከፈለጉ የደንበኛ ስኬት ቡድናችንን
ላይ ያግኙ።
ስለ ሬንፎረስት አሊያንስ የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ http://www.rainforest-alliance.org ይጎብኙ፣ info@ra.org ላይ ወይም የሬንፎረስት አሊያንስ አምስተርዳም ቢሮ፣ De Ruijterkade 6፣ 1013AA Amsterdam፣ The Netherlands ያግኙን።
የግርጌ ማስታወሻዎች
ለአበቦች፣ የጅምላ ሚዛን ትረሰብሊቲ የሚከናወነው የሰርቲፊኬት ባለቤቱ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ (ቀን/ሳምንት/ዓመት) በሚቀበለው ሰርቲፋይድ የሆኑ ግብዓቶች (ግንዶች) ብዛት ላይ ተመስርቶ ሲሆን፣ የሰርቲፊኬት ባለቤቱ በመጨረሻው ምርቱ ውስጥ ያለውን የሰርቲፋይድ ግብዓት መቶኛ እንዲገልጽ ያስችለዋል። ↑
ዋና ዕጽዋት እና ቅመማ ቅመሞች የሚባሉት፦ ሮይቦስ (rooibos)፣ ቫኒላ፣ ሳፍሮን፣ በርበሬ፣ ቀረፋ፣ የበርበሬ ቃሪያ፣ ኦሬጋኖ፣ ድንብላል፣ ፓፕሪካ (የቃሪያ ዱቄት)፣ ኮረሪማ፣ እንስላል፣ ቅርንፉድ፣ ፓርስሊ (የሾርባ ቅጠል)፣ ገውዝ፣ ጦስኝ፣ የላውሮ ቅጠል፣ ሮዝመሪና (የስጋ መጥበሻ) እና ታራጎን (tarragon) ናቸው። ↑
ማረጋገጥ = የሰርቲፊኬት ባለቤቱ (CH) ከሰርቲፋይድ አቅራቢዎች የሚመጡ የደረሱ ግብይቶች ዝርዝርን (መጠን፣ የትረሰብሊቲ ደረጃ እና ሌሎች የቀረቡ ማጣቀሻዎች) ከክፍያ መጠየቂያ እና ከአቅራቢዎቻቸው ጋር ካላቸው ውል ጋር የሚስማሙ መሆኑን ገምግሞ ሲያጸድቅ ነው።
4 ጥቅም ላይ ማዋል = የንግድ ምልክት ባለቤት የሆነው የሰርቲፊኬት ባለቤት፣ እንደ መጨረሻ የሸማች ምርት ሆነው የሚሸጡትን የምርት መጠኖች ከትረሰብሊቲ ፕላትፎርሙ ላይ ለይቶ ሲያስወጣ (ሲቀንስ) ነው። "ጥቅም ላይ ማዋል" የሚለው ተግባር ለሬንፎረስት አሊያንስ ሰርቲፋይድ ምርቶች የኦንላይን ትረሰብሊቲ ማብቂያ ምልክት ነው። ↑